top of page

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 100ሚሊዮን ብር ወጪ ያደረገበትንና የቁጥጥር ባለሙያዎቹን የሚከታተልበት ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • 4 hours ago
  • 1 min read

ህዳር 24 2018


የአዲስ አበባገቢዎች ቢሮ 100ሚሊዮን ብር ወጪ ያደረገበትንና የቁጥጥር ባለሙያዎቹን የሚከታተልበት ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናገረ።


ግብር ከፋዮችን ለመከታተል የሚሰማሩ የመስሪያ ቤቱ የቁጥጥር ባለሙያዎችን ካሜራ የተገጠመበት የደምብ ልብስ አልብሶ ማሰማራቱን ቢሮው ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርቶ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።


የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ወደዚህ ስራ የተገባበትን ምክንያት ሲያስረዱ የቁጥጥር ባለሙያዎች ያለ አግባብ ይቀጡናል፤የእጅ መንሻ እንድንሰጥ ይደራደሩናል የሚሉና ሌሎችም ቅሬታዎች ተደጋግመው ከግብር ከፋዩ የሚመጡ በመሆኑ ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ነው ብለዋል።

ree

ባለሙያዎቹ የሚለብሱት ካሜራ የተገጠመበት የደምብ ልብስ በቀጥታ በማዕከል ከተተከለው የቁጥጥር ካሜራ ጋር የተገናኘ ነው የሚሉት አቶ ቢኒያም፤ ባለሙያዎቹ የት እንደተመደቡ፣ከግብር ከፋዩ ጋር የሚያደርጉት ንግግር በድምፅና በምስል በቀጥታ ከማዕከል ክትትል የሚደረግበት መሆኑን አስረድተዋል።


በመሆኑም ከዚህ በኋላ ለቁጥጥር ወደግብር ከፋዩ የሚመጡ ባለሙያዎች በካሜራ እይታ ውስጥ ሆነው የሚሰሩ በመሆኑ ያለ አግባብ ተቀጣሁ፣ ስራዬን እንዳልሰራ አድርገውኛል የሚል ግብር ከፋይ ካለ የተቀረፀው ቪዲዮ እየታየ መልስ የሚሰጥበት አሰራር ይኖራልም ተብሏል።


በሁሉም ቅርንጫፎች ያሉ 800 ያህል የገቢዎች ቢሮ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለዚህ ስራ መሰማራታቸውን ሃላፊው አቶ ቢኒያም ጠቅሰው ለግብር ከፋዩ ቅሬታ እፎይታን የሚሰጥ ነው ያሉት ይህ ቴክኖሎጂ በኢንሳ አማካኝነት የለማ ነው ማለታቸውንም ሰምተናል።


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page