top of page


''ከማህበረሰቡ ከሚቀርቡለት የተበደልን አቤቱታዎች 35 በመቶዎቹ እኔን የሚመለከቱ አይደሉም'' እምባ ጠባቂ ተቋም
ጥቅምት 26 2018 የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ከማህበረሰቡ ከሚቀርቡለት የተበደልን አቤቱታዎች 35 በመቶዎቹ እኔን የሚመለከቱ አይደሉም አለ፡፡ በህግ የተሰጠኝ ሃላፊነት የግልም ሆነ የመንግስት ድርጅቶች ማህበረሰቡ ላይ የሚፈፅሟቸውን አስተዳደራዊ በደሎች የተመለከቱ አቤቱታዎችን ተቀብሎ በመመርመር የተበዳዮችን እምባ ማበስ ነው የሚለው ተቋሙ፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚቸገርበት ጉዳይ ማህበረሰቡ ወደ እምባ ጠባቂ ተቋም ማምጣት ያለበትን ጉዳይ አለማወቅ እንደሆነ ነግሮናል፡፡ በዚህ ምክንያት አጠቃላይ አቤቱታዎች 35 በመቶዎቹ አይመለከቱንም ብለን የምንመልሳቸው ናቸው ያሉን የተቋሙ ምክትል እምባ ጠባቂ ዶክተር የኔነህ ስመኝ ናቸው፡፡ በህዝብ ምርጫ የተቋቋሙ ምክር ቤቶች በህግ አውጪነታቸው የሚሰጧቸው ውሳኔዎችን፤ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያሉና ውሳኔ
Nov 5, 20251 min read


የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እስካሁን ወደ ማህበረሰቡ ለተቀላቀሉ የቀድሞ ተዋጊዎች ከ7.2 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈሉን ተናግሯል፡፡
ጥቅምት 26 2018 የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እስካሁን ወደ ማህበረሰቡ ለተቀላቀሉ ከ80,000 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች ከ7.2 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈሉን ተናግሯል፡፡ ከባለፈው ዓመት ህዳር ወር ጀምሮ በአጠቃላይ ከ80,000 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች በትግራይ፣ በአፋር፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የታሃድሶ ስልጠና ወስደው ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን የኮሚሽኑ ኮሚኒሽን እና አለም አቀፍ ግንኙት ዳይሬክተር ሃብታሙ መሰለ ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ በዚህም ለእያንዳንዱ የቀድሞ ተዋጊ ከስልጠናው በኋላ ስራ ለመጀመሪያ 90,400 ብር እንደተሰጣቸው ነግረውናል፡፡ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ወደ ስራ ሲገባ 371,971 የቀድሞ ተዋጊዎች አሉ ብሎ ሲሆን እስካሁን 80,000 በላይ የሚሆኑትን ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀል ችሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ 63,000 የሚሆኑ
Nov 5, 20251 min read


ጥቅምት 26 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#እስራኤል የእስራኤሉ የኢነርጂ እና የመሰረተ ልማት ሚኒስትር ኤሊ ኮኸን ወደ ጋዛው ጦርነት መመለሳችን አይቀርም አሉ፡፡ ዔሊ ኮኸን በጋዛ ወደ ጠንካራው ድብደባችን ለመመለስ የምንጠብቀው የሟች ታጋቾችን አስከሬን በሙሉ መረከብ ብቻ ነው ሲሉ ለአገራቸው ቻናል 7 ቴሌቪዥን መናገራቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ባቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች የሰላም እቅድ በጋዛ አልፎ አልፎ ቢጣስም የተኩስ አቁም ስራ ላይ ውሏል፡፡ እቅዱ የተኩስ አቁሙን መዝለቅ የሚከታተል አለም አቀፍ አረጋጊ ሀይል በጋዛ እንዲሰፍር ይጠይቃል፡፡ ዔሊ ኮኸን ግን አለም አቀፍ ሀይል ቢሰፍር እንኳ ሐማስን ትጥቅ ማስፈታቱ አይሆንለትም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የአገራቸው ጦር ግን ወደ ጋዛው ዘመቻ ተመልሶ ሐማስን ትጥቅ ማስፈታቱን በብቃት ማሳካት ይችላ
Nov 5, 20252 min read


ጨው፣ ስኳር፣ ስብ በብዛት የሚገባባቸው በፋብሪካ የተቀነባበሩ፣ የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር ይረዳል የተባለ ህግ እየተሰናዳ ነው፡፡
ጥቅምት 25 2018 ጨው፣ ስኳር፣ ስብ በብዛት የሚገባባቸው በፋብሪካ የተቀነባበሩ፣ የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር ይረዳል የተባለ ህግ እየተሰናዳ ነው፡፡ ገና በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለው ህጉ በፋብሪካ የሚቀነባበሩ ምግቦች በውስጣቸው የያዟቸውን ንጥረ ነገሮችና መጠን በግልፅ እንዲፅፉ፣ ያስገድዳል፡፡ ምርቱን ማስተዋወቅ ይከለክላል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ምህረት ስዩም የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxj
Nov 5, 20251 min read


በአዲስ አበባ በ3 ወራት ውስጥ ከ25,000 በላይ ህፃናት ተወልደው፣ የልደት ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ጥቅምት 26 2018 በአዲስ አበባ በ3ወራት ውስጥ ከ25,000 በላይ ህፃናት ተወልደው፣ የልደት ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በወቅቱ የልደት ምዝገባ ያደረጉ ህጻናት ቁጥር ከ25,000 በላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ ነግረውናል፡፡ ጋብቻ ከ2,500 በላይ፣ ፍቺ 853 ፣ ሞት 1,258 ፣ ጉዲፈቻ ደግሞ 58 በአጠቃላይ 30,500 ኩነቶች ባጋጠሙ በወቅታቸው መመዝገባቸውን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ 3 ወራት በወቅቱ በዘገየና ጊዜ ገደቡ ባለፈ 172,011 ወሳኝ ኩነቶች መመዝገባቸውን ከኤጀንሲው ሰምተናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇�
Nov 5, 20251 min read


ጥቅምት 25 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ኢራን የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አርጋቺ አገሬ ከአሜሪካ ጋር ወደ ኒኩሊየር ነኩ ንግግር ለመመለስ የሚያጣድፉት ጉዳይ የለም አሉ፡፡ አርጋቺ ከአሜሪካ ጋር በእኩልነት ደረጃ ካልሆነ በስተቀር አንዳችም ንግግር ማድረግ እንደማትሻ መናገራቸውን አልጀዚራ ፅፏል፡፡ አሜሪካ ኢራን በጭራሽ ዩራኒየም ማብላላት የለባትም የሚል አቋም አላት፡፡ አዲሱ የአሜሪካ የንግግር ሀሳብም በዚሁ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ነው ይባላል፡፡ ኢራን ደግሞ ይሄን በጭራሽ አልቀበልም ባይ ነች፡፡ ምዕራባዊያኑ ኃያላን ኢራን የኒኩሊየር ቦምብ የመስራት ውጥን አላት ሲሉ ይከሷታል፡፡ ቴሕራን በበኩሏ የኒኩሊዩር መርሐ ግብሬ ለኤሌክትሪክ ማመንጫ እና ለሰላማዊ አገልግሎት የታለመ ነው የሚል መሟገቻ ታቀርባለች፡፡ #ሜክሲኮ ፔሩ ከሜክሲኮ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች፡፡ ፔሩ ዲ
Nov 4, 20252 min read


ኢትዮጵያ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ አቅሟን ለማሳደግ ከፈረንሳይ ተቋም ጋር ውል አሰረች፡፡
ጥቅምት 25 2018 ኢትዮጵያ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ዝርጋታ አቅሟን ለማሳደግ ከፈረንሳይ ተቋም ጋር ውል አሰረች፡፡ የመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ተጠቃሚዎች የሆኑት ኢንዱስትሪዎች መሆኑ የተነገረ ሲሆን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያስተዳድራቸው እና ከሚመራቸው መስመሮች አንዱ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ አቅምን ለማሳደግ የተፈራረመችው ከፈረንሣዩ 'ኤሊክቲሪሲቲ ደ ፍራንስ' (EDF) ጋር መሆኑን ሰምተናል፡፡ በሌላ በኩል አገልግሎቱ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግብዓቶች ከሚያመርት የኬንያ ኩባንያ ጋር ውይይት ማረጉን ተናግሯል፡፡ ተቋሙ ከኩባንያው ጋር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግብዓቶችን በኢትዮጵያ ማምረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየቱን የሰማን ሲሆን
Nov 4, 20251 min read


ለአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት በቂ መሬት እንዲቀርብ ከመንግስት ጋር ውይይት ተጀምሯል ተባለ
ጥቅምት 25 2018 ለአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት በቂ መሬት እንዲቀርብ ከመንግስት ጋር ውይይት ተጀምሯል ተባለ። በዘርፉ መሰማራት የሚፈልጉ ብዙ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ባለሃብቶች እንዳሉም ተነግሯል። የአበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ አሁን ላይ በዓመት በአማካይ ከ500 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ለኢትዮጵያ እንደሚያስገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከሁለት መቶ ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠሩንም የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር ተናግሯል። በ2.45 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ላይ እየተካሄደ ያለ ልማት መሆኑም ተጠቅሷል። በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀሙ መሆናቸውን የሚናገሩት የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ፤ አለም አቀፍ ደረጃዎችን አሟልቶ ለመገኘትም ጥረት እያደ
Nov 4, 20251 min read


''ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የሊዝ ክፍያ ካልፈፀሙ መሬቱን እንዲነጠቁ ህግ ቢያዝም ብዙዎችን እየታገስኩ ነው''
ጥቅምት 25 2018 በአዲስ አበባ የሊዝ ባለ ይዞታዎች ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የሊዝ ክፍያ ካልፈፀሙ መሬቱን እንዲነጠቁ ህግ ቢያዝም ብዙዎችን እየታገስኩ ነው ሲል ተቆጣጣሪ መ/ቤቱ ተናገረ፡፡ የሊዝ ክፍያ ያልከፈሉ ከ10,000 በላይ ነዋሪዎችንም በኦዲት አግኝቻለሁ ብሏል፡፡ በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የከተማዋን መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮን ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ተህቦ ንጉሴ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡...
Nov 4, 20251 min read


ኢትዮጵያ ተጨማሪ ብድር መጠየቋ የሚያስከትለው ጫና የለም ወይ?
ጥቅምት 25 2018 ኢትዮጵያ ከተለያዩ የውጪ አበዳሪዎች የወሰደችው ከፍ ያለ የብድር ጫና እንዳለባት ይነገራል፡፡ ከወሰደቻቸው ብድሮች መካከል የመክፈያ ጊዜያቸው ደርሶ የአንዳንዶቹም አልፎ በሂደት ላይ ያለ ድርድር ላይ መሆኗም ይታወቃል፡፡ እንዲያም ሆኖ ከአይኤምኤፍ (IMF) ተጨማሪ ብድር መጠየቋ የሚያስከትለው ጫና የለም ወይ? ባለሙያ ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ትዕግስት ዘሪሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com
Nov 4, 20251 min read


ጥቅምት 25 2018 - በንጋት ሃይቅ ዙሪያ ምን ለመስራት ታስቧል?
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን ለማድረግ ታስቧል። የውሃ ላይ ተንሳፋፊ ሆቴሎች ፣ የውሃ ስፖርትና ሌላውንም መዝናኛ በዙሪያው መስራት ይቻላል። ብዙ ሀገራት ለዚህ ከግድብ ጋር ለተገናኘ ቱሪዝም (Dam Tourism) እንግዳ አይደሉም። ለነገሩ እንግዳ የሆነችው ኢትዮጵያ መሰል ስራዎችን ለመስራት የሃገራትን ልምድ እያየች ነው ሲሉ በቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ ስለሺ ግርማ ተናግረዋል። ለመሆኑ በንጋት ሃይቅ ዙሪያ ምን ለመስራት ታስቧል? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram..
Nov 4, 20251 min read


በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል የቀጠለው ውጥረት ወደ ዳግም አውዳሚ ጦርነት እንዳያመራ የሰላም ጥረቶች እንዲቀጥሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል
ጥቅምት 25 2018 በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል የቀጠለው ውጥረት ወደ ዳግም አውዳሚ ጦርነት እንዳያመራ ሁሉም ዓይነት የሰላም ጥረቶች እንዲቀጥሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል፡፡ የሰሜን ዕዝ የተጠቃበትን 5ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተሰናዳ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ህወሓት ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ያደረጋቸው “ትንኮሳዎች፣ እምቢ ባይነቶች፣ ስራዎች እና ሴራዎች” ወደ ጦርነት ለመግባት ከበቂ በላይ መሆነቸውን ተናግረው እኛ ምንም ብንታገስ ከተጠቃን ግን መከላከላችን አይቀርም ሲሉ ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እኛ ብቻ ጦርነትን ማስቀረት አንችልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይህን አስመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራ
Nov 4, 20252 min read


በኢትዮጵያ ማንም እየተነሳ ሐውልት እንዳያቆምና እንዳያፈርስ የሚከለክል የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ተጠየቀ፡፡
ጥቅምት 25 2018 በኢትዮጵያ ማንም እየተነሳ ሐውልት እንዳያቆም እና የቆሙትን ማንም ባሻው ሰዓት እንዳያፈርስ የሚከለክል የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ተጠየቀ፡፡ ይህ ጥያቄ የቀረበው ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻህፍት(ወመዘክር) ‘’ስለ አደባባይ ሐውልቶቻችን’’ በሚል ርዕስ በተሰናዳ ሥነ ጥባባዊ ወይይት ላይ ነው፡፡ የውይይቱን መነሻ ጹሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ ሥነ ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዲን ሠዓሊ አገኝሁ አዳነ የዘመን መልክ የሆኑ በሶስት ተከታታይ መንግስታት የተሰሩ የአደባባይ ሐውልቶችን የተመለከተ ዳሰሳ አቅርበዋል፡፡ ዳሰሳው የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባን መሰረት ተደርገው የተሰሩትን ሐውልቶች የተመለከተ ነው፡፡ የአደባባይ ሐውልቶች የዘመኑን መንፈ
Nov 4, 20253 min read


በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን አዋሽ ኢንሹራንስ ተናገረ፡፡
ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን አዋሽ ኢንሹራንስ ተናገረ፡፡ በበጀት ዓመቱ የተገኘው ያልተጣራ ትርፍ ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ27 በመቶ በላይ እድገት አለው ተብሏል፡፡ በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት የኩባንያው የተከፈለ ካፒታል በ38 በመቶ አድጎ 2.65 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የተፈረመ ካፒታሉ ደግሞ 4 ቢሊዮን መሆኑን አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ከላከልን መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡ ኩባንያው በዋነኛ የሥራ ዘርፎች ማለትም በጀነራል ኢንሹራንስ (Non-Life) የ43 በመቶ፣ በሕይወት ዘርፍ ኢንሹራንስ ደግሞ የ48 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ተናግሯል፡፡ እንዲሁም በተካፉል የ124 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ተናግሯል፡፡ በዚህም ተካፉልን ጨምሮ በሁሉም የሥራ ዘርፎች በድምሩ ከ4.53 ቢሊዮን
Nov 3, 20251 min read


የትግራዩን ጦርነት ያስቆመውን ስምምነት የተፈራረሙ ወገኖች ፖለቲካዊ ምክክር እንዲያደርጉ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጠየቀ
ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የትግራዩን ጦርነት ያስቆመውን የሰላም ስምምነት የተፈራረሙ ወገኖች ከመጪው ምርጫ በፊት ፖለቲካዊ ምክክር እንዲያደርጉ በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጠየቀ፡፡ የህብረቱ ልዑክ ከተፈረመ ትላንት 3 ዓመት የሞላውን የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫውም የፕሪቶሪያው የሠላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ እና የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀዬቸው እንዲመለሱ አሳስቧል። ጦርነት መቆሙን እና የተቋረጡ መንግስታዊ አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ መደረጋቸው እንደ በጎ እርምጃ የሚወሰዱ ናቸው ያለው መግለጫው ቀሪ የስምምነቱ ክፍሎችም ተፈጻሚ እንዲሆኑ ጠይቋል። የተጀመረው የትጥቅ ማስፈታት እና ማስረከብ እንዲቀጥል እንዲሁም ታጣቂዎች ሠላማዊ ህይወት የሚመሩበት አሰራር እንዲቀጥል ፍላጎታችን ነው
Nov 3, 20251 min read


በንጋት ሀይቅ እስከ 25,000 ሄክታር መሬት በመስኖ ማልማት ይቻላል ተባለ
ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የህዳሴውን ግድብ ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሀይቅ እስከ 25,000 ሄክታር መሬት በመስኖ ማልማት ይቻላል ተባለ፡፡ የህዳሴውን ግድብ ከኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫነት ጋር ብቻ ተገናኝቶ እንዲነሳ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ይፈልጋሉ ተብሏል። በግድቡ የድርድር ወቅትም ለሀይል ማመንጫ ብቻ የሚል ውልን ኢትዮጵያ እንድትፈርም በተደጋጋሚ ትጠየቅ እንደነበርም ተነግሯል። የህዳሴው ግድብና እሱን ተከትሎ የተፈጠረው ንጋት የሰው ሰራሽ ሃይቅ ግን ለኢትዮጵያ ከሀይል ማመንጫ በላይ የመስኖም፣ የዓሣ ምርትም እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻም ጭምር ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ በጥናት እየለየች በሀይቁ ዙሪያ የመስኖ እርሻን ማስፋፋት እንዳለባት ያነሱት የግድቡ መሪ ተደራዳሪ የነበሩት ስለሺ በቀለ (ዶ.ር) እስከ 25 ሺህ ሄክታር መሬትንም በዙሪያው ማልማት
Nov 3, 20251 min read


ዲጂታል ስርዓት እና ኢትዮጵያ
ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም #ጉዳያችን - ዲጂታል ስርዓት እና ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ስርዓት ለመግባት እየፈጠነች ያለችው ኢትዮጵያ አብራ ልታስብና ጥንቃቄ ልታደርግባቸው የሚገቡ ስጋቶቿስ ምንድን ናቸው? የኤ.አይ.ቲ ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ እና የቴክኖሎጂ ባለሞያው አቶ እስራኤል ብሩክ፤ በጉዳዩ ላይ የሰጡንን ማብራሪያ ያድምጡ… ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X :...
Nov 3, 20251 min read


ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም - ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ማስቆም የሚቻለው እንዴት ነው?
ሰዎች በብሔራቸው በሃይማኖታቸው እየተለዩ ግድያ እንደሚፈፀምባቸው በተለያየ ጊዜ የወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ ሰሞኑንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የሆኑ ሰዎች መገደላቸው የየሀይማኖቱ ተቋማት ባወጡት መግለጫ ጠቅሰዋል፡፡ የሃይማኖት ተቋማቱ መንግስት በህይወት የመኖር መብትን እንዲያስከብር ድርጊቱን የፈፀሙትንም ለህግ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል፡፡ ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ማስቆም የሚቻለው እንዴት ነው? ስንል የሃይማኖት አባቶችን ጠይቀናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ… ያሬድ እንዳሻው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/She
Nov 3, 20251 min read
ጥቅምት 21 2018 - የሴቶችን ሰላም እና ደህንነት ያስጠብቃል የተባለ ድንጋጌ ኢትዮጵያ ከተቀበለች 25 ዓመት ቢሆንም እስካሁን ተግባራዊ ለማድረግ ብሄራዊ የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጅታ አላጠናቀቀችም ተባለ
የሴቶችን ሰላም እና ደህንነት ያስጠብቃል የተባለ ድንጋጌ ኢትዮጵያ ከተቀበለች 25 ዓመት ቢሆንም እስካሁን ተግባራዊ ለማድረግ ብሄራዊ የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጅታ አላጠናቀቀችም ተባለ፡፡ ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች መካከል አንዱ እንደሆነም ተነግሯል፡፡ ይህንን ድንጋጌ ኢትዮጵያ ብሄራዊ የድርጊት መርሃ ግብር አጠናቅቃ ተግባራዊ ብታደርግ ሴቶች በተፈጥሮም ይሁን በሰው ሰራሽ ምክንያት የሚገጥማቸውን ችግር አስቀድሞም ይሁን አደጋው ከደረሰ በኋላ ለመከላከል ይረዳል ተብሏል፡፡ ውሳኔው ወይም አለም አቀፍ ድንጋጌው 13 25 እንደሚባልና ከወጣም 25 ዓመት እንደሆነ ሰምተናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድማጥ… ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.c
Oct 31, 20251 min read


ጥቅምት 21 2018 - በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች ቆመው እውነተኛ እርቅ እና ሰላም እንዲወርድ የንግዱ ማህበረሰብ ጠየቀ፡፡
ነጋዴዎቹ ይህን የጠየቁት ትናንት "የንግድ ሚና ለሰላም ግንባታ'' በሚል ሀሳብ አዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባሰናዳው የፓናል ወይይት ላይ ነው። የውይይቱ ተሳታፊ አደም ካሚል (ረ/ፕ) ኢትዮጵያ የምትታወቅበት የረዥም ጊዜ ታሪኳ ፍትህ እና ሰላም እንደሆነ አስረድተዋል። ያ ባይሆን ኖሮ ነብዩ ሞሀመድ ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ አይልኩም ነበር ይህም የምንኮራበት ታሪክ ነው ሲሉ አስታውሰዋል። ትናንት የፍትህ እና የሰላም ሀገር ከሆነች ዛሬ ምን ተፈጥሮ ነው? ችግሩ ምንድነው? የሚለውን ምሁራን እና የሃይማኖት አባቶች ትኩረት አድርገው በጥናት ሊለዩት ይገባል ብለዋል። ሌላ የውይይቱ ተሳታፊ መሳሪያ አንስተው እየታገሉ ያሉት የእኛው እህት ወንድሞቻችን ናቸው በስልጣን ላይ ያሉትም እንደዛው የእኛው ናቸው እያፋጁን
Oct 31, 20253 min read


ጥቅምት 21 2018 - ኢትየጵያ ያላት የእንስሳት ሀብት ከፍተኛ ቢሆንም ህዝቦቿ ከዘርፉ የሚደርሳቸው የነፍስ ወከፍ ፍጆታ ግን ከዓለም ዝቅተኛ የሚባል ነው ተባለ
ኢትየጵያ ያላት የእንስሳት ሀብት ከፍተኛ ቢሆንም ህዝቦቿ ከዘርፉ የሚደርሳቸው የነፍስ ወከፍ ፍጆታ ግን ከዓለም ዝቅተኛ የሚባል ነው ተባለ፡፡ የእንስሳት በሽታ፣ የገበያ ትስስር ማጣት፣ የመረጃ አለማግኘት ችግር፣ ባህላዊ የእርባታ ዘዴዎች እና ለዘርፉ ሚደረጉ ድጋፎች ማነስ፤ ሀገሪቷ በዘርፉ የሚገባትን ተጠቃሚነት ካሳጧት ምክንያቶች መካከል እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አለማየሁ መኮንን(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ያላት የእንስሳት ሀብት የምግብ ዋስትና ለማስጠበቅ ትልቅ አቅም ያለው ቢሆንም ዘርፉ በሚገባው ልክ ጥቅም ላይ እየዋለ እንዳልሆ ተናግረዋል፡፡ ሀገሪቱ የሚባክነውን የዘርፉ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በተጠቀሱት ችግሮች ላይ በብርቱ መስራት ይጠበቅባታል ተብሏል፡፡ ይህ የተባለው በእንስሳት ሃብት ልማት እና የእንስሳት ተዋ
Oct 31, 20252 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








