top of page

የአ/አ ት/ት ቢሮ ከት/ቤቶች ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ለወላጆች ቅሬታ ፈጥሯል

  • sheger1021fm
  • 3 hours ago
  • 1 min read

ህዳር 24 2018


የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ለወላጆችና መምህራን ቅሬታ ፈጥሯል፡፡


ቢሮው ከ256 ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 40,000 ተማሪዎች በ54 ማዕከላት በተሻለ የማስተማር ችሎታቸው በተመረጡ መምህራን ከመደበኛው የትምህርት ቀን ወጪ የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠሁ ነው ብሎ ነበር፡፡


እንዲህ ዓይነቱ አሰራር በሌሎች ሀገራትም የተለመደ ቢሆንም ከተማሪ ወላጆችና መምህራን በማጠናከሪያው ላልተካተቱ ተማሪዎችስ ምን ታስቧል? የሚል ጥያቄ አስነስቷል፡፡


የተማሪ ወላጆችና መምህራን ጥሩ ውጤት ላላቸው ተማሪዎች ማጠናከሪያ ከመስጠት፣ በትምህርት አቀባበላቸው ደከም ያሉትን ማበረታታት አይሻልም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡


ትምህርት ቢሮው በበኩሉ የቅዳሜው የማጠናከሪያ ትምህርት ለተመረጡት ተማሪዎች ብቻ ይሰጥ እንጂ ከሰኞ እስከ አርብ ባለው ጊዜ ውስጥ ከመደበኛ የትምህርት ሰዓት ውጪ ለሌሎቹም ትኩረት ተሰጥቷቸው እያጠኑ ነው ብሏል፡፡

ree

የትምህርት ቢሮው ምክትል ስራ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ጥሩ ውጤት ላላቸው ተማሪዎች ማጠናከሪያ ከመስጠት፣ በትምህርት አቀባበላቸው ደከም ያሉትን ማበረታታት አይሻልም ወይ? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ ጎበዝ ተማሪዎችን የመረጥነው በሁለት ምክንያቶች ነው ብለዋል፡፡


አንደኛ በተማሪዎች መካከል ፉክክር ለመፍጠር ሲሆን ሌላው ደግሞ ማጠናከሪያውን የወሰዱ ተማሪዎች ሌሎችን እንዲያስጠኑ ነው ሲሉ ኃላፊው መልሰዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page