top of page

ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች ምርቶች እና አገልግሎቶቻቸውን የሚጠቀሙ ሰዎች ጋር ለመድረስ እንደሚቸገሩ ይናገራሉ፡፡

  • sheger1021fm
  • 1 hour ago
  • 1 min read

ጥር 14/2018

 

ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች ምርቶች እና አገልግሎቶቻቸውን የሚጠቀሙ ሰዎች ጋር ለመድረስ እንደሚቸገሩ ይናገራሉ፡፡

 

ለዚህም ተስማሚ የሽያጭ ቦታ በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት አለመቻል፣ የበጀት እጥረትን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች እንደሚያጋጥሟቸው ይሰማል፡፡

 

ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የሚገጥማቸውን ችግር ያቀላል፣ ምርታቸውንም ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል የተባለን ስራም ቴክና ሶሉሽንስ የተሰኘ ተቋም እየሰራ መሆኑን ነግሮናል፡፡

 

ተቋሙ ወደ ስራ ከገባ ሶስት አመታትን እያስቆጠረ መሆኑን የተናገረ ሲሆን በስፋት ከቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ ስራዎችን እንደሚከውን ተናግሯል፡፡

 

በዚህም ቴክና ሶሉሽንስ በስሩ ተወካይ ሀብ የተሰኘ አሰራር ዘርግቷል የተባለ ሲሆን ይህም የጋራ መሸጫ ቦታን በማመቻቸት ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የሚያመርቱትን ምርት ለሸማቹ ማቅረብ ላይ በትኩረት ይሰራል ተብሎለታል፡፡

 

በተለይ ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች ገበያው ላይ በስፋት እንዲገቡ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል የተባለለት ይህ አሰራር በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ምርቶቻቸውን ከማስተዋወቅ ጀምሮ ሌሎች ስራዎች ይሰራላቸዋል ተብሏል፡፡

 

አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያሉ ጥቃቅንና አነስተኛ አምራቾች የተጋነነ ወጭ ሳያወጡ ተወካይ ሀብ ባዘጋጀው የምርት መሞከሪያ ቦታ ላይ ምርቶቻቸውን በማስገባት በቀላሉ ወደ ገበያው እንዲገቡ ያግዛቸዋልም ተብሏል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

 ፋሲካ ሙሉወርቅ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..

 

X : https://x.com/shegerfm?s=2                 

Website፡ https://www.shegerfm.com/                          

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page