ጥቅምት 21 2018 - የሴቶችን ሰላም እና ደህንነት ያስጠብቃል የተባለ ድንጋጌ ኢትዮጵያ ከተቀበለች 25 ዓመት ቢሆንም እስካሁን አላፀደቀችም ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- 6 minutes ago
- 1 min read
የሴቶችን ሰላም እና ደህንነት ያስጠብቃል የተባለ ድንጋጌ ኢትዮጵያ ከተቀበለች 25 ዓመት ቢሆንም እስካሁን አላፀደቀችም ተባለ፡፡
ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች መካከል አንዱ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ይህንን ድንጋጌ ኢትዮጵያ ብታፀድቅ ሴቶች በተፈጥሮም ይሁን በሰው ሰራሽ ምክንያት የሚገጥማቸውን ችግር አስቀድሞም ይሁን አደጋው ከደረሰ በኋላ ለመከላከል ይረዳል ተብሏል፡፡
ውሳኔው ወይም አለም አቀፍ ድንጋጌው 13 25 እንደሚባልና ሃገራት ተቀብለው እንዲያጸድቁት ከተላለፈ 25 ዓመት እንደሆነ ሰምተናል፡፡
በሌሎች የዓለም ሀገራት ማፅደቅ ብቻ ሳይሆን በየአምስት ዓመቱ እየተሻሻለ ተግባራዊ እንደሚደረግ የነገሩን የአፍሪካ ሴቶች ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዩት ውስጥ የምርምር ክፍል ሃላፊና ለእዚሁ ተብሎ በተቋቋመ ኮሚቴ ውስጥ ደግሞ የቴክኒክ ኮሚቴ በመሆን ለሁለት ዓመታት ያገለገሉት አቶ ማንይንገረው ሸንቁጥ ናቸው፡፡
ሌሎች 25 ዓመት ሞላው ብለው ለማክበር ቀናት የሚቆጥሩት ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያ ግን እንዳላፀደቀችው ተናግረዋል፡፡
አሁን ባለው የሰላም እጦት እና ግጭት ለሚቸገሩ ሴቶች እንዲሁም ለሌሎችም ውሳኔ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ኢትዮጵያ እንድታጸድቀው ተጠይቋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድማጥ…
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








