top of page

ህዳር 25 2018 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሁለት ሚኒስትሮችን እና የአንድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሹመትን አፀደቀ።

  • Dec 4, 2025
  • 1 min read

ሹመታቸው በምክር ቤቱ የፀደቀላቸው የሠላም ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ እድሪስ፤ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቢንያም ኤሮ ናቸው።


አቶ መሃመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተሹመው  ስራ የጀመሩት ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም እንደነበር ይታወሳል።


አቶ አዲሱ አረጋ ደግሞ ሐምሌ 25/ 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብርና ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡


አንድ የምክር ቤቱ አባል በተለይ የሠላም ሚኒስትሩ አቶ መሃመድ እድሪስ ከተሾሙ ዓመት እንዳለፋቸው በመጥቀስ ሹመቱ እስከ አሁን በምክር ቤቱ ሳይጸድቅ መቆየቱ አግባብ ነው ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል።


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ በሰጡት ምላሽ በተለያዩ ምክንያቶች ሹመቱ በምክር ቤቱ ሳይፀድቅ መቆየቱን ተናግረው ማሳሰቢያውን ግን ተቀብለናል ብለዋል።


ምክር ቤቱም የሁለቱን ሚኒስትሮችን እና የስራ አስፈጻሚውን ሹመት በሙሉ ድምጽ አፅድቆታል።


ተሿሚዎቹም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት አማካይነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።


ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

Recent Posts

See All
በፊንቴክ የማጭበርበር ወንጀል ዛሬ በአቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ተወነሰ፡፡

ሚያዝያ 28/2018 በፊንቴክ የማጭበርበር ወንጀል ዛሬ በአቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ተወነሰ፡፡ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በአቃቤ ህግ ዛሬ የመሰረተባቸውን የክስ ዝርዝሩን ያደመጠው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከአምስተኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል በስተቀር

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page