top of page

ጥቅምት 21 2018 - ኢትየጵያ ያላት የእንስሳት ሀብት ከፍተኛ ቢሆንም ህዝቦቿ ከዘርፉ የሚደርሳቸው የነፍስ ወከፍ ፍጆታ ግን ከዓለም ዝቅተኛ የሚባል ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • 3 hours ago
  • 2 min read

ኢትየጵያ ያላት የእንስሳት ሀብት ከፍተኛ ቢሆንም ህዝቦቿ ከዘርፉ የሚደርሳቸው የነፍስ ወከፍ ፍጆታ ግን ከዓለም ዝቅተኛ የሚባል ነው ተባለ፡፡


የእንስሳት በሽታ፣ የገበያ ትስስር ማጣት፣ የመረጃ አለማግኘት ችግር፣ ባህላዊ የእርባታ ዘዴዎች እና ለዘርፉ ሚደረጉ ድጋፎች ማነስ፤ ሀገሪቷ በዘርፉ የሚገባትን ተጠቃሚነት ካሳጧት ምክንያቶች መካከል እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ree

በግብርና ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አለማየሁ መኮንን(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ያላት የእንስሳት ሀብት የምግብ ዋስትና ለማስጠበቅ ትልቅ አቅም ያለው ቢሆንም ዘርፉ በሚገባው ልክ ጥቅም ላይ እየዋለ እንዳልሆ ተናግረዋል፡፡


ሀገሪቱ የሚባክነውን የዘርፉ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም በተጠቀሱት ችግሮች ላይ በብርቱ መስራት ይጠበቅባታል ተብሏል፡፡

ይህ የተባለው በእንስሳት ሃብት ልማት እና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ትኩረት ያደረገ አውደ ርዕይ እና ጉባኤ በተከፈተበት መድረክ ላይ ነው፡፡


አዉደ ርዕዩ በእንስሳት መኖ፣ የዶሮ እርባታ፣ የእንስሳት ጤና፣ በወተት፣ በስጋ እና እንቁላል እንዲሁም በንብ እና በአሳ ሃብት ልማት ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነም ሰምተናል።


በዝግጅቱ ከ14 ሃገራት የተውጣጡ ከ100 በላይ ዓለምዓቀፍ የእንስሳት ሃብት ዘርፍ የሚሰሩ ድርጅቶች አንደሚሳተፉ እና ከ5,000 በላይ የኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ እና አለም አቀፍ ሀገራት ጎብኚዎች ይገኛሉ ሲሉ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡

ree

በሚሊኒየም አዳራሽ ትናንት የተከፈተው የእንስሳት ዘርፍ አውደ ርዕይ እና ጉባኤ እስከ ነገ ጥቅምት 22 ድረስ ለብኝዎች እና ለተሳታፊዎች ክፍት እንደሆነ ተነግሯል።


በኢትዮጵያ የላም ውትተ ምርትን አሁን ካለበት በዓመት 6.9 ቢሊዮን ሊትር ወድ 11,7 ቢሊየን ሊትር፣ የዕንቁላል ምርትን ከ3.2 ቢልየን ወደ 9.1 ቢሊየን እና የዶሮ ስጋ ምርትን ከ90 ሜትሪከ ቶነ ወደ 296,000 ሜትሪክ ቶን እንዲሁም የማር ምርትን ከ 147,000 ወደ 296,000 ሜትሪክ ቶን በ4 ዓመት ውስጥ ለማሳደግ በመንግስት ታቅዶ እየተሰራ ነው መባሉ ሰምተናል።


የእንስሳት ሀብት በአለም ዙሪያ ቢያንስ 1.3 ቢሊዮን ሀዝቦችን ኑሮ እንደሚደግፍ የዓለም ምግብ ድርጅት ዘገባ ያሳያል።


ዘርፉ ባደጉት ሀገራት 40 በመቶ የሚጠጋውን በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ደግሞ 20 በመቶውን የግብርና ምርት እንደሚሸፍን መረጃዎች ያስረዳሉ።


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - በሥራቅ አርሲ ዞን ባለንበት በጥቅምት ወር ብቻ 25 ሰዎች መገደላቸውን፣ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ተናገረ።

በኦሮሚያ ክልል በሥራቅ አርሲ ዞን ባለንበት በጥቅምት ወር ብቻ 25 ሰዎች መገደላቸውን፣ ይህንንም የተመለከተው በከባድና ጥልቅ የኃዘን ስሜት መሆኑን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ተናገረ። ቋሚ ሲኖዶስ በኦሮሚያ  ክልል በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር በጉና፣ በመርቲ፤ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋ

 
 
 
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page