top of page

''በሩብ ዓመቱ 3,319 የመድሀኒት እና የክትባት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርቶች ደርሰውኛል'' የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን

  • sheger1021fm
  • Dec 5, 2025
  • 1 min read

ህዳር 26 2018


በሩብ ዓመቱ 3,319 የመድሀኒት እና የክትባት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርቶች ደርሰውኛል ሲል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ፡፡


ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2018 ሩብ ዓመት፣ 723 የመድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርቶችን(ADE) እንዲሁም 2,596 የክትባት የጎንዮሽ ጉዳት ሪፖርቶችን (AEFI) በድምሩ 3,319 ሪፖርቶች እንደሰበሰበ ተናግሯል፡፡


በተጨማሪም 15 አስከፊ የመድኃኒት ወይም የክትባት የጎንዮሽ ክስተት ሪፖርቶችን የማጣራት ስራ ሰርቻለሁም ብሏል፡፡


257 አዳዲስ የህክምና መሳሪያዎች ሰነድ በመገምገም የገበያ ፈቃድ እንደሰጠም ተናግሯል፡፡

ለ13 ህክምና መሳሪያ አስመጪና አከፋፋይ ደግሞ የቅድመ ፈቃድ ኢንስፔክሽን አድርጎ የብቃት ማረጋገጫ እንደተሰጠም አስረድቷል፡፡


የህክም ሙከራ እንድካሄድ የተፈቀደላቸዉን ተቋማት ላይ መልካም የህክምና ሙከራ ቁጥጥር መስራት 4 ታቅዶ 3(75%) የህክምና ሙከራ ቁጥጥር ተሰርቷል ሲል በሪፖርቱ ተናግሯል፡፡


በአጠቃላይ ባለፉት 3 ወራት 313 መድኃኒቶችን የገበያ ፈቃድ መስጠቱን ጠቅሷል፡፡


ለቁጥጥር አሰራር ግብአት ሊሆኑ የሚችሉ 1,178 ጥቆማዎች፣ መረጃዎችንና አስተያየቶች ከህብረተሰቡ ተቀብያለሁ ብሏል፡፡


ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተቀብያለሁ ያላቸውን የመድሀኒት፣ የክትባት የጎንዮሽ ጉዳቶች እና ሌሎች ጥቆማዎች ላይ የተወሰዱ ርምጃዎችን በሪፖርቱ አልጠቀሰም፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page