top of page

ለኢመደበኛ ፍለሰቱ ትልቁ ምክንያት ተደረጎ የተነሳውም ድህነት ነው፡፡

  • sheger1021fm
  • 3 minutes ago
  • 1 min read

ጥር 12/2018

 

በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሳይቀር ወጣቶችን ወደ ስደት መርቀው መሸኘታቸው ኢመደበኛ ፍልሰትን ከሚያስፋፉ ምክንያቶች አንዱ ሆኖ ቀጥሏል ሲል የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

 

እነዚህ አካላት ይህንን የሚያደርጉትም በኢመደበኛ ስደት ወጣቶች የሚደርስባቸው አደጋ እና ስቃይ ካለለመገንዘብ ነው ብሏል፡፡

 

በየአካባቢው ‘’የእከሌ ልጅ እኮ ያለፈለት እና ለቤተሰቦቹም ኤፍኤስአር(FSR) መኪና የገዛው  ስደት ሄዶ ነው’’ በሚሉ እና መሰል ማበረታቻዎች ወጣቶች ለኢመደበኛ ፍልሰት እየተዳረጉ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

 

ይህ የተነገረው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች፣ የአረጋውያን፣ የማህበራዊ ጥበቃ መብቶች፣ ኢመደበኛ ፍልሰትን እና ቤተሰብን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ለሚዲያ ባለሞያዎች በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው የግንዛቤ መስጫ መድረክ ላይ ነው።

 

በተለይ አሁን አሁን ህጋዊ የሚመስለው ኢመደበኛ ፍልሰት በረቀቁ የማታለያ ዘዴዎች በመታጀቡ፣ ከፍተኛ ደመወዝ የሚያገኙ ባለሞያዎች ጭምር ስራቸውን ትተው ያላቸውን ሁሉ ከፍለው እንደሚታለሉ ተነግሯል፡፡

 

በኢመደበኛ መልኩ በመፍለስ ላይ እያሉ በአንድ ጊዜ ሰላሳ አርባ ሞተው የሚገኙበት ወቅት መኖሩንም ተጠቅሷል፡፡

 

ለኢመደበኛ ፍለሰቱ ትልቁ ምክንያት ተደረጎ የተነሳውም ድህነት ነው፡፡

 

ከድህነት በተጨማሪም የተሻለ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሚፈልሱትም በተሳሳተ መረጃ የተነሳ ነው እንደሆነ ተነግሯል፡፡

 

ለመሆኑ በየጊዜው እየተደጋገመ አስከፊነቱ የሚወራለት ኢመደበኛ ፍለሰትን ለመቀነስ ምን እየሰራ እንደሆ የተጠየቀው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እስከ ወረዳ እና ቀበሌዎች ድረስ ባሉ መዋቅሮች ግንዛቤ እየሰጠ እንደሆነ አስረድቷል፡፡

 

ባለፉት 3 ዓመታት በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከግማሽ ሚሊዮን በበላይ ኢትዮጵያዊንን ወደ ሀገር እንደተመለሱ ተነግሯል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 ማንያዘዋል ጌታሁን

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..

 

X : https://x.com/shegerfm?s=2                 

Website፡ https://www.shegerfm.com/                          

Recent Posts

See All
የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡

ጥር 12/2018 የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር "ስራቸውን በአግባቡ አልሰሩም፣ ህግን አላከበሩም ፣ ኦዲት ሪፖርት ለዓመታት አላቀረቡም ፣ጠቅላላ ጉባዔም ወቅቱን ጠብቀው ማካሄድ አልቻሉም"በሚል ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡ የቀድሞ ቦርድ አባላት ስራቸወን በአግባቡ ባለመ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page