top of page

‘’በትግራይ ገበያ የኤርትራ ናቅፋ ለግብይት እየዋለ ነው’’ በሚል ለቀረበው ወቀሳ የትግራይ ክልል ንግድ ቢሮ ምላሽ

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 2 min read

ጥር 14 2018


‘’በትግራይ ገበያ ውስጥ አንድ የኤርትራ ናቅፋ በኢትዮጵያ 8 ብር እየተገዛ ነው ለግብይት አገልግሎትም ውሏል’’ እየተባለ ለቀረበው ወቀሳ የትግራይ ክልል ንግድ ቢሮ "ሌላ እየተደረገ ባለበት ወቅት ይህ ቢኖር አያስገርምም፤ ግን መኖሩን አላረጋገጥንም" የሚል ምላሽ ሰጠ፡፡


የትግራይ ክልል ብዝሃነት እና ህዝቦች ግንኙነት ጽህፈት ቤት በበኩሉ ከኤርትራ ጋር ያለው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንጂ የንግድ አይደለም ብሏል፡፡


አዲግራትን ጨምሮ በትግራይ ክልል ለኤርትራ ቅርብ በሆኑ የክልሉ ከተሞች በናቅፋ ግብይት እየተደረገ ነው የሚል መረጃ መዘወዘወር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡


የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይህንኑ እየተናሩ ነው፡፡


የዲሞክሪሳዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ የኤርትራ ገንዘብ በክልሉ ግበያ ውስጥ መሰራጨቱን ለግብያት እና ሸቀጥ ልውውጥ መዋሉን ተናግሯል፡፡


አቶ ሃለፎም ነርዐ የሰምረት የፓርቲ ጽህፈት ቤት ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ናቸው፡፡


አቶ ሃለፎም በትግራይ ክልል በተለይ በኤርትራ ድንበር አካባቢዎች ህግወጥ ንግዶች መባባሳቸውን ተናግረው ግብይቱ ደግሞ የሚካሄደው አንድ የኤርትራ ናቅፋ በኢትዮጵያ 8 ብር ሂሳብ መሆኑን ነግረውናል፡፡


ይህም ወደ ትግራይ ክልል የሚገባውን ነዳጅ እና ሸቀጥ ተመልሶ ወደ ኤርትራ እንዲወጣ ማድረጉን አብራርተዋል፡፡


ይህ ህገ ወጥ ተግባርም በትግራይ ያለው የዋጋ ንረትም ከፍተኛ እንዲሆን አድርጓል ሲሉ የዲሞክሪሳዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኮሙኒኬሽን ሃላፊ አስረድተዋል፡፡


የትግራይ ክልል ብዝሃነት እና ህዝቦች ግንኙነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቃላይ አሳፋ ይህ ክስ ብክልሉ ያለውን ህዝብ ችግር ለመሸፍን የሚደረግ ጥረት ነው ሲሉ ክሱን አጣጥለዋል፡፡


አቶ ቃላይ ናቅፋ በትግራይ ገብያ ውስጥ ገብቶ መገበያያ ይሆናል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው ፣ምክንያቱም ህጋዊ ያልሆነ ገንዘብ ገብቶ ህጋዊ መገብያያ የሚሆንበት ምክንያት ስለሌለ ብለዋል፡፡


ናቅፋ ብትግራይ ገበያ ውስጥ አለ የሚል የትኛውም አካል መጥቶ መመልከት ይችላል ሲሉ የትግራይ ክልል ብዝሃነት እና ህዝቦች ግንኙነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቃላይ አሰፋ ተናግረዋል፡፡


አቶ ቃላይ ያለው የህግ ወጥ ገንዘብ ዝውውር ሳይሆን ልክ እንደሌሎች ክልሎች ሁሉ የትግራይ ህዝብም ከጎረቤት የኤርትራ ህዝብ ጋር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ነው ያለው ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡


ይህም ልክ በሁሉም የአገሪቱ ደንበር አካባቢ እንዳለ ህዝብ የሚደረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንጂ የንግድ እና የመንግስት ለመንግስት ግንኙት አይደለም ብለዋል አቶ ቃላይ፡፡


የክልሉ ንግድ እና ዘርፍ መሃበራት ምክርቤት በበኩሉ መረጃውን ሰምተን ለማጣራት ሞክረናል በከተሞችን ተመልክተናል ግን የሚወራው እና እዛ ያለው ሃቅ ፍጹም የተለያየ ነው ብሏል፡፡


የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንትአቶ በሪሁ ሃፍቱ ግብይቱ ያለው የኤርትራ ሰራዊት ለቆ ባልወጣባቸው አካባቢዎች ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡

እንደተባለው በአጎራባች ከተሞች ናቅፍ ለግብይት ውሎ ቢሆን ኖሮ ውጤቱ መቀሌ ላይ ይታይ ነበር የሚልት አቶ በሪሁ ሃፍቱ መሰል እንቅስቃሴዎች እኛንም የሚጎዳ ስለሆነ ብናይ ኖሮ ለራሳችን ስንል አናጋልጥ ነበር ሲሉ አብራርተዋል፡፡


የትግራይ ክልል ንግድ እና ኤክስፖርት ኤጀንሲ በበኩሉ መረጃውን መሰምማቱን ነገር ግን እንዳላጠራ ተናግሯል፡፡


የኤጀንሲው ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተክልሽ ገ/ሒውት ነዳጅን ጨምሮ የኮንትሮባንድ ንግድ አለ የተባለውን ከስ አስተባብለዋል፡፡


ነዳጅ ለክልሉ መንግስት ጉዳይ መፈጸሚያ ራሱ በቂ እየቀረበ ባልሆነበት በዚህ ወቅት ነዳጅ በኮንትሮባድ ይወጣል ማለት ልክ አይደለም ብለዋል፡፡


በአሁኑ ወቅት ለትግራይ ክልል የሚቀርበው ነዳጅ መቀርብ ከሚገባው 7 በመቶው ብቻ ወይንም 850ሺ ሊትር ብቻ ይህን እንዴት ብለን ነው ወደ ጎረቤት ከዚህ ላይ በሽያጭ የምናወጣው ሲሉ ዳይሬክተሩ መልሰዋል፡፡


ለተረጂዎች እርዳታ ማድረሻ ነዳጅ የለንም፣ የመስኖ ስራዎችን በነዳጅ እጥረት ቆመዋል እያልን ባለንበት ወቅት ይህ ክስ መቅረቡ ተገቢ አይደለም ሲሉም አክለዋል፡፡

ናቅፋ በክልሉ ገበያዎች ውስጥ መኖሩን አለመኖሩን የክልሉ ንግድ እና ኤክስፖርት ኤጀንሲ እስካሁን እንዳልተወያየበት የተናገሩት የኤጀንሲው ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተክልሽ ገ/ሒውት ከዚህ በኋላ የምናጣራ ይሆናል፤ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ምንም ቢኖር የሚያስገርም አይደለም ሲሉ መልሰዋል፡፡

ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..


X : https://x.com/shegerfm?s=2

Website፡ https://www.shegerfm.com/

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page