በአዲስ አበባ በ3 ወራት ውስጥ ከ25,000 በላይ ህፃናት ተወልደው፣ የልደት ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡
- sheger1021fm
- 53 minutes ago
- 1 min read
ጥቅምት 26 2018
በአዲስ አበባ በ3ወራት ውስጥ ከ25,000 በላይ ህፃናት ተወልደው፣ የልደት ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በወቅቱ የልደት ምዝገባ ያደረጉ ህጻናት ቁጥር ከ25,000 በላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥጋቡ ሹመይ ነግረውናል፡፡
ጋብቻ ከ2,500 በላይ፣ ፍቺ 853 ፣ ሞት 1,258 ፣ ጉዲፈቻ ደግሞ 58 በአጠቃላይ 30,500 አምስት መቶ ኩነቶች ባጋጠሙ በወቅታቸው መመዝገባቸውን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡
በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ 3 ወራት በወቅቱ በዘገየና ጊዜ ገደቡ ባለፈ 172,011 ወሳኝ ኩነቶች መመዝገባቸውን ከኤጀንሲው ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








