top of page

ሕብረት ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከግብር በፊት የ749.04 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • 8 minutes ago
  • 1 min read

ህዳር 29 2018


ሕብረት ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከግብር በፊት የ749.04 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ፡፡


ባንኩ ይህን ያለው 28ኛውን የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው እለት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡


በጉባዔው ላይ የባንኩን ዓመታዊ ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ተሰማ የባንኩ ሀብት 113.93 ቢሊየን ብር መድረሱን ተናግረዋል፡፡


ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ17.96 በመቶ ወይም የ17.35 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል።


የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 92.68 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተጠቅሷል።


ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ18.03 ቢሊዮን ብር ወይም የ24.16 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የቦርድ ሰብሳቢው አስረድተዋል፡፡


ከወለድ ነፃ ፋይናንስን ጨምሮ አጠቃላይ የባንኩ የብድር ክምችት ወደ 79.33 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል፡፡


ሕብረት ባንክ የውጪ ምንዛሪ ግኝት ካለፈው ዓመት የ47.4 በመቶ ወይም የ96.49 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ በማሳየት 300 ሚሊየን ዶላር መድረሱ ተነግሯል፡፡


በበጀት ዓመቱ የባንኩ አጠቃላይ ገቢ ወደ 16.74 ቢሊዮን ብር ማደጉንና ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ26.55 በመቶ ወይም የ3.51 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየቱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።


በነሐሴ ወር 2017 ዓ.ም የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚም ሆነው የተሸሙት አቶ ንጉሱ ገ/እግዚእብሔር የባንኩን አፈፃፀም ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያሳድጉት የቦርድ ሰብሳቢው እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page