በኢትዮጵያ ፈቃድ ያላቸው መገናኛ ብዙኃን 309 ደረሱ ተባለ።
- sheger1021fm
- 3 hours ago
- 1 min read
ጥር 13/2018
በኢትዮጵያ ፈቃድ ያላቸው መገናኛ ብዙኃን 309 ደረሱ ተባለ።
እነዚህ መገናኛ ብዙሀን ተመዝገበውና ፈቃድ አግኝተው በስራ ያሉ መሆናቸው ተነግፘል።
በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በህጋዊ መንገድ ፈቃድና ምዝገባ አግኝተዉ የሚንቀሳቀሱ የብሮድካስት፣ የበይነ መረብ፣ የህትመት እና የዉጭ መገናኛ ብዙኃን መሆናቸውን ሰምተናል።
ከ 309 ውስጥ 175 የብሮድካስት፣ 20 የህትመት፣ 35 የዉጭ ሚዲያ ክሮስፖንዳንት፣ 73 የበይነመረብ፣ አምስት የክፍያ ኢንተርኔት ብሮድካስት እና አንድ ነፃ የኢንተርኔት ብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን በባለሥልጣኑ ምዝገባ እና ፈቃድ አግኝተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ታውቋል።
ከእነዚህም ውስጥ 254ቱ በስርጭት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ 55ቱ ደግሞ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ባለስልጣኑ ተናግሯል።
በባለሥልጣኑ ባለፉት ስድስት ወራትም ለ39 የመገናኛ ብዙኃን በፍቃድና ክትትል ዘርፍ የፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አገልግሎት ሰጥቷል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
X : https://x.com/shegerfm?s=2
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD












Comments