ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች በፈረሡላ 8,000 እና 9,000 ብር ይገዛ የነበረ ቡና ዋጋ በእጥፍ በመጨመሩ ላኪዎች እየተቸገሩ ነው ተባለ።
- sheger1021fm
- 53 minutes ago
- 1 min read
ህዳር 25 2018
ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች በፈረሡላ 8,000 እና 9,000 ብር ይገዛ የነበረ ቡና ዋጋ በእጥፍ በመጨመሩ ላኪዎች እየተቸገሩ ነው ተባለ።
ላኪዎች በዚህ ዋጋ ቡና እየገዙ ለአለም ገበያ ማቅረብ እንደሚከብዳቸው የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ተናግሯል።
አርሶ አደሮች እና ላኪዎች ዋጋውን ከፍ ያደረጉት ወደፊት ይበልጥ ይጨምራል በሚል ግምት እንደሆነም ማህበሩ ጠቅሷል።
ወደ ውጪ ቡና የሚልኩ ነጋዴዎች ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች ምርቱን የሚገዙበት ዋጋ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ተናግሯል፡፡
የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ግዛት ወርቁ እንዳሉት ቀደም ሲል በፈረሱላ ስምንት ሺህ እና ዘጠኝ ሺህ ብር ከአርሶ አደሮችና አቅራቢዎች ይገዛ የነበረ ቡና አሁን በፈረሱላ እስከ ሃያ ሺህ ብር እየተባለ ነው፡፡
አንድ ፈረሱላ ቡና በሃያ ሺህ ብር ገዝቶ ወደ ለውጪ ገበያ ማቅረብ ለላኪዎች ከባድ ነው ብለዋል፡፡
አርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች ዋጋ እየጨመሩ ያሉት ወደፊት ይበልጥ መሸጫው ከፍ ይላል በሚል ግምት እንደሆነ አቶ ግዛት ተናግረዋል።
አሁን ያለው የአለም አቀፍ ቡና መሸጫ ግን ዋጋው እንደሚጨመር ሳይሆን እንደሚቀንስ የሚያመለክት ነው ብለዋል።
ላኪዎች ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች ቡናን የሚገዘቡት ዋጋ ካልተስተካከለ ምርቱን ለአለም ገበያ ማቅረብ አስቸጋሪ ይሆናል ሲሉ አቶ ግዛት ስጋታቸውን ተናግረዋል።
ቡና ደግሞ ለኢትዮጵያ ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ ምርት በመሆኑ ነገሩ እንደ ቀላል ሊታይ የሚችል አይደለም ሲሉ አክለዋል።
ችግሩን ለመፍታት መንግስት መመሪያ ማውጣት ይችላል ያሉት አቶ ግዛት ለላኪዎች ማበረታቻዎችን ማቅረብም ሌላው አማራጭ እንደሆነ ጥቅሰዋል።
ዋጋው አሁን ባለበት የሚቀጥል ከሆነ ኢትዮጵያ የምታገኘው ገቢ ብቻ ሳይሆን ወደ ውጪ የምትልከው ቡና መጠንም እንደሚቀንስ አቶ ግዛት ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments