ግብርናውን ለማዘመን የገበሬውን ህይወት ለማሻሻል እና የተሻለ ምርታማነት እውን እንዲሆን የምርምር ስራዎች ሲከወኑ ቆይቷል፡፡
- Jan 15
- 1 min read
ጥር 7/2018
ግብርናውን ለማዘመን የገበሬውን ህይወት ለማሻሻል እና የተሻለ ምርታማነት እውን እንዲሆን የምርምር ስራዎች ሲከወኑ ቆይቷል፡፡
ለተጠቀሰው መሰል ዓላማ ከሰራቸው 400 የምርምር ስራዎች መካከል 20 ከመቶ የሚሆኑት በስራ ላይ ሳይውሉ መቅረታቸውን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ተናግሯል፡፡
80 ከመቶ ወይም 320 ተቋሙ የሰራቸው የምርምር ስራዎች ደግሞ ለታለመላቸው ዓላማ በስራ ላይ መዋላቸውን ሰምተናል፡፡
ተቋሙ ይህን ያለው የ15 ዓመታት የሰራውን ስራ በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ነው ፡፡
የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ(ዶ/ር) ተቋማቸው ላለፉት 15 ዓመታት ከሰራቸው ጥናቶች መካከል 80 የሚሆኑት ወደ ስራ ያልገቡት እንዲጠናላቸው ያዘዙ ተቋማት ጥናቱን ለመተግበር አቅም ስላነሳቸውና በሌሎችም ምክንያት ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

አሁን የሚሰሩ ማንኛውም የምርምር ስራዎች እንደሚተገበሩ እምነት ካላሳደርን አንሰራም ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከ15 አመት በፊት ሲመሰረት በ25 ዓመት ውስጥ የአገሪቱ ግብርናን መለወጥ (ትራንስፎርም) ማድረግ ዋነኛ ግቡ ነው ለዚህ የሚረዱ መሰረቶች ባለፉት ጊዜያት ተሰርተዋል ብለዋል፡፡
ገበሬው አዲስ ነገር ሲያይ ሊቃወም ይችላል ይህም የሚያደርገው የመጣው አዲስ ስራ ለእሱ ጠቃሚ መሆኑን ማየት ስለሚፈልግ ነው፡፡
ስራው አዋጭ ሆኖ ሲያገኘው ግን ለውጡን ለመቀበል ፍቃደኛ ነው ይላሉ ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ፡፡
ተቋማቸውም ለገቤው አዳዲስ ስራ ይዞ ሲሄድ ኪሳራ ቢመጣ ካሳ እንደሚከፍሉ መተማመኛ በመስጠት ለስራው ፈቃደኛ እንዲሆን እናደርጋለን ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
ግብርና አዋጭ የስራ ዘርፍ ነው የሚሉት የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ ወደ ዘርፉ ለመግባት ግን ድፍረት ይጠይቃል በማለት ተናግረዋል፡፡
ይህን እያደረጉ ያሉ ገበሬዎች አሁን ላይ ውጤታማ እየሆኑ ነው ሌሎች ገበሬዎች ደግሞ እነሱን ለመከተል ሲሰሩ ይታያልም ይላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በግብርና ዘርፍ ላይ በየጊዜው የሚወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ፣ ዘርፉ የሚመራበት ፍኖተ ካርታ ከአጋሮች ጋር በመሆን እንዳሰናዳ ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
X : https://x.com/shegerfm?s=2
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD





Comments