የሥነ ምድር እና የከርሰ ምድር የውሃ ሀብት ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
- sheger1021fm
- 4 hours ago
- 1 min read
ጥር 15/2018
የሥነ ምድር እና የከርሰ ምድር የውሃ ሀብት ተመራማሪው ፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ዓለም አቀፍ የሥነ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ሳይንቲስቱ ጤናዓለም አየነው(ፕ/ር) በትናንትናው ዕለት ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተነግሯል።
በከርሰ ምድር የውሃ ዘርፍ ላሉ ችግሮች በምርምር መፍትሄን በማቅረብ የኢትዮጵያን ችግር ፈቺ የሆኑ በርካታ ጥናታዊ ምርምሮችን በመስራት በቀዳሚነት ከሚነሱ የዘርፉ ምሁራን አንዱ ናቸው።

ፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጂኦሎጂ የትምህርት ዘርፍ አግኝተዋል።
በኔዘርላንድስ ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የኤሮ ስፔስ እና የጂኦ ኢንፎርሜሽን ሳይንስ ተቋምም በውሃ ሀብት ጥናት የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል።
ከአምስተርዳም ፍሪ ዩኒቨርሲቲ በሀይድሮጂኦሎጂ በዶክትሬት ዲግሪ መመረቃቸውም ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አባል የነበሩት ፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለረጅም ዓመታት በቋሚነት እንዲሁም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተጋባዥነት ሲያስተምሩ ቆይተዋል።

በነጌሌ ቦረና ከተማ ታህሳስ 21 ቀን 1959 ዓ.ም. የተወለዱት ፕሮፌሰር ጤናዓለም የበለስ ኢንጂነሪንግ መስራችና ባለቤትም ናቸው።
በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ያለፈው የፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ከቀኑ 9 ሰዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈፀማል ተብሏል።
ሸገር በታላቁ የሥነ ምድር እና የከርሰ ምድር የውሃ ሀብት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው እና ለስራ አጋሮቻቸው በሙሉ መፅናናትን ይመኛል።
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD












Comments