top of page


በአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያዎች ሊደርስ የሚችል የአደጋ ስጋት ሲኖር የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እርምጃ እንዲወስድ የሚፈቀድ ረቂቅ አዋጅ ወደ ቋሚ ኮሚቴ ተመራ፡፡
ጥር 15/2018 በአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያዎች ሊደርስ የሚችል የአደጋ ስጋት ሲኖር የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እርምጃ እንዲወስድ የሚፈቀድ ረቂቅ አዋጅ ወደ ቋሚ ኮሚቴ ተመራ፡፡ በአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያዎች ላይ ከትከሻ የሚተኮስ የአየር መከላከያ መሳሪያ፣ ሰው አልባ አውሮፕላንን ጨምሮ ስጋት ማድረስ የሚችል ማንኛውም ሊቃጣ የሚችል የአደጋ ስጋት ሲኖር የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የመከላከል እርምጃ እንዲወስድ የሚፈቀድ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ነው ለቋሚ ኮሚቴው የተመራው። ፓርላማው ወደ ቋሚ ኮሚቴ የመራው ረቂቅ የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አዋጅ የመንገደኞችን ምዝገባ እና ቅድመ-በረራ መረጃ የመሰብሰብና የማሰራጨት ትግበራን እንዲመራ እና እንዲያስተባባር ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃላፊነት ይሰጣል። የህዝብ እንደራሴዎች
6 days ago2 min read


የሥነ ምድር እና የከርሰ ምድር የውሃ ሀብት ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ጥር 15/2018 የሥነ ምድር እና የከርሰ ምድር የውሃ ሀብት ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ዓለም አቀፍ የሥነ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ሳይንቲስቱ ጤናዓለም አየነው(ፕ/ር) በትናንትናው ዕለት ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተነግሯል። በከርሰ ምድር የውሃ ዘርፍ ላሉ ችግሮች በምርምር መፍትሄን በማቅረብ የኢትዮጵያን ችግር ፈቺ የሆኑ በርካታ ጥናታዊ ምርምሮችን በመስራት በቀዳሚነት ከሚነሱ የዘርፉ ምሁራን አንዱ ናቸው። ፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጂኦሎጂ የትምህርት ዘርፍ አግኝተዋል። በኔዘርላንድስ ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የኤሮ ስፔስ እና የጂኦ ኢንፎርሜሽን ሳይንስ ተቋምም በውሃ ሀብት ጥናት የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። ከአምስተር
6 days ago1 min read


ዳሸን ባንክ ከአንድ ዓመት በፊት ባስጀመረው የሴቶች የአቅም ግንባታ መርሀ ግብር ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት አካሄደ።
ጥር 14/2018 ዳሸን ባንክ ከአንድ ዓመት በፊት ባስጀመረው የሴቶች የአቅም ግንባታ መርሀ ግብር ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት አካሄደ። በተለያዩ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ሴት ሰራተኞቹን አቅም ለማጎልበትና ወደከፍተኛ የአመራር ሃላፊነቶች ለማሳደግ ያለመውና ለአንድ ዓመት ያህል ሲተገበር በቆየው አጠቃላይ የሴቶችን አቅም የማጎልበት መርሃ-ግብር (Comprehensive Women Empowerment Program) ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል። ባንኩ ከአንድ አመት በፊት የሴቶች አቅም ግንባታ መርሃ ግብርን ማስጀመሩ ይታወሳል። በአንድ አመት ጊዜም ከ140 በላይ የሚሆኑ ሴት የባንኩ ባልደረቦች በዚህ መርሃግብር የመሳተፍና በተለያዩ መንገዶች አቅማቸውን የማጎልበት እድል አግኝተዋል ብሏል። በዚህ መርሃ-ግብር በአንድ ዓመት ሶስት የትስስርና ውይ
7 days ago1 min read


መጪው ምርጫ ፍትሃዊ፣ ትክክለኛ እና ተቀባይነት ያለው አንዲሆን የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ኢዜማ ጠየቀ፡፡
ጥር 14/2018 መጪው ምርጫ ፍትሃዊ፣ ትክክለኛ እና ተቀባይነት ያለው አንዲሆን የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ምርጫ ቦርድ እጩ ምዝገባ ውስጥ ለመግባት የሚያስችለውን የሲስተም ፍቃድ ስላልሰጠው እስካሁን የእጩ ታዳደሪዎቹን ማስበዝገብ አለመቻሉብ ተናግሯል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…… የኔነህ ሲሳይ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ….. YouTube : https://url-shortener.me/2DTR Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1 Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY WhatsApp : https://url-shortener.me/2DU0 X : https://x.com/shegerfm?s=2
7 days ago1 min read
ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች ምርቶች እና አገልግሎቶቻቸውን የሚጠቀሙ ሰዎች ጋር ለመድረስ እንደሚቸገሩ ይናገራሉ፡፡
ጥር 14/2018 ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች ምርቶች እና አገልግሎቶቻቸውን የሚጠቀሙ ሰዎች ጋር ለመድረስ እንደሚቸገሩ ይናገራሉ፡፡ ለዚህም ተስማሚ የሽያጭ ቦታ በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት አለመቻል፣ የበጀት እጥረትን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች እንደሚያጋጥሟቸው ይሰማል፡፡ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የሚገጥማቸውን ችግር ያቀላል፣ ምርታቸውንም ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል የተባለን ስራም ቴክና ሶሉሽንስ የተሰኘ ተቋም እየሰራ መሆኑን ነግሮናል፡፡ ተቋሙ ወደ ስራ ከገባ ሶስት አመታትን እያስቆጠረ መሆኑን የተናገረ ሲሆን በስፋት ከቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ ስራዎችን እንደሚከውን ተናግሯል፡፡ በዚህም ቴክና ሶሉሽንስ በስሩ ተወካይ ሀብ የተሰኘ አሰራር ዘርግቷል የተባለ ሲሆን ይህም የጋራ መሸጫ ቦታን በማመቻቸት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የሚያመርቱትን ምርት ለሸማቹ ማቅረብ ላይ በትኩ
7 days ago1 min read


በዩጋንዳ የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የምርጫ ዋነኛ ተፎካካሪ የነበረው ሮበርት ካያጉላኒ ለፖሊስ እጅ እንዲሰጥ ከትናንት አንስቶ የ48 ሰዓታት ጊዜ ተሰጠው፡፡
ጥር 14/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #ዩጋንዳ በዩጋንዳ የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የምርጫ ዋነኛ ተፎካካሪ የነበረው ሮበርት ካያጉላኒ ለፖሊስ እጅ እንዲሰጥ ከትናንት አንስቶ የ48 ሰዓታት ጊዜ ተሰጠው፡፡ ካያጉላኒ ማስጠንቀቂያው የተሰጠው የአገሪቱ የጦር ሰራዊት አዛዥ በሆኑት የፕሬዘዳንቱ ልጅ ጄኔራል ምዑዚ ኬኔሩጋባ እንደሆነ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ ሮበርት ካያጉላኒ አወዛጋቢውን ምርጫ ተከትሎ ራሱን መሸሸጉ እየተናገረ ነው፡፡ የቀድሞው አቀንቃኝ እና በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን የተሰኘው ሮበርት ካያጉላኒ ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ አሸናፊ የተደረጉበት ምርጫ ታላቅ ማጭበርበር የተፈፀመበት ነው ብሏል፡፡ ካያጉላኒ የምርጫው ውጤት እንዲሰረዝ ለማድረግ ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ አልሟገትም ማለቱ ተሰምቷል፡፡ አማራጭ ሰላማዊ የትግል መንገዶችን
7 days ago2 min read


ከቻይና እና ከብራዚል ጋር ፍርደኞች ማስተላለፍ የሚያስችል አዋጅ ፀደቀ፡፡
ጥር 14/2018 ከቻይና እና ከብራዚል ጋር ፍርደኞች ማስተላለፍ የሚያስችል አዋጅ ፀደቀ፡፡ የህዝብ እንደራሴዎች የአዋጁ እንዴት ተፈፃሚ ይሆናል? በሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት ስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ ኢትዮጵያ ከቻይና፣ ከብራዚልና ከደቡብ አፍሪካ መንግስታት ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችንና ፍርደኞችን ለማስተላለፍ ያደረገችው ስምምነትን የተመለከቱ 3 ረቂቅ አዋጆችን አስመልክቶ ከህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረቡለትን የውሳኔ ሃሳቦች መርምሮ ረቂቅ አዋጆች በመመርመር አፅድቋል፡፡ በኢትዮጵያ እና በቻይና መንግስት መካከል የተደረገው የወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር ስምምነት በተመለከተ ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ በንባብ ያቀረቡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገ
7 days ago2 min read


ኢትዮጵያ ከ2 ዓመት በኋላ ለምታዘጋጀው ለኮፕ 32 በጉባኤ ከወዲሁ ምን መስራት አለበት?
ጥር 14/2018 ኢትዮጵያ እስከ አሁን በግዝፈቱ አዘጋጅታው የማታውቀው አይነት ጉባኤ ከ2 ዓመት በኋላ ይጠብቃታል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤ ወይንም ኮፕ 32 በጉባኤውም ከ 80,000 በላይ ሰዎች ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከተማዋ አሁን ላይ ያላት የእንግዳ ማረፊያ፣ ሆቴል፣ ደግሞ 25,000 አንግዳ መያዝ የሚችል ነው፡፡ የእንግዳ ማረፊያው፣ ትራንስፖርቱ፣ ጉብኝቱ የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከወዲሁ ምን መሰራት አለበት? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. በረከት አካሉ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ….. YouTube : https://url-shortener.me/2DTR Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1 Facebook
7 days ago1 min read


‘’በትግራይ ገበያ የኤርትራ ናቅፋ ለግብይት እየዋለ ነው’’ በሚል ለቀረበው ወቀሳ የትግራይ ክልል ንግድ ቢሮ ምላሽ
ጥር 14 2018 ‘’በትግራይ ገበያ ውስጥ አንድ የኤርትራ ናቅፋ በኢትዮጵያ 8 ብር እየተገዛ ነው ለግብይት አገልግሎትም ውሏል’’ እየተባለ ለቀረበው ወቀሳ የትግራይ ክልል ንግድ ቢሮ "ሌላ እየተደረገ ባለበት ወቅት ይህ ቢኖር አያስገርምም፤ ግን መኖሩን አላረጋገጥንም" የሚል ምላሽ ሰጠ፡፡ የትግራይ ክልል ብዝሃነት እና ህዝቦች ግንኙነት ጽህፈት ቤት በበኩሉ ከኤርትራ ጋር ያለው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንጂ የንግድ አይደለም ብሏል፡፡ አዲግራትን ጨምሮ በትግራይ ክልል ለኤርትራ ቅርብ በሆኑ የክልሉ ከተሞች በናቅፋ ግብይት እየተደረገ ነው የሚል መረጃ መዘወዘወር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይህንኑ እየተናሩ ነው፡፡ የዲሞክሪሳዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ የኤርትራ ገንዘብ በክልሉ ግበያ ውስጥ መሰራጨቱን ለግብያት እና ሸቀጥ ልውውጥ መዋሉን ተናግሯል፡
7 days ago2 min read


የብር ኖትን በሃገር ውስጥ ማሳተም ካለው ክብደት አንፃር ወይስ ትኩረት ያለ መስጠት ችግር?
ጥር 13/2018 መንግስት እስከ ዛሬ በውጪ የሚታተመውን የኢትዮጵያ የብር ኖቶች በሃገር ውስጥ የማተም ዕቅድ እንዳለው ተናግሯል። ይህም የብር ኖቶችን በውጪ ሃገራት ለማሳተም ሀገር የምታወጣውን ወጪ ያስቀርላታል ተብሏል። ለመሆኑ የብር ኖቶችን በሃገር ውስጥ ማተም በቢሊዮን ዶላሮች የሚያስወጣውን ወጪ የሚቀንስ ከሆነ እስከ ዛሬስ በውጪ ሃገር ማሳተሙ ለምን ተመራጭ ሆኖ ቆየ? የብር ኖትን በሃገር ውስጥ ማሳተም ካለው ክብደት አንፃር ወይስ ትኩረት ያለ መስጠት ችግር? የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ጥላሁን ግርማ ለዘርፉ ትኩረት ያለመስጠት ችግር ነው የሚል ምላሽ አላቸው። ባለሙያው መንግስታት የራሳቸው ቅድሚያ የሚሰጡአቸው ጉዳዮች ስሏሏቸው እስከ ዛሬም የብር ኖቶችን በሃገር ውስጥ ማሳተም ብዙም ትኩረት ሳይሰጡት ቆይተው ሊሆን ይችላል? የሚል ሙ
Jan 212 min read


አለም አቀፍ ገዥዎች በዋጋ ምክንያት ለኢትዮጵያ ሰሊጥ የሚያሳዩትን ፍላጎት እየቀነሱ ነው ተባለ።
ጥር 13/2018 አለም አቀፍ ገዥዎች በዋጋ ምክንያት ለኢትዮጵያ ሰሊጥ የሚያሳዩትን ፍላጎት እየቀነሱ ነው ተባለ። የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት እና ብራዚል ሰሊጥን ከኢትዮጵያ ባነሰ ዋጋ ለአለም ገበያ እያቀረቡ በመሆናቸው የገዥዎች ፍላጎት ወደ እነሱ እያደላ ስለመሆኑ ተነግሯል። ሰሊጥ ከሀገር ውስጥ አምራቾች የሚገዛበት ዋጋ ከፍ ያለ በመሆኑ በአለም አቀፍ ግብይቱ ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ ተነግሯል። ከአምራቾች ከፍ ባለ ዋጋ የተገዛውን ሰሊጥ ተወዳዳሪ ሆኖ በአለም ገበያ ላይ መሸጥ እንዳልተቻለ ከኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመም ላኪዎች ማህበር ሠምተናል። ብራዚልን የመሰሉ አዳዲስ ሰሊጥ አምራች ሀገራት አጋጣሚውን በሰፊው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ኤዳኦ አብዲ ተናግረዋል። እኛ በሜትሪክ ቶን እስከ 1300 ዶላር የ
Jan 212 min read


ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን ገዛው።
ጥር 13/2018 ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን ገዛው። የግዢና ሽያጭ ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል። ሚድሮክ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን ዘመናዊና ቅንጡ በሆነ መልኩ የማሪዮት ደረጃን (autograph collection by Marriot ) ጠብቆ እንደሚያድሰውና ኢትዮጵያ ለምታዘጋጀው 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እንደሚያደርሰው ተናግሯል። አቶ ጀማል አሕመድ የሆቴሉን አገልግሎት በዘርፉ አለም በደረሰበት ደረጃ በማዘመን ለእንግዶች ምቹና ጥራቱን የጠበቀ የማረፊያ ቦታ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። የዋቤ ሸበሌ ሆቴል የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን የሆቴሉን ታሪክ ጠብቆ በማዘ
Jan 211 min read


ደህንነቱ ያልተጠበ ከ13 ሺህ ኩንታል በላይ የጨው ምርት በክትትል መያዙን የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ።
ጥር 13/2018 ደህንነቱ ያልተጠበ ከ13 ሺህ ኩንታል በላይ የጨው ምርት በክትትል መያዙን የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ። ባለስልጣኑ ይህንን ያለው ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ጋር በትብብር በመሆን በህብረተሰቡ ላይ የጤና ጉዳት የሚያስከትሉ ምርቶችን በተመለከተ የወሰደውን ርምጃ አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ላይ ነው። የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ነጋሸ ስሜ እነዚህ የተያዙ የጨው ምርቶች ለጤና ጎጂ መሆናቸው በላብላቶሪ ተረጋግጧል ብለዋል። የጨው ምርቶቹ በተለይም በአስገዳጅነት ማሟላት ያለባቸውን የአዮዲን መጠን ሳያሟሉ የቀሩ ናቸው ተብሏል። በህጉ መሰረት የጨው ምርት ለገበያ ከመቅረቡ በፊት በተመጠነ አዮዲን መበልፀጉ መረጋገጥ አለበት ተብሏል። አሁን ተያዙ የተባሉ የጨው ምርቶች
Jan 211 min read


በኢትዮጵያ ፈቃድ ያላቸው መገናኛ ብዙኃን 309 ደረሱ ተባለ።
ጥር 13/2018 በኢትዮጵያ ፈቃድ ያላቸው መገናኛ ብዙኃን 309 ደረሱ ተባለ። እነዚህ መገናኛ ብዙሀን ተመዝገበውና ፈቃድ አግኝተው በስራ ያሉ መሆናቸው ተነግፘል። በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በህጋዊ መንገድ ፈቃድና ምዝገባ አግኝተዉ የሚንቀሳቀሱ የብሮድካስት፣ የበይነ መረብ፣ የህትመት እና የዉጭ መገናኛ ብዙኃን መሆናቸውን ሰምተናል። ከ 309 ውስጥ 175 የብሮድካስት፣ 20 የህትመት፣ 35 የዉጭ ሚዲያ ክሮስፖንዳንት፣ 73 የበይነመረብ፣ አምስት የክፍያ ኢንተርኔት ብሮድካስት እና አንድ ነፃ የኢንተርኔት ብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን በባለሥልጣኑ ምዝገባ እና ፈቃድ አግኝተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታውቋል። ከእነዚህም ውስጥ 254ቱ በስርጭት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ 55ቱ ደግሞ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ባለስልጣኑ ተናግሯል። በባለሥልጣኑ ባለፉት ስድስት
Jan 211 min read


ለኢመደበኛ ፍለሰቱ ትልቁ ምክንያት ተደረጎ የተነሳውም ድህነት ነው፡፡
ጥር 12/2018 በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሳይቀር ወጣቶችን ወደ ስደት መርቀው መሸኘታቸው ኢመደበኛ ፍልሰትን ከሚያስፋፉ ምክንያቶች አንዱ ሆኖ ቀጥሏል ሲል የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ እነዚህ አካላት ይህንን የሚያደርጉትም በኢመደበኛ ስደት ወጣቶች የሚደርስባቸው አደጋ እና ስቃይ ካለለመገንዘብ ነው ብሏል፡፡ በየአካባቢው ‘’የእከሌ ልጅ እኮ ያለፈለት እና ለቤተሰቦቹም ኤፍኤስአር(FSR) መኪና የገዛው ስደት ሄዶ ነው’’ በሚሉ እና መሰል ማበረታቻዎች ወጣቶች ለኢመደበኛ ፍልሰት እየተዳረጉ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ይህ የተነገረው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች፣ የአረጋውያን፣ የማህበራዊ ጥበቃ መብቶች፣ ኢመደበኛ ፍልሰትን እና ቤተሰብን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ለሚዲያ
Jan 201 min read
የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡
ጥር 12/2018 የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር "ስራቸውን በአግባቡ አልሰሩም፣ ህግን አላከበሩም ፣ ኦዲት ሪፖርት ለዓመታት አላቀረቡም ፣ጠቅላላ ጉባዔም ወቅቱን ጠብቀው ማካሄድ አልቻሉም"በሚል ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡ የቀድሞ ቦርድ አባላት ስራቸወን በአግባቡ ባለመስራታቸው እና ሪፖርት ባለማቅረባቸው "ይቅርታ" ጠይቀዋል፡፡ ከ600 በላይ ንቁ በስራ ላይ ያሉ ድርጅቶች አባላት ያሉት ማህበሩ ጥቅላላ ጉባዔውን እና የምስረታ 50ኛ ዓመቱን ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ፋካሊቲ የመሰብሰብያ አዳራሽ አካሂዷል፡፡ የተከናወኑ ስራዎችን እና ዓመታዊ ሪፖርት እንዲቀርብ ወደ መድረክ ወጥተው የነበሩት የማህበሩ ፕሬዚዳንት እና የቦርድ አባላት በአግባቡ የተቀናጀ ሪፖርት አ
Jan 203 min read


የወል ትርክት እንዴት መገንባት ይቻል ይሆን?
ጥር 7/2018 በኢትዮጵያ ትርክቶች በዝተው ከአንድነት ይልቅ ልዩነት እየሰፋ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ለኢትዮጵያውያን የጋራ መገለጫ የሆኑ የበዙ ሁነቶች እና ታሪኮች ባለቤት ብንሆንም በተቃራኒ ትርክቶች በዝተው ከአንድነት ይልቅ ልዩነት እየሰፋ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ መንግስትም የፀና ሀገረ መንግስት ለመገንባትም ጭምር የሚያለያዩ ትርክቶችን በጋራ ትርክት መተካት ያስፈልጋል በሚል እየሰራበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለመሆኑ ለዘመናት የዘለቁ የብሔርተኝነት የልዩነት ትርክቶች ለጦርነትና ራሴን ችዬ ሀገር እሆናለሁ እስከማለት በደረሰበት በአሁኑ ወቅት የጋራ ትርክትን መገንባት ይቻላል ወይ? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. ያሬድ እንዳሻው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ….. YouTube :...
Jan 151 min read


ግብርናውን ለማዘመን የገበሬውን ህይወት ለማሻሻል እና የተሻለ ምርታማነት እውን እንዲሆን የምርምር ስራዎች ሲከወኑ ቆይቷል፡፡
ጥር 7/2018 ግብርናውን ለማዘመን የገበሬውን ህይወት ለማሻሻል እና የተሻለ ምርታማነት እውን እንዲሆን የምርምር ስራዎች ሲከወኑ ቆይቷል፡፡ ለተጠቀሰው መሰል ዓላማ ከሰራቸው 400 የምርምር ስራዎች መካከል 20 ከመቶ የሚሆኑት በስራ ላይ ሳይውሉ መቅረታቸውን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ተናግሯል፡፡ 80 ከመቶ ወይም 320 ተቋሙ የሰራቸው የምርምር ስራዎች ደግሞ ለታለመላቸው ዓላማ በስራ ላይ መዋላቸውን ሰምተናል፡፡ ተቋሙ ይህን ያለው የ15 ዓመታት የሰራውን ስራ በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ነው ፡፡ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ(ዶ/ር) ተቋማቸው ላለፉት 15 ዓመታት ከሰራቸው ጥናቶች መካከል 80 የሚሆኑት ወደ ስራ ያልገቡት እንዲጠናላቸው ያዘዙ ተቋማት ጥናቱን ለመተግበር አቅም ስላነሳቸውና
Jan 151 min read


የኒውክሊየር ኃይል ከውሃ፣ ከንፋስና ከፅሐይ የኃይል አማራጮች በተሻለ ለኢትዮጵያ ምን የተለየ ነገር ይዞላት ይመጣ ይሆን?
ጥር 6/2018 ኢትዮጵያ 13 ቢሊየን ዶላር በጀት ይጠይቃል የተባለን የኒውክሊየር ሀይል ማመንጫ ለመገንባት በዝግጅት ላይ ነች፡፡ በውሃ፣ ነፋስና ፀሐይ ላይ ጥገኛ የነበረው የኤሌክትሪክ ሀይል አማራጭ የኒውክሊየር ሀይልንም ይጠቀማል ተብሏል፡፡ የኒውክሊየር ሀይል ግንባታ ለኢትዮጵያ ምን ይዞላት ይመጣል? የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮምሽን ምክትል ኮሚሽነር ኢንጅነር አብዱልቃድር ዑመር የኒውክሊየር ኃይል ከሌሎች የአሌክትሪክ ኃይል አማራጮች በተሻለ በተለዋዋጭ የአየር ሁኔታ እና ሌሎች ተፅዕኖ ውስጥ ሆኖ እንኳን የማይወዥቅ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ ይችላል ይላሉ፡፡ ምክትል ኮሚሽነሩ ውሃ፣ ፀሐይ እና ንፋስ የኃይል አማራጮች የማመንጨት አስተማማኝነታቸው 50 ከመቶ በታች ሲሆን የኒውክለር ግን 92 በመቶ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ይህም ኒውክለርን ከሌሎች የኃይል
Jan 142 min read


በሀገራዊ ምክክር የፖለቲካ ልሒቃን፣ ፖለቲከኞች መሳተፍ አለመሳተፍ በውጤቱ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድን ነው?
ጥር 6/2018 በሀገራዊ ምክክር የፖለቲካ ልሒቃን፣ ፖለቲከኞች መሳተፍ አለመሳተፍ በውጤቱ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድን ነው? የሁለቱን ወገን ሃሳብ ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. ያሬድ እንዳሻው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ….. YouTube : https://url-shortener.me/2DTR Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1 Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY WhatsApp : https://url-shortener.me/2DU0 X : https://x.com/shegerfm?s=2 Website፡ https://www.shegerfm.com/ LinkedIn : https://url-sh
Jan 141 min read


በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የግል አየር መንገዶች ለአውሮፕላኖቻቸው ጥገና በዓመት እስከ 800,000 ዶላር ያወጣሉ ተባለ፡፡
ጥር 6/2018 በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የግል አየር መንገዶች ለአውሮፕላኖቻቸው ጥገና በዓመት እስከ 800,000 ዶላር ያወጣሉ ተባለ፡፡ አየር መንገዶቹን ከዚህ ወጪ፣ የውጭ ሀገር ጉዞና እንግልት ለማዳን ያግዛል የተባለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለኢትዮጵያ አየር ሀይል የአውሮፕላን ጥገና ፈቃድ ተሰጥቶታል፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ የግል አየር መንገዶች በቁጥር አስራ ሁለት መድረሳቸው ተነግሯል። የነዚህ አየር መንገዶች ንብረት የሆኑ መካከለኛና አነስተኛ አውሮፕላኖች ጥገና ሲፈልጉ አገልግሎቱን የሚሰጣቸው እራሱን የቻለ የጥገና ማዕከል በሀገር ውስጥ አልነበረም ተብሏል። በዚህም ምክንያት ለጥገና አገልግሎት ወደ ኬንያና ሌሎችም ሀገሮች ለመጓዝ እንደሚገደዱ ተሰምቷል። ይህም ብዙ ወጪን የሚያስወጣቸው አቅማቸውንም የሚፈታተን መሆኑን ሰምተናል። አሁን ግን
Jan 141 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








