ደህንነቱ ያልተጠበ ከ13 ሺህ ኩንታል በላይ የጨው ምርት በክትትል መያዙን የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ።
- sheger1021fm
- 3 hours ago
- 1 min read
ጥር 13/2018
ደህንነቱ ያልተጠበ ከ13 ሺህ ኩንታል በላይ የጨው ምርት በክትትል መያዙን የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ተናገረ።
ባለስልጣኑ ይህንን ያለው ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ጋር በትብብር በመሆን በህብረተሰቡ ላይ የጤና ጉዳት የሚያስከትሉ ምርቶችን በተመለከተ የወሰደውን ርምጃ አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ነጋሸ ስሜ እነዚህ የተያዙ የጨው ምርቶች ለጤና ጎጂ መሆናቸው በላብላቶሪ ተረጋግጧል ብለዋል።

የጨው ምርቶቹ በተለይም በአስገዳጅነት ማሟላት ያለባቸውን የአዮዲን መጠን ሳያሟሉ የቀሩ ናቸው ተብሏል።
በህጉ መሰረት የጨው ምርት ለገበያ ከመቅረቡ በፊት በተመጠነ አዮዲን መበልፀጉ መረጋገጥ አለበት ተብሏል።
አሁን ተያዙ የተባሉ የጨው ምርቶች አንዳንዶቹ ከሚገባው መጠን በላይ አንዳንዶቹ ደግሞ ከመጠን ያነሰ የአዮዲን መጠን የተገኘባቸው ናቸው ብሏል ተቋሙ።
ለጤና ጎጂ ሆነው ተገኝተዋል የተባሉት የጨው አምራቾች 3 ሲሆኑ በስምም አፋር፣ አፍዴር ወለላ እና በርዋቅ እንደሚባሉ ይፋ አድርጓል።
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለጤና አስጊ እንደሆነ የጠረጠረው ምርት ካለ በ 8482 ይጠቁመኝ ብሏል።
ማንያዘዋል ጌታሁን












Comments