top of page

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን አዋሽ ኢንሹራንስ ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Nov 3, 2025
  • 1 min read

ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም


በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን አዋሽ ኢንሹራንስ ተናገረ፡፡


በበጀት ዓመቱ የተገኘው ያልተጣራ ትርፍ ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ27 በመቶ በላይ እድገት አለው ተብሏል፡፡


በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት የኩባንያው የተከፈለ ካፒታል በ38 በመቶ አድጎ 2.65 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የተፈረመ ካፒታሉ ደግሞ 4 ቢሊዮን መሆኑን አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ከላከልን መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡

ኩባንያው በዋነኛ የሥራ ዘርፎች ማለትም በጀነራል ኢንሹራንስ (Non-Life) የ43 በመቶ፣ በሕይወት ዘርፍ ኢንሹራንስ ደግሞ የ48 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ተናግሯል፡፡


እንዲሁም በተካፉል የ124 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ተናግሯል፡፡


በዚህም ተካፉልን ጨምሮ በሁሉም የሥራ ዘርፎች በድምሩ ከ4.53 ቢሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ ገቢ መሰብሰብ ችያለሁ ብሏል፡፡

የኩባንያው የቅርንጫፍና የአገናኝ ቢሮዎች ብዛት በዓመቱ መጨረሻ 71 ደርሷል፡፡


የሽያጭ ወኪሎችን ብዛት ደግሞ ከ300 በላይ በማድረስ ከ100.000 በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች የመድን አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ብሏል አዋሽ ኢንሹራንስ፡፡


በተጨማሪም በግብርናው ዘርፍ ከተፈጥሮ አደጋ እና ከአየር ንብረት መዛባት ጋር ተያይዞ የሚፈጠርን አደጋ በተመለከተ የሰብል መድን አገልግሎት በዘንድሮው ዓመት መስጠት መጀመሩንም በመግለጫው ተናግሯል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page