የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በሚል ምክንያት ከሲዳማ ክልል ሃገረ ሰላም እስከ ዝዋይ ባቱ ድረስ ባለው መንገድ በርከት ያሉ ማደያዎች ቢኖሩም አንዳቸውም ናፍጣ የላቸውም።
- sheger1021fm
- 5 minutes ago
- 1 min read
ህዳር 29 2018
የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በሚል ምክንያት ከሲዳማ ክልል ሃገረ ሰላም እስከ ዝዋይ ባቱ ድረስ ባለው መንገድ በርከት ያሉ ማደያዎች ቢኖሩም አንዳቸውም ናፍጣ የላቸውም።
በጄሪካን ግን ይሸጣል።
በሲዳማ ክልል ሀገረ ሰላም እስከ ሀዋሳ ከተማ መግቢያ ድረስ፣ ከሃዋሳ እስከ ዝዋይ ባቱ ባሉ ማደያዎች የመኪና ናፍጣ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን ከቦታው ተመልክተናል።
በእዚህ አካባቢ ስንዘዋወር እንደተመለከትነው ማደያዎች ውስጥ ነዳጅ የለም ቢባልም ማደያው አካባቢና ማደያዎች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች በጀሪካን ነዳጅ እንደሚሸጥ ሲናገሩና ሂሳብ ለማስማማት ሲሞክሩም አይተናል።
በሲዳማ ክልል ሀገረ ሰላም ላይ ህዳር 27 ቀን 2018 በነበርንበት ወቅት ማደያዎች ውስጥ ናፍጣ የለም የሚል ተደጋጋሚ ምላሾች ቢሰጡንም እዚያው አካባቢ ያሉ ግለሰቦች ግን ናፍጣ በጀሪካን እነሱ ጋር መኖሩን ሲናገሩ ሰምተናል።

በዚህ መንገድም አዲስ አባበ 121 ብር አካባቢ የሚሸጠው አንድ ሊትር ናፍጣ165 ብር ሂሳብ ሲሸጥ ተመልክተናል።
ዝዋይ ባቱ የሚገኝ አንድ ማደያ ስንጠይቅ ናፍጣ የለም የሚል ምላሽ ከማደያው የተሰጠ ሲሆን ማደያው አጠገብ ያሉ ሱቆች ውስጥ ግን በጀሪካን እንደሚሸጡ ተመልክተናል።
በዚሁ ዕለት ዝዋይ ባቱ አንድ ሊትር ናፍጣ በህገወጥ መንገድ በጀሪካን ከ180 ብር እስከ 200 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን አይተናል።
ይህም እየሆነ ያለው ሰሞኑን የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በሚል ግምት መሆኑን ሰምተናል።
በረከት አካሉ








