top of page

ዳሸን ባንክ ከአንድ ዓመት በፊት ባስጀመረው የሴቶች የአቅም ግንባታ መርሀ ግብር ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት  አካሄደ።

  • sheger1021fm
  • 15 minutes ago
  • 1 min read

ጥር 14/2018  

 

ዳሸን ባንክ ከአንድ ዓመት በፊት ባስጀመረው የሴቶች የአቅም ግንባታ መርሀ ግብር ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት  አካሄደ።

 

በተለያዩ የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ሴት ሰራተኞቹን አቅም ለማጎልበትና ወደከፍተኛ የአመራር ሃላፊነቶች ለማሳደግ ያለመውና ለአንድ ዓመት ያህል ሲተገበር በቆየው አጠቃላይ የሴቶችን አቅም የማጎልበት መርሃ-ግብር (Comprehensive Women Empowerment Program) ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል።

 

ባንኩ ከአንድ አመት በፊት የሴቶች አቅም ግንባታ መርሃ ግብርን ማስጀመሩ ይታወሳል።

 

በአንድ አመት ጊዜም ከ140 በላይ የሚሆኑ ሴት የባንኩ ባልደረቦች በዚህ መርሃግብር የመሳተፍና በተለያዩ መንገዶች አቅማቸውን የማጎልበት እድል አግኝተዋል ብሏል።

 

በዚህ መርሃ-ግብር በአንድ ዓመት ሶስት የትስስርና ውይይት መድረኮች የተካሄዱ ሲሆን በእያንዳንዱ የውይይት መድረክ ላይ ከ200 በላይ ታዳሚዎች መሳተፋቸውን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ ተናግረዋል።

 

ሴቶች በዚህ መድረክ አማካኝነት የሚያገኟቸው የአመራር ክህሎትና አቅም ግንባታ ስልጠናዎች ለባንኩ ስኬት የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ስለሆነ ይህ አይነቱ መርሀ ግብር ለወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።

 

በአሁኑ ሰዓት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሴቶች በተለያዩ የአመራር እርከኖች እያገለገሉ መሆኑን ያነሱት አቶ አስፋው ዓለሙ በባንኩ ካሉት ከ11 ሺ በላይ ቋሚ ሰራተኞች ከ3300 በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

 

ፋሲካ ሙሉወርቅ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..

 

X : https://x.com/shegerfm?s=2                 

Website፡ https://www.shegerfm.com/                          

Recent Posts

See All
ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች ምርቶች እና አገልግሎቶቻቸውን የሚጠቀሙ ሰዎች ጋር ለመድረስ እንደሚቸገሩ ይናገራሉ፡፡

ጥር 14/2018   ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች ምርቶች እና አገልግሎቶቻቸውን የሚጠቀሙ ሰዎች ጋር ለመድረስ እንደሚቸገሩ ይናገራሉ፡፡   ለዚህም ተስማሚ የሽያጭ ቦታ በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት አለመቻል፣ የበጀት እጥረትን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች እንደሚያጋጥሟቸው ይሰማል፡፡   ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የሚገጥማቸውን ችግር ያቀላል፣ ም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page