የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እስካሁን ወደ ማህበረሰቡ ለተቀላቀሉ የቀድሞ ተዋጊዎች ከ7.2 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈሉን ተናግሯል፡፡
- sheger1021fm
- 1 hour ago
- 1 min read
ጥቅምት 26 2018
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እስካሁን ወደ ማህበረሰቡ ለተቀላቀሉ ከ80,000 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች ከ7.2 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈሉን ተናግሯል፡፡
ከባለፈው ዓመት ህዳር ወር ጀምሮ በአጠቃላይ ከ80,000 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች በትግራይ፣ በአፋር፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የታሃድሶ ስልጠና ወስደው ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን የኮሚሽኑ ኮሚኒሽን እና አለም አቀፍ ግንኙት ዳይሬክተር ሃብታሙ መሰለ ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ በዚህም ለእያንዳንዱ የቀድሞ ተዋጊ ከስልጠናው በኋላ ስራ ለመጀመሪያ 90,400 ብር እንደተሰጣቸው ነግረውናል፡፡
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ወደ ስራ ሲገባ 371,971 የቀድሞ ተዋጊዎች አሉ ብሎ ሲሆን እስካሁን 80,000 በላይ የሚሆኑትን ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀል ችሏል፡፡
ከዚህ ውስጥ 63,000 የሚሆኑት ከትግራይ ክልል ናቸው የተባለ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ከሶስቱ ክልሎች ናቸው ብለዋል የኮሚሽኑ ኮሚኒኬሽን እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ሃብታሙ መሰለ፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








