top of page

አለም አቀፍ ገዥዎች በዋጋ ምክንያት ለኢትዮጵያ ሰሊጥ የሚያሳዩትን ፍላጎት እየቀነሱ ነው ተባለ።

  • sheger1021fm
  • 55 minutes ago
  • 2 min read

ጥር 13/2018


አለም አቀፍ ገዥዎች በዋጋ ምክንያት ለኢትዮጵያ ሰሊጥ የሚያሳዩትን ፍላጎት እየቀነሱ ነው ተባለ።


የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት እና ብራዚል ሰሊጥን ከኢትዮጵያ ባነሰ ዋጋ ለአለም ገበያ እያቀረቡ በመሆናቸው የገዥዎች ፍላጎት ወደ እነሱ እያደላ ስለመሆኑ ተነግሯል።


ሰሊጥ ከሀገር ውስጥ አምራቾች የሚገዛበት ዋጋ ከፍ ያለ በመሆኑ በአለም አቀፍ ግብይቱ ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ ተነግሯል።


ከአምራቾች ከፍ ባለ ዋጋ የተገዛውን ሰሊጥ ተወዳዳሪ ሆኖ በአለም ገበያ ላይ መሸጥ እንዳልተቻለ ከኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመም ላኪዎች ማህበር ሠምተናል።


ብራዚልን የመሰሉ አዳዲስ ሰሊጥ አምራች ሀገራት አጋጣሚውን በሰፊው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ኤዳኦ አብዲ ተናግረዋል።

እኛ በሜትሪክ ቶን እስከ 1300 ዶላር የምንለውን ሰሊጥ እነሱ ከ950 ዶላር አንስቶ እየሸጡ ነው ብለውናል።


ከዚህ ቀደም ቡና ከአምራቾች የሚገዛበት ዋጋ በተመሳሳይ ከፍ ብሎ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ኤዳኦ በመንግስት ጣልቃ ገብነት ሁኔታዎች መስተካከላቸውን ጠቅሰዋል።

ተመሳሳይ የመንግስት ውሳኔ በሰሊጥ ላይም ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።


አርሶ አደሩ ለተለያዩ ምርቶቹ ተገቢውን ዋጋ እያገኘ አይደለም ፤ ተጠቃሚው በመሃል ያለው ደላላ እና ሌላ ሌላው ነው ሲባል በተደጋጋሚ ይሰማል።


አሁን ሰሊጥ አምራቾች በአጋጣሚ የተሻለ ዋጋ ቢያገኙ መንግስት ጣልቃ ገብቶ የሚሸጡበትን እንዲቀንሱ ያድርግ መባሉ ምን ያህል ፍትሃዊ ይሆናል ስንል አቶ ኤዳኦን ጠይቀናል።


ከሰሊጥ ጋር በተገናኘ የሚነሳው ሌላው ጉዳይ በሚመረትባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር ነው።


በተለይ ሁመራን ከመሰሉ እና በሰሊጥ ከሚታወቁ አካባቢዎች ምርቱ በወቅቱ ለገበያ እንዳይቀርብ የፀጥታ ችግሩ ምክንያት እንደሆነ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲነገር ቆይቷል።


ይሄ የፀጥታ ችግር አሁን ተሻሽሏል ወይ ያልናቸው የማህበሩ ፕሬዝዳንት ተከታዩን መልሰዋል።


በ2017/18 የምርት ዘመን ከ1 ሚሊየን 222 ሺህ ሔክታር መሬት በላይ መሬት በሰሊጥ ሰብል እንደተሸፈነ የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።


እስካለፈው ህዳር ወርም ከግማሽ በላዩ እንደተሰበሰበ መረጃው ጠቅሷል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..


X : https://x.com/shegerfm?s=2

Website፡ https://www.shegerfm.com/

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page