ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የብር የመግዛት አቅም ከዶላር አንፃር በ6 ብር ተዳክሟል፡፡
- sheger1021fm
- 41 minutes ago
- 1 min read
ህዳር 25 2018
ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የብር የመግዛት አቅም ከዶላር አንፃር በ6 ብር ተዳክሟል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠናከር እንዳለበት የሚጠበቀው የብር የመግዛት አቅምን እየተዳከመ ቀጥሏል፡፡
ይህም የሰዎችን የመግዛት አቅም የሚፈትን፤ በተለይ ከውጭ የሚመጡ ቁሶችን ዋጋ ደግሞ እጅጉ የሚያስወድድ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ከወጭ ንግድ እና ከተለያዩ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ ምንጮች እየተገኘ ያለው ዶላር ከአምናው ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑ እና በመሰል ምክንያቶች የውጭ ምንዛሬ ገበያው በራሱ መረጋጋት ይጠበቅበት ነበር ያሉት የፕራግማ ካፒታል መስራችና የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ባለሙያው መርዕድ ፍቅረዮሐንስ ናቸው፡፡

ይሁንና በብልሹ አሰራር ፣ በባንኮች ግልፅ ያልሆነ የውጭ ምንዛሬ ግብይትና በተለያዩ ችግሮች ገበያው እንዳልተረጋጋ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ለክፉ ቀን የመጠባበቂያ ክምችቷን ማሳደግ የሚጠበቅባት ኢትዮጵያ በየሁለት ሳምንቱ ሚሊዮን ዶላሮችን በብሔራዊ ባንክ በኩል ለጨረታ እያወጣች ለባንኮች ታስከፍላለች፡፡
እንደ ፖሊሲ እርምጃ ይህ ትክክል ቢሆንም እስከመቼ የሚለው ግን መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው ብለዋል፡፡
እስከመቼ ጨረታ እያወጡ ገበያ የማረጋጋት ስራው ይቀጥላል ሲሉ የሚጠይቁት አቶ መርዕድ የኬንያ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት 12 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ኬንያ በእጅጉ ያነሰ 4 ቢሊዮን ዶላር መጠባበቂያ ክምችት እንዳላት ተናግረው ብሔራዊ ባንክ የሚያወጣው ጨረታ በቀጠለ ቁጥር ክምችቱን እንደሚያሳሳው ነግረውናል፡፡
ይህም በሂደት ችግሮችን ስለሚያስከትል የውጭ ምንዛሬ ገበያው እንዳይረጋጋ የሚያውኩ አሰራሮችን ፈትሾ መፍትሄ መስጠቱ ላይ ትኩረት ቢደረግ መልካም ነው ሲሉ መክረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments