በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የግል አየር መንገዶች ለአውሮፕላኖቻቸው ጥገና በዓመት እስከ 800,000 ዶላር ያወጣሉ ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- 5 hours ago
- 1 min read
ጥር 6/2018
በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የግል አየር መንገዶች ለአውሮፕላኖቻቸው ጥገና በዓመት እስከ 800,000 ዶላር ያወጣሉ ተባለ፡፡
አየር መንገዶቹን ከዚህ ወጪ፣ የውጭ ሀገር ጉዞና እንግልት ለማዳን ያግዛል የተባለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለኢትዮጵያ አየር ሀይል የአውሮፕላን ጥገና ፈቃድ ተሰጥቶታል፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ የግል አየር መንገዶች በቁጥር አስራ ሁለት መድረሳቸው ተነግሯል።
የነዚህ አየር መንገዶች ንብረት የሆኑ መካከለኛና አነስተኛ አውሮፕላኖች ጥገና ሲፈልጉ አገልግሎቱን የሚሰጣቸው እራሱን የቻለ የጥገና ማዕከል በሀገር ውስጥ አልነበረም ተብሏል።

በዚህም ምክንያት ለጥገና አገልግሎት ወደ ኬንያና ሌሎችም ሀገሮች ለመጓዝ እንደሚገደዱ ተሰምቷል።
ይህም ብዙ ወጪን የሚያስወጣቸው አቅማቸውንም የሚፈታተን መሆኑን ሰምተናል።
አሁን ግን ይህንን በሂደት ሙሉ ለሙሉ የሚያስቀር ስራ መጀመሩ፤ የመጀመሪያው እውቅናም ለአየር ኃይል መሰጠቱ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንንም ስለዚሁ እውቅና ጠይቀናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD












Comments