የትግራዩን ጦርነት ያስቆመውን ስምምነት የተፈራረሙ ወገኖች ፖለቲካዊ ምክክር እንዲያደርጉ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጠየቀ
- sheger1021fm
 - 1 day ago
 - 1 min read
 
ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም
የትግራዩን ጦርነት ያስቆመውን የሰላም ስምምነት የተፈራረሙ ወገኖች ከመጪው ምርጫ በፊት ፖለቲካዊ ምክክር እንዲያደርጉ በኢትዮጵያ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጠየቀ፡፡
የህብረቱ ልዑክ ከተፈረመ ትላንት 3 ዓመት የሞላውን የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫውም የፕሪቶሪያው የሠላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ እና የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀዬቸው እንዲመለሱ አሳስቧል።
ጦርነት መቆሙን እና የተቋረጡ መንግስታዊ አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ መደረጋቸው እንደ በጎ እርምጃ የሚወሰዱ ናቸው ያለው መግለጫው ቀሪ የስምምነቱ ክፍሎችም ተፈጻሚ እንዲሆኑ ጠይቋል።
የተጀመረው የትጥቅ ማስፈታት እና ማስረከብ እንዲቀጥል እንዲሁም ታጣቂዎች ሠላማዊ ህይወት የሚመሩበት አሰራር እንዲቀጥል ፍላጎታችን ነው ብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments