በዩጋንዳ የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የምርጫ ዋነኛ ተፎካካሪ የነበረው ሮበርት ካያጉላኒ ለፖሊስ እጅ እንዲሰጥ ከትናንት አንስቶ የ48 ሰዓታት ጊዜ ተሰጠው፡፡
- sheger1021fm
- 1 hour ago
- 2 min read
ጥር 14/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
በዩጋንዳ የፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የምርጫ ዋነኛ ተፎካካሪ የነበረው ሮበርት ካያጉላኒ ለፖሊስ እጅ እንዲሰጥ ከትናንት አንስቶ የ48 ሰዓታት ጊዜ ተሰጠው፡፡
ካያጉላኒ ማስጠንቀቂያው የተሰጠው የአገሪቱ የጦር ሰራዊት አዛዥ በሆኑት የፕሬዘዳንቱ ልጅ ጄኔራል ምዑዚ ኬኔሩጋባ እንደሆነ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡
ሮበርት ካያጉላኒ አወዛጋቢውን ምርጫ ተከትሎ ራሱን መሸሸጉ እየተናገረ ነው፡፡
የቀድሞው አቀንቃኝ እና በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን የተሰኘው ሮበርት ካያጉላኒ ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ አሸናፊ የተደረጉበት ምርጫ ታላቅ ማጭበርበር የተፈፀመበት ነው ብሏል፡፡
ካያጉላኒ የምርጫው ውጤት እንዲሰረዝ ለማድረግ ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ አልሟገትም ማለቱ ተሰምቷል፡፡
አማራጭ ሰላማዊ የትግል መንገዶችን እከተላለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡
የናይጀርያ ጦር በአገሪቱ ሰሜን ምዕራብ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 62 ሰዎችን አስለቀቅኳቸው አለ፡፡
ታጋቾቹን በማስለቀቅ ጥረት 5 የጦር ባልደረቦች እና አንድ ፖሊስ ተሰውተዋል መባሉን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡
ከአጋቾቹም መካከል ሁለቱ መገደላቸው ታውቋል፡፡
ታጋቾቹ በተለቀቁበት ዘመቻ 3 አጋቾች እና በርካታ የጦር መሳሪያ መያዛቸው ተጠቅሷል፡፡
አጋቾቹ ሽፍቶች ናቸው ተብሏል፡፡
በዛምፋራ ግዛት ከሽፍቶች በተጨማሪ የቦኮ ሐራም ፅንፈኛ ቡድን ተፅዕኖ የበረታበት ግዛት እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡
የደቡብ ሱዳኑ የጦር ሀይል አዛዥ ጄኔራል ፓውል ማጆክ በየግዛቱ የተቀሰቀሰውን የትጥቅ አመፅ በሳምንት ጊዜ ፀጥ አድርጉልኝ ሲሉ ለወታደሮቻቸው ትዕዛዝ ሰጡ፡፡
ጄኔራሉ ትዕዛዝ የሰጡት ቦር በሚባል የጦር ግምባር በተገኙበት ወቅት እንደሆነ ሱዳንስ ፖስት ፅፏል፡፡
የደቡብ ሱዳን መንግስት ጦር በተለያዩ ግዛቶች አመፀው ከተነሱ ከSPLM-IO ታጣቂዎች ጋር እየተዋጋ ነው ተብሏል፡፡
እንደ ጆንግሌይ እና ማዕከላዊ ኢኳቶሪያ በተባሉት ግዛቶች ውጊያው እየተፋፋመ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
አማጺያኑ ፓጁት የተባለውን ስፍራ መያዛቸው ተሰምቷል፡፡
ፓጁት ወታደራዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ይነገርለታል፡፡
የSPLM-IO መሪ ሪያክ ማቻር በመንግስት ላይ አመፅ አነሳስተዋል ተብለው ከታሰሩ አመት ሊሆናቸው ነው፡፡
ባለቤታቸውም አንጀሊና ቴኒ ሰሞኑን ከአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው ተባርረዋል፡፡
2ኛው አጠቃላይ ስምምነት ከሽፏል ከሚባል ደረጃ መድረሱ እየተነገረ ነው፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD








