top of page

ኢትዮጵያ በ10 ዓመት፤ ከተቻለም ከዚያ ባጠረ ጊዜ ውስጥ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ትገነባለች ተባለ።

  • sheger1021fm
  • 3 minutes ago
  • 1 min read

ህዳር 29 2018


ኢትዮጵያ በ10 ዓመት፤ ከተቻለም ከዚያ ባጠረ ጊዜ ውስጥ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ትገነባለች ተባለ።


ዛሬ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ዝግጅት፣የኒውክሊየር የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ መጀመር ይፋ ተደርጓል።


በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንም ስራዬን መጀመሬን እወቁት ብሏል።


የኒውክሊየር የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱን ለመገንባት ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ (አይ.ኤ.ኢ.ኤ) የሚያስቀምጣቸውን 19 መሠረታዊ የሆኑ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቃል ተብሏል።


ኢትዮጵያም ይህንኑ መስፈርት አሟልታ በተቆጣጣሪ ኤጀንሲው እገዛና ክትትል ለመስራት ዝግጁ ነች ተብሏል።

ree

የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አብዱረዛቅ ዑመር ሲናገሩ እንደሰማነው የስራው ሂደት ሶስት ምዕራፎች ይኖሩታል።


የመጀመሪያው ምዕራፍ ስራውን ለመጀመር ዝግጁ መሆን የሚበሰርበት የዛሬው አይነት ሂደት ነው ብለዋል።


ሁለተኛው ምእራፍ አማራጭና የግንባታ ቦታን መለየት፣የቴክኖሎጂ መረጣ የጨረታ ሂደትና ሌሎችንም ስራዎች ያጠቃልላል ብለዋል።


ሶስተኛው ምእራፍ የግባታውን ስራ ማጠናቀቅን የሚመለከት እንደሆነ አብራርተዋል።


እያደገ ባለው የሀይል ፍላጎት ውስጥ የኒክሊየር ሀይል ተጨማሪ አማራጭ እንደሚሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጤሞቲዮስ(ዶ/ር) ተናግረዋል።


ኢትዮጵያ ፕሮጀክቱን ተዓማኒ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በፍጥነት መገንባት አለባት ሲሉ የተናገሩት ደግሞ የዓለም አቀፉ የኒክሊየር ኃይል ማመንጫ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካኤል ቹዳኮቭ(ዶ/ር) ናቸው።


ኢትዮጵያ ከሁለት ወር በፊት የኒክሊየር የኃይል ማመንጫውን ለመገንባት ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር ስምምነት መፈረሙ የሚታወስ ነው።


ዛሬ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ጋር በትብብር የተሰናዳው ዝግጅትም ወደ ስራ መገባቱን ማብሰሪያ ትልቁ ምእራፍ ነው ተብሏል።


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page