top of page


የኤስኦኤስ የህፃናት መንደር (SOS Children's Villages)
ህዳር 16 2018 ለተለያየ ችግር የተጋለጡ ህፃናትን በምፈልገው ልክ እንዳላግዝ በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶች እንቅፋት ሆነውብኛል ሲል በህፃናት ጥበቃ እና ልማት ዙሪያ የሚሰራው ኤስኦኤስ የህፃናት መንደር የተሰኘ ጅርጅት ተናገረ። ግብረሰናይ ድርጅቱ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ስራዎቼን አንዴ እየጀመርኩ አንዴ እያቋረጥኩ ለመስራት ተገድጃለሁም ብሏል። ይህንን የነገሩን የኤስኦኤስ የህፃናት መንደር (SOS Children's Villages) የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ዳይሬክተር ሳህለማርያም አበበ ናቸው። ከአፋር፣ ከቤኒሻንጉልጉመዝ እና ከጋምቤል ክልሎች ውጪ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ላይ እየሰራን ነው ሲሉ አቶ ሳሀለማርያም ተናግዋል፡፡ በተለይ ግጭት በተደጋጋሚ በሚጎበኛቸው ትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ህፃ
Nov 25, 20251 min read


የልብ ህመም ለገጠማቸውና ወረፋ ለሚጠባበቁ ህፃናት ከእንግሊዝ በመጡ ባለሙያዎች ህክምና እየተሰጠ ነው ተባለ፡፡
ህዳር 16 2018 በልብ በር መጥበብ እንዲሁም በኢንፌክሽን ምክንያት የልብ ህመም ለገጠማቸውና ወረፋ ለሚጠባበቁ ህፃናት ከእንግሊዝ በመጡ ባለሙያዎች ህክምና እየተሰጠ ነው ተባለ፡፡ በኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ውስጥ ካሉ አብዛኛዎቹ በዚህ ችግር ምክንያት የመጡ ህፃናት መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ህክምናው ልብ ሳይከፈት በደምስር የሚሰጥ የልብ ህክምና አይነት መሆኑን የነገሩን የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ዳዊት እሸቱ ከህክምና ስራው ባለፈ ለማዕከሉ የሚያስፈልጉ አላቂ የህክምና ዕቃዎች ድጋፍ ይገኝበታል ብለዋል፡፡ በዚህ ዙር ከ18-20 ህፃናት ህክምናው እንደሚሰራላቸውም ተናግረዋል፡፡ በማዕከሉ አሁንም ድረስ ወረፋ የሚጠባበቁ 8 000 ያህል ህፃናት መኖራቸውን የሚናገሩት ዶክተር ዳዊ
Nov 25, 20251 min read


በጥልቀት ማድመጥን ለተሻለ ተግባቦት እንዴት እንጠቀምበት በሚለው ጉዳይ ላይ እየሰራበት መሆኑን ብሪትሽ ካውንስል ተናገረ፡፡
ህዳር 16 2018 ሰዎችን ይበልጥ የምንረዳበት መላ የሆነውን በጥልቀት ማድመጥን ለተሻለ ተግባቦት እንዴት እንጠቀምበት በሚለው ጉዳይ ላይ እየሰራበት መሆኑን ብሪትሽ ካውንስል ተናገረ፡፡ በእንግሊዝ መንግስት የሚደገፈውና በሃገራት መካከል ግንኙነቶችን ለማጠናከር እንዲሁም ለወጣቶች የተለያዩ እድሎችን በመፍጠር እየሰራ እንደሆነ የሚናገረው ብሪትሽ ካውንስል፤ ዩዝ ኮኔክት በተባለው ፕሮግራሙ ወጣቶች ክልሎቶቻቸውን እንዲያሳድጉ ይሰራል ያሉን የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተርና የፕሮግራም ሃላፊ የሆኑት መፅናናት ሳህለ ናቸው፡፡ ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ ከ70 በላይ ወጣቶችን በጥልቀት መደማመጥና መግባባት ላይ በማሰልጠን እነርሱ ሌሎችን እንዲያሰለጥኑ ለማድረግ እየሰሩ ስለመሆኑም ነግረውናል፡፡ ስለምን ይህንን ጉዳይ መረጣችሁት ያልናቸው ወ/ሮ መጽናናት ከቅር
Nov 25, 20251 min read


ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ተወዳደሪ ለመሆን የጉምሩክ አሰራሯን ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚጠበቅባት ጥናት አመላከተ፡፡
ህዳር 16 2018 ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ተወዳደሪ ለመሆን የጉምሩክ አሰራሯን ቀላል እና ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚጠበቅባት ጥናት አመላከተ፡፡ ጥናቱን ያስጠናው የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ሲሆን፤ ጥናቱን ለማጠናቀቅ 4 ወራት ፈጅቷል ተብሏል፡፡ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና 1.4 ቢሊዮን ሰዎችን እና ወደ 3 ትሪሊዮን ዶላር ዓመታዊ ጥቅል ምርት የሚይዝ መሆኑ በጥናቱ ተካቷል፡፡ በጥናቱ መሰረት የኢትዮጵያ የጉምሩክ አሰራር ውስብሰብ እና ቅልጣፍና የሚጎለው ነው፡፡ ይህም አገሪቱ ተወዳዳሪ እንዳትሆን የሚደርግ ነው ፡፡ ኢትዮጵያ ከ6 ዓመታት በፊት ባፀደቀቸው በዚህ ነፃ የንግድ ስምምነት ተጠቃሚ እና ተወዳዳሪ ለመሆን የህግ ማዕቀፎቿን ፣ የተቋማት ቅንጅት፤ የጉምሩክ ህጎቿን እና የመሰረተ ልማት ክፍተቷን ማስተካካል ይጠበቅባታል ተብሏል፡፡ ሀገሪቱ የንግድ ቀ
Nov 25, 20251 min read


ህዳር 16 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ቻይና የቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ጂን ፒንግ ታይዋን ከእናት አገሯ ጋር መቀላቀሏ በአሁኑ ወቅት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው አሉ፡፡ ሺ ጂን ፒንግ ስለዚሁ ጉዳይ በስልክ ለአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ እንደነገሯቸው የቻይና መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ማውራታቸው አናዶሉ ፅፏል፡፡ ታይዋን ራሴን የቻልኩ ነፃ አገር ነኝ ብትልም ቻይና ግን ታይዋንን እንዳፈነገጠች የገዛ ግዛቷ አድርጋ ትቆጥራታለች፡፡ የቻይና መንግስት እና አድራጊ ፈጣሪው የቻይና ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር ቀደም ሲል ታይዋን በዚያም ሆነ በዚህ መልሳ የቻይና አካል መሆኗ አይቀርም ሲሉ ቆይተዋል፡፡ በአዲሱ የቻይና ፕሬዘዳንት የታይዋን አቋም የአሜሪካ ይፋዊ አስተያየት ምን እንደሆነ አልተሰማም፡፡ ቻይና ቀደም ሲል በታይዋን ዙሪያ ገባ ታላላቅ የጦር ልምምዶችን ማድረጓን መረጃው አስታውሷል፡፡ #አ
Nov 25, 20251 min read


ስታንዳርድ ኢንሹራንስ አ.ማ፤ በኢትዮጵያ 19ኛው የመድህን ሰጪ በመሆን ከቀናት በኋላ ገበያውን ይቀላቀላል ተባለ።
ህዳር 16 2018 ስታንዳርድ ኢንሹራንስ አ.ማ፤ በኢትዮጵያ 19ኛው የመድህን ሰጪ በመሆን ከቀናት በኋላ ገበያውን ይቀላቀላል ተባለ። ኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ሽፋን ካላደገባቸው እና በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ድርሻም ዝቅተኛ ከሆነባቸው ከቀዳሚ ሀገሮች ውስጥ መሆኗ ይነገራል። ''በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ሽፋን ገና ያልደረሰባቸው ብዙ የስራ ዘርፎች አሉ'' ሲሉ የስታንዳርድ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና ሰራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን አሰፋ ነግረውናል። ከ305 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ ከብሔራዊ ባንክ እውቅና በማግኘት 19ኛው የኢንሹራንስ ሰጪ ኩባንያ በመሆን ስራ የሚጀምረው ስታንዳርድ ኢንሹራንስ፤ የአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር 1747 አባላት የመሰረቱት መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ነግረውናል። የኢንሹራንስ ተቋሙ ትልቁ ባለድርሻም አዋጭ የ
Nov 25, 20251 min read


ህዳር 15 2018''ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን ሀገር እንድትሆ የነበራትን ድርሻ ሀገሪቱን በማረጋገቱ ላይም ለራሷ ስትል ሀላፊነቷን ልትወጣ ይገባል'' ሲሉ በህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ተናገሩ፡፡
የአሜሪካ የተራዕዶ ድርጅት USAID የድጋፍ ፖሊሲውን መቀየሩ የኢትዮጵያን የስደተኛ ምላሽ ፈተና ውስጥ ከትቶታል ተብሏል፡፡ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነጋዎ(ዶ/ር) ይህን የተናገሩት የስደተኞች እና ስደት ተመላሾች አገልግሎት ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር የ3 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ለውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው። የተቋሙን ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በ27 መጠለያ ጣቢያዎች ወስጥ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች መኖራቸውን ተናግረዋል። 95 ከመቶ ወይም ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉት ስደተኞች ከጎረቤት ሀገራት የተሰደዱ መሆናቸውን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተ፤ ከ41 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከደቡብ ሱዳን፣ 33 በመቶ ከሶማሊያ፣ 17 ከመቶ ከኤርትራ እና ከሌ
Nov 25, 20252 min read


ህዳር 15 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ናይጄርያ ከናይጄርያዋ ኒጀር ግዛት የአንድ የካቶሊክ ትምህርት ቤት ከታገቱት ከ300 በላይ ተማሪዎች መካከል ሃምሳው ከአጋቶቻቸው ማምለጣቸው ተሰምቷል፡፡ ጉዳዩን የሚከታተለው ቡድን 50ው ተማሪዎች ከአጋቾቻቸው ማምለጣቸውን አረጋግጫለሁ ማለቱን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ይሁንና በምን ሁኔታ እና ከየት እንዳመለጡ አላብራራም፡፡ አምላጮቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል ማለቱ ተሰምቷል፡፡ የናይጀሪያ የፀጥታ ሀይሎች ታጋቾቹን ለማስለቀቅ በተቀናጀ አሰሳ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያም በኬቢ ግዛት ከሚገኝ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት 20 ተማሪዎች ታግተው መወሰዳቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡ እገታውን በመስጋት ብዙዎቹ የናይጀሪያ ግዛቶች ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ማድረጋቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ #ሳውዲ_አረቢያ ሳውዲ አረቢያ በ1
Nov 24, 20252 min read


የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት ለጎረቤት አገራት እና በቅርብ ርቀት ላለው የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ
ህዳር 15 2018 የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት ለጎረቤት አገራት እና በቅርብ ርቀት ላለው የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ቅርብ መሆን እንዳለበት ይነሳል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጣ ለውጥ ቢኖርም አሁንም መሻሻል ያለበት ብዙ ነው ይላሉ በዚህ ዙሪያ ያነጋገርናቸው ዲፕሎማት፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2
Nov 24, 20251 min read


ደረጃቸውን ያልጠበቁ የኤሌክትሪክ መኪኖች ለገበያ እየቀረቡ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ
ህዳር 15 2018 መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ወደ ሀገር እንዳይገቡ መከልከሉን ተከትሎ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥራቸው በርክቷል፡፡ በሌላ በኩል ግን ደረጃቸውን ያልጠበቁ የኤሌክትሪክ መኪኖች ለገበያ እየቀረቡ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በበኩሉ ከጉምሩክ ፍተሻ አምልጠው የሚገቡ ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቅሶ እናስተካክላለን የሚል ምላሽ ሰጥቶናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ንጋት መኮንን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡..
Nov 24, 20251 min read


ኢትዮጵያዊያን ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት ለስራ ከሄዱ በኋላ ለሚያጋጥሟቸው የጤና እክሎች ተከታትሎ መፍትሄ የሚሰጥ አሰራር የለም ተባለ፡፡
ህዳር 15 2018 ኢትዮጵያዊያን ወደ ተለያዩ የአረብ ሀገራት ለስራ ከሄዱ በኋላ ለሚያጋጥሟቸው የጤና እክሎች ተከታትሎ መፍትሄ የሚሰጥ አሰራር የለም ተባለ፡፡ ይንን ችግርም ለመፍታ ይረዳል የተባለ እና የሀገር ውስጥ እና የአለም አቀፍ ተቋማት በጋራ የሚሰሩበት ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን ሰምተናል። ፕሮጀክቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ እና ሌሎችም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ይሳተፉበታል ተብሏል። ከዚህ ቀደም ሴቶች ለቤት ሰራተኝነት ወደ አረብ ሀገራት ሲሄዱ አንዴ ብቻ ተመርምረው እንደሚሄዱ እና በስራ ወቅት የጤና ችግር ቢገጥማቸው እንኳን ቋሚ ክትትል የሚያደርግ አሰራር እንዳልነበረ ሲነገር ሰምተናል፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያውያኑ ለተለያ የጤና ቀ
Nov 24, 20251 min read


ከ200,000 ለሚልቁ ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ መስክ
ህዳር 15 2018 ከፍተኛ ሊባል የሚችል ቁጥር ያላቸው ሴቶች በኢትዮጵያ የአበባ እርሻ ልማት የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል። የዘርፉ ስኬቶች ከሚባሉ ጉዳዮች አንዱም ይኸው የስራ ዕድል ፈጠራ ነው። እንዲያም ሆኖ የሚሰሙ አንዳንድ ቅሬታዎች አሉ ። ለተመሳሳይ ስራ እኩል ክፍያ ያለማግኘት መብት አለመከበር እና የኬሚካል አጠቃቀም ችግር ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ የአበባ እርሻ ልማት ከተጀመረ ሃያ ዓመታት አልፈዋል። በእነዚህ ጊዜያት ዘርፉ ቀላል የማይባል ዕድገት ማሳየቱን መንግስት እና በስራው የተሰማሩ ባለሃብቶች ይናገራሉ። ልማቱ ሲጀመር ከ28.5 ሚሊየን ዶላር የማይበልጠው የዘርፉ የአመት ገቢ አሁን ላይ ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ መሆኑ እንደ ማሳያ ይቀርባል። ከ200,000 ለሚልቁ ሰዎች የስራ ዕድል የፈጠረ መስክ መሆኑም እንዲሁ ይነሳል።
Nov 24, 20252 min read


ኢትዮጵያ የአርብቶ አደሮችን ድንበር ተሻጋሪ ችግሮች ለመፍታት ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተባብራ እንደምትሰራ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ(ዶ/ር) ተናገሩ።
ህዳር 13 2018 ኢትዮጵያ የአርብቶ አደሮችን ድንበር ተሻጋሪ ችግሮች ለመፍታት ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተባብራ እንደምትሰራ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ(ዶ/ር) ተናገሩ። በአካባቢው ሀገራት የሚገኙ አርብቶ አደሮች ወቅቶችን በመከተል ከቤት እንስሳቶቻቸው ጋር ድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታው አስታውሰዋል። በዚህ እንቅስቃሴያቸውም ከግጦሽ መሬት እና ውሃ ጋር የተገናኙ ችግሮች ይገጥሟቸዋል ብለዋል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ኢትዮጵያ ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተቀራርባ እንደምትሰራ ተናግረዋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD) ትኩረቱን በአካባቢው ሀገራት በሚገኙ አርብቶ አደሮች ላይ ያደረገ ውይይት እዚህ በአዲስ አበባ አካሂዷል። በውይይቱም በአካባቢው አርብቶ አደሮች መካከል ኢኮ
Nov 22, 20251 min read


አሐዱ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ተናገረ።
ህዳር 13 2018 አሐዱ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ተናገረ። ባንኩ በበጀት ዓመቱ በበዙ የባንክ ስኬት መለኪያዎች ይበል የሚያስብል ውጤት ማስመዝገቡን በዛሬው ዕለት ባካሄደው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናግሯል። ይህ ውጤት የተመዘገበውም በበዙ ችግሮች ውስጥ አልፎ መሆኑንም ጠቅሷል። የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ በበጀት ዓመቱ 7.88 ቢሊዮን ብር ደርሷል፤ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ41 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል። በሂሳብ ዓመቱ ከ88.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰቡንም #አሐዱ_ባንክ ጠቅሷል። ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ10.3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከ2.16 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ ከቀ
Nov 22, 20251 min read


የተለያዩ እና ብዙም ያልተለመዱ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዤ መጥቻለሁ ሲል ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ተናገረ።
ህዳር 12 2018 የተለያዩ እና ብዙም ያልተለመዱ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዤ መጥቻለሁ ሲል ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ተናገረ። ማህበሩ በዛሬ ዕለትም በይፋ ስራ መጀመሩን በሰጠው መግለጫ አስረድቷል። ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ለሚዲያ እና ኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተለይ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበት አማራጭ መያዙንም አስረድቷል። የህብረት ስራ ማህበሩ በሴት የቦርድ አባላት የሚመራና በዘርፉ የረጅም ዓመት ልምድ ባካበቱ ባለሞያዎች የተቋቋመ መሆኑም አስረድቷል። በዘርፉ አሁን ላይ እየተተገበሩ ከሚገኙ የብድር አገልግሎቶች በተለየ መልኩ አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ መምጣቱን በመጠቆም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚነትን ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑም ተጠቅሷል። በቡድን የሚመጡ ብድር ፈላጊዎች ልዩ የወለድ ቅ
Nov 21, 20251 min read


ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በኢትዮጵያ በሚከሰቱ ሞቶች ከግማሽ በላይ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑንን ጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
ህዳር 12 2018 ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በኢትዮጵያ በሚከሰቱ ሞቶች ከግማሽ በላይ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑንን ጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ የኩላሊት ህመተኞችን በተመለከተ የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች መጀመራቸውን ሰምተናል፡፡ እየጨመሩ ካሉ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች መካከል የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት፣ ስትሮክ፣ ኩላሊት፣ የልብና የደም ስር መዘጋት እንዲሁም የአዕምሮ መታወክና ካንሰር ከብዙ በጥቂቶቹ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ ተናግሯል፡፡ በተለይም የደም ግፊት ከፍተኛ ለሆነ የኩላሊት በሽታ እያጋለጠ እንደሆነና በዚህም 6 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ስር ለሰደደ የኩላሊት ህመም አንደሚጋለጡ በጥናት መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ነግረውናል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ያሉት ስር የሰደደ የኩላሊት ህመምን ለ
Nov 21, 20251 min read


በየጊዜው የሚለዋወጡ ህጎች የኢንቨስትመንት መስኩ ተገማች እንዳይሆን ማድረጉን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተናገረ።
ህዳር 12 2018 በየጊዜው የሚለዋወጡ ህጎች የኢንቨስትመንት መስኩ ተገማች እንዳይሆን ማድረጉን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተናገረ። የፀጥታ ችግርም እንቅፋት እንደሆነበት ኮሚሽኑ ለህዝብ እንደራሴዎች ተናግሯል፡፡ ኪሚሽኑ ይህን የተናገረው የሶስት ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ትናንት ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ባቀረበበት ወቅት ነው። የኢንቨስትመንት ኮሚሽንን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሪፖርት በንባብ ያቀረቡት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዳገቶ ኩምቢ ባለፉት 3 ወራት 400 ሚሊዮን ዶላር በተኪ ምርት ወይንም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት ታቅዶ መፈጸም የተቻለው ግን 211 ሚሊዮን ዶላር ወይንም የእቅዱን 53 በመቶ እንደሆነ አስረድተዋል። 19 የሚሆኑ ድርጅ
Nov 21, 20252 min read


ለኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት 32 በመቶ ያሚያበረክተው ግብርና
ህዳር 12 2018 ለኢትዮጵያ ጥቅል ሀገራዊ ምርት 32 በመቶ ያሚያበረክተው ግብርና፤ አሁንም በአብዛኛው በበሬ ከማረስ አልተላቀቀም፡፡ ዛሬም የሀገሬው #ገበሬ ከራሱ አልፎ ሌሎችን መመገብ ፈተና ሲሆንበት ይታያል። ለመሆኑ ለሃገር ውስጥ የምርት አቅርቦትም ይሁን የግብርና ወጪ ንግዱን ገቢ ለማሳደግ እንዴት መሰራት አለበት ስንል የዘርፉን ባለሞያ ጠይቀናል፡፡ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢኮኖሚክስ ምርምር ዳይሬክተር እና ተመራማሪው ታደለ ማሞ(ዶ/ረወ) ገበሬው ችግር የሆነበትንና የተሻለ የምርት አቅርቦት እንዲኖር ቢሰራበት ያሉትን ነግረውናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTub
Nov 21, 20251 min read


በኢትዮጵያ ያሉት ከተሞች መልሰው መልማት አለባቸው ይባላል፤ ግን እንዴት ?
ህዳር 12 2018 በኢትዮጵያ ያሉት ከተሞች ስማቸው ነው እንጂ ከተማ በብዙ መስፈርቶች ከተሞች አለመሆናቸውን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ከተሞቹ መልሰው መልማት አለባቸው ይባላል፡፡ ግን እንዴት ? ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ያሬድ እንዳሻው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s 🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2
Nov 21, 20251 min read


ለመጪውን የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንዲሁም የገና በዓል ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሚሄዱ የውጪ ዜጎች አውደርዕይ መሰናዳቱ ተነገረ
ህዳር 12 2018 መጪውን የፈረንጆች አዲስ ዓመት እንዲሁም የገና በዓል አስመልክቶ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለሚሄዱ የውጪ ሃገር ዜጎች በተለይም ለዲኘሎማቲክ ማህበረሰቡ አውደርዕይ መሰናዳቱ ተነገረ፡፡ ኢትዮጵያን ለዓለም ሀገራት ለማስተዋቅ የተለያዩ ለስጦታ የሚሆኑ ምርቶች ይገኙበታል የተባለው አውደርዕይ የተሰናዳው በሦስት ድርጅቶች ነው ተብሏል፡፡ ኤልቬዜት ኢንተርናሽናል ኤቨንት፣ ዲሊኦፖል ሆቴል፣ እና ሳራ ኔክስት ፋሽን ዲዛይን በጋራ አውደርዕዩን ማሰናዳታቸው ተነግሯል፡፡ የፈረንጆቹ የገና በዓል የተለያዩ ስጦታዎች የሚሰጡበት በመሆኑ ይህንን እድል በመጠቀም ምርቶች እንዲተዋወቁ አውደ ርዕዩ መሰናዳቱን የሳራ ኔክስት ፋሽን ዲዛይን መስራች ሳራ መሀመድ ተናግረዋል፡፡ በአውደ ርዕዩ በተለያዩ ምርቶች ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች እንደሚሳተፉ እና ልምድ የሚ
Nov 21, 20251 min read


‘’በሩብ ዓመቱ ከቀረቡልኝ ቅሬታዎች የሚበዙት፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው’’
ህዳር 12 2018 ህዝብ የሚበድሉ አንዳንድ የመንግስት እና የግል ተቋማት የምሰጣቸውን የእርምት ሀሳብ ባለመቀበል እያስቸገሩኝ ነው ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ። ተቋማቱ አስተዳደራዊ በደል መፈፀማቸውን ያምናሉ፤ ግን ለማስተካከል ፍቃደኛ እየሆኑ አይደለም ተብሏል። በተቋሙ የህግና አስተዳደር በደል ምርመራ መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መንግስቱ ቀኜ አስተዳደራዊ በደል ፈፅመው እንዲያስተካክሉ የነገርናቸው አንድ አንድ ተቋማት፣ የመፍትሔ ሃሳቡን መቀበላቸው በጥፋተኝነት ያስጠይቀናል የሚል ፍራቻ አላቸው ብለውናል፡፡ አንድ አንድ ተቋማት ደግሞ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ምንም አይነት ህጋዊ ዕርምጃ መውሰድ አይችልም የሚል የተሳሳተ ግምት እንዳላቸው ኃላፊው ነግረውናል። የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በሩብ ዓመቱ ከቀረቡለት አቤቱ
Nov 21, 20251 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page








