top of page

በንጋት ሀይቅ እስከ 25,000 ሄክታር መሬት በመስኖ ማልማት ይቻላል ተባለ

  • sheger1021fm
  • 22 hours ago
  • 1 min read

ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም


የህዳሴውን ግድብ ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሀይቅ እስከ 25,000 ሄክታር መሬት በመስኖ ማልማት ይቻላል ተባለ፡፡


የህዳሴውን ግድብ ከኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫነት ጋር ብቻ ተገናኝቶ እንዲነሳ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ይፈልጋሉ ተብሏል።


በግድቡ የድርድር ወቅትም ለሀይል ማመንጫ ብቻ የሚል ውልን ኢትዮጵያ እንድትፈርም በተደጋጋሚ ትጠየቅ እንደነበርም ተነግሯል።

ree

የህዳሴው ግድብና እሱን ተከትሎ የተፈጠረው ንጋት የሰው ሰራሽ ሃይቅ ግን ለኢትዮጵያ ከሀይል ማመንጫ በላይ የመስኖም፣ የዓሣ ምርትም እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻም ጭምር ነው ተብሏል።


ኢትዮጵያ በጥናት እየለየች በሀይቁ ዙሪያ የመስኖ እርሻን ማስፋፋት እንዳለባት ያነሱት የግድቡ መሪ ተደራዳሪ የነበሩት ስለሺ በቀለ (ዶ.ር) እስከ 25 ሺህ ሄክታር መሬትንም በዙሪያው ማልማት ይቻላል ብለዋል።


ቀጣዩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ትልቁ ፕሮጀክትም መስኖን በሀገር አቀፍ ደረጃ ማስፋፋት መሆን አለበት ተብሏል።


ኢትዮጵያን ይህንን እንድትጠቀምበት ተጠይቋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page