ከቻይና እና ከብራዚል ጋር ፍርደኞች ማስተላለፍ የሚያስችል አዋጅ ፀደቀ፡፡
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 2 min read
ጥር 14/2018
ከቻይና እና ከብራዚል ጋር ፍርደኞች ማስተላለፍ የሚያስችል አዋጅ ፀደቀ፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች የአዋጁ እንዴት ተፈፃሚ ይሆናል? በሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት ስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ ኢትዮጵያ ከቻይና፣ ከብራዚልና ከደቡብ አፍሪካ መንግስታት ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችንና ፍርደኞችን ለማስተላለፍ ያደረገችው ስምምነትን የተመለከቱ 3 ረቂቅ አዋጆችን አስመልክቶ ከህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረቡለትን የውሳኔ ሃሳቦች መርምሮ ረቂቅ አዋጆች በመመርመር አፅድቋል፡፡
በኢትዮጵያ እና በቻይና መንግስት መካከል የተደረገው የወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር ስምምነት በተመለከተ ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ በንባብ ያቀረቡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ፤ ሁለቱ ሃገራት ፍርደኞችን በመለዋወጥ ፍርዳቸውን በየሃገሮቻቸው እንዲጨርሱ ለማድረግ ከቻይና መንግስት ጋር የተደረገው ስምምነት የፍርደኞችን መብት ያከበረ፤ አለም አቀፍ ሂደትን መሰረት ያደረገ ውጤታማ የፍርደኞች ማስተላለፍ እንዲኖር ለማድረግ የሚያግዝ መሆን ጠቅሰዋል፡፡
የሁለቱ ሃገራት የቀደመና ዘለቅ ላለ ጊዜ የቆየው የዲፕሎማሲና የንግድ ግንኙነት ይህንን ስምምነት ለመተግበር እንደሚያግዝና ቀጣዩን የሃገራቱን ግንኑነት እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል ብለዋል፤ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት፡፡
በስምምነቶቹ ላይ ጥያቄ ያነሱት የፓርላማ አባላት በተለይ በኢትዮጵያ በአብዛኛው ወንጀል ፈፅመው የሚገኙት የቻይና ዜጎች በህገ ወጥ የማዕድን ማውጣትና በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መሆኑን ጠቅሰው፤ እነዚህ ከባድ ወንጀሎች የሃገራችንን ኢኮኖሚ የሚጎዱ ናቸው፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎቹን አሳልፎ ለሃገራቸው መንግስት ለመስጠት ስንስማማ መንግስታቸው ቅጣታቸውን እንዲጨርሱ እንደሚያደርግ ምን ያህል እርግጠኞች ነን? ስምምነቱ እኩል ተፈፃሚነት ይኖረዋል ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡
ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት ህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ወ/ሮ እፀገነት በበኩላቸው ስምምነቱ ሁለቱም ሃገራት በፍቃዳቸው ተስማምተው የሚፈጽሙት በመሆኑ አንዱ ሃገር ሌላው ሃገር ላይ ጫና የሚያሳድርገበት ምክንያት እንደሌለ አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም የሰዎችን ሰብዓዊ ክብራቸው ተጠብቆ በሃገራቸው ፍርዳቸውን እንዲጨርሱ እድል የሚሰጥ ስምምነት እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ከተመለከታቸው ጉዳዮች መካከል የሆኑት በኢትዮጵያና በቻይና፣ በብራዚል እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ መንግስታት መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችንና ፍርደኞችን የማስተላለፍ ስምምነትን የተመለከቱትን 3ቱንም አዋጆች በአባላጫ ድምፅ አጽድቋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD












Comments