top of page


ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው የዋጋ ግሽበቱ ነጠላ ድጅት እስኪደርስ ድረስ ይቀጥላል ተባለ፡፡
ታህሳስ 21/2018 ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲው የዋጋ ግሽበቱ ነጠላ ድጅት እስኪደርስ ድረስ ይቀጥላል ተባለ፡፡ ይህም የባንኮች የብድር አሰጣጥ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተጥሎ የቆየው ገደብ እንደሚቀጥል ያሳያል፡፡ ባንኮች ለአስቀማጮች ይሰጡት የነበረው የ7 በመቶ ወለድ በብሔራዊ ባንክ የተወሰነ እንደነበር ይታወሳል፡፡ አሁን ባንኮች እና ቆጣቢዎች እንዲደራደሩበት ወይም ለገበያው እንዲተው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ወስኗል፡፡ በብሔራዊ ባንክ ስር የተቋቋመ የገንዘብ ፖሊስ ኮሚቴ ዛሬ አምስተኛ ዙር ስብሰባውን አካሂዶ መግለጫ አውጥቷል፡፡ ለዛሬ ስብሰባውም የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው የተለያዩ 4 ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የብሄራዊ ባንክ የ15 በመቶ የፖሊሲ ተመን ባለበት እንዲቀጥል የሚለው የመጀመሪያው ውሳኔ ነው፡፡ በሌላ በኩል ኮሚቴው በባንኮች ያለው የጥሬ ገንዘብ ክ
Dec 30, 20252 min read


ምርትና አገልግሎት ያላቸውን፣ ሸማቹንና አሻሻጭን የሚያገናኝ የሞባይል መተግበሪያ በይፉ ስራ መጀመሩ ተነገረ።
ታህሳስ 18/2018 ምርትና አገልግሎት ያላቸውን፣ ሸማቹንና አሻሻጭን የሚያገናኝ የሞባይል መተግበሪያ በይፉ ስራ መጀመሩ ተነገረ። መተግበሪያው "ዳንቴል" ይባላል። በዳንቴል ሶፍትዌር የተዘጋጀው "ዳንቴል" የሞባይል መተግበሪያ አምራቾች ምርታቸውን፣ አገልገሎት አቅራቢዎች ያላቸውን አገልግሎት ሙሉ መረጃ የሚያስቀምጡበት፣ መረጃውን ደግሞ በየራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚያጋሩና ሽያጭ እንዲከናወን የሚያደረጉ ደግሞ የኮሚሽን ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችል ስርዓት ይዞ የመጣ ነው። ይህም ለሸማቹ ገበያ ወጥቼ የት ምን አገኛለሁ የሚለውን የሚያቀልል፣ ለአምራቹም ሰፊ የገበያ እድል የሚፈጥር፣ በተለይ በሽያጭ ስራ ገቢ ለማግኘት ለሚፈልጉ ስልካቸውን ተጠቅመው ገቢ እንዲያገኙ የሚያስች እንደሆነ የድርጅቱ ሀላፊዎች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። መተግበ
Dec 27, 20251 min read


የኢትዮዽያ የሎጅስቲክስ ስርዓት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና
ታህሳስ 17/2018 የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የሀገራትን የምርት ልውውጥ ለማሳደግ ኢኮኖሚያቸውን ይደግፋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ ኢትዮዽያም በዚሁ መስመር ወደ ቀጠናው የንግድ እና ጭነት ስራ ጀምራለች። ሆኖም የሎጀቲክስ ስራውም ጎን ለጎን ሊሰራበት እንደሚገባ ይመከራል። ኢትዮጵያ ከ 90 በመቶ በላይ ጭነቶችን በመኪና ታጓጉዛለች፡፡ በቀጠናው ሀገራት ጋር የሚኖራትን የንግድ ግንኙነት በባቡር እና በሌሎች መንገዶች ብታቀላጥፍ ደግሞ ሎጀስቲክሱ ይበልጥ ውጤት ያመጣል። ገቢ ወጭ እቃዎችን ከአንድ ላኪ ሐገር ወደ ኢትዮዽያ በባሕር፣ በአየር፣ በመሬት ወይም በባቡር ማቀላጠፍ የሎጀስቲክስ ዋና ዋና ስራዎችን ያቀላል። በተለይ በኢትዮጵያ ከገቢና ወጭ ጭነት ጋር በተገናኘ ፤ የመሀል ሐገር ኢኮኖሚው የተሻለ ውጤት እንዲቆጠርበት ፤የጭነት መኪኖች የመ
Dec 26, 20251 min read


ኢትስዊች ኢትዮ-ፔይ(EthioPay) ሲል የሰየመውን ብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ መለያ ይፋ አደረገ፡፡
ታህሳስ 10/2018 ኢትስዊች ኢትዮ-ፔይ(EthioPay) ሲል የሰየመውን ብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ መለያ ይፋ አደረገ፡፡ ኢትዮ-ፔይ ሁሉንም የኢትስዊች ተናባቢ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶች በአንድ ማንነት ስር የሚያሰባስብ እና በፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት በኩል ለደንበኞች ከፊት የሚታይ የብራንድ መለያ ነው ተብሏል። ኢትዮ-ፔይ በርካታ የክፍያ አገልግሎቶችን ለማቀፍ የተነደፈ ብራንድ መሆኑ ትናንት ይፋ በተደረገበት ስነስርዓት ላይ ተነግሯል፡፡ በዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ውስጥ ደህንነቱ በተጠበቀ እና በቅጽበት የዲጂታል ክፍያዎችንም ሆነ የገንዘብ ዝውውር የሚያንቀሳቅስ ብቸኛ የጋራ የዲጂታል መስመር ሆኖ የሚያገለግል ነው ተብሏል። በዋናነት ኢትዮ-ፔይ ገንዘብን በቅጽበት ማንቀሳቀስ ብቻ ሳይሆን የፋይናንስ እና ሌሎች ተቋማትን እንዲሁም ደ
Dec 19, 20251 min read


ንብ ኢንተርናሸናል ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመርኩ 10 ዓመት ሞላኝ አለ።
ታህሳስ 10/2018 ንብ ኢንተርናሸናል ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመርኩ 10 ዓመት ሞላኝ አለ። ከ10 ዓመት በፊት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶች “ንብ ሃላል” በሚል ስያሜ በልዩ መስኮት መስጠት መጀመሩን እና በተለዩ ቅርንጫፎች አገልግሎቱን ሲሰጥ እንደቆየ ባንኩ ተናግሯል። ይህንን የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠትም ንብ ባንክ የሚፈለገውን የሸሪዓ ሕግ አማካሪ ኮሚቴ በማቋቋም የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን ሰምተናል። በዚህ ሰዓትም ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ 23 ቅርንጫፎች እንዳሉት አስረድቷል። በቀሩት ሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በልዩ መስኮት አገልግሎቱ እየቀረበ ነው ተብሏል። የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሔኖክ ከበደ በአዲስ መልክ የተዘጋጀውን ከወለድ ነፃ የ
Dec 19, 20251 min read


የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዲጂታል መንገድ የሚሸጠው ሎተሪ ከፍ እያለ መምጣቱን ተናገረ፡፡
ታህሳስ 9/2018 የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዲጂታል መንገድ የሚሸጠው ሎተሪ ከፍ እያለ መምጣቱን ተናገረ፡፡ ለእዚህም አሁን በገበያ ላይ ያለው የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ዕጣ ተጠቃሽ ነው ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ1954 ለመጀመሪያ ጊዜ እድለኞችን መሸለም እንደጀመረ አስታውሷል፡፡ አገልግሎቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲጂታል ሎተሪ የጀመረው ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህም ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ ጎን ለጎን በዲጅታል፣ በሞባይል መተግበሪያዎች አማካኝነት የቀረበ ነው፡፡ ይህን የዲጂታል ሎተሪ ''ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ'' ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በጋራ የተሰራ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በገበያ ላይ ያለው እና በሃገሪቱ የሎተሪ ሽልማት ታሪክ ትልቁን ወይም 60 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ሎተሪ ገበያ ላይ
Dec 18, 20251 min read


የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከሶስት ዓመት በፊት በጀመረው ከማስያዣ ነፃ በሆነው "ምቹ ብድር አገልግሎት" 40 ቢሊዮን ብር ማበደሩን ተናገረ፡፡
ታህሳስ 8/2018 የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ ከሶስት ዓመት በፊት በጀመረው ከማስያዣ ነፃ በሆነው "ምቹ ብድር አገልግሎት" 40 ቢሊዮን ብር ማበደሩን ተናገረ፡፡ ምቹ ዲጂታል ብድር ከተጀመረ 3 ዓመት ከ3 ወር አንደሆነው ባንኩ ለሸገር በላከው መግለጫ ጠቅሷል፡፡ 40 ቢሊዮን ብር ብድሩ ከ2.44 ሚሊዮን በላይ በሆኑ ሂሳቦች የተሰጠ መሆኑንም ሰምተናል፡፡ ከዚህም ውስጥ 80 በመቶ ተበዳሪዎች ሴቶችን ናቸው ተብሏል፡፡ ብድሩ በጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ሥራ ዘርፍ ለተሰማራው ማህበረሰብ አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ ዋስትና ሆኗል ሲል ብንኩ አስረድቷል፡፡ ምቹ ለብድር ማስያዣ በሚሆን ንብረት እጦት፣ ከፋይናንስ አገልግሎት ተገልለው የቆዩትን የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ዘርፍ የደረሰና ለስኬታቸው ዋቢ እየሆነ ያለ ፈጣን ብድር መሆኑንም በመግለጫው ተጠቅሷል። እን
Dec 17, 20252 min read


ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተከፈለ ካፒታሉ 5 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ተናገረ፡፡
ታህሳስ 3/2018 ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተከፈለ ካፒታሉ 5 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ተናገረ፡፡ ይህም ትልቅ ስኬት ነው ብሏል፡፡ በ2016 በጀት ዓመት የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 2.4 ቢሊዮን ብር እንደነበር ያስታወሰው ባንኩ በአንድ ዓመት ውስጥ የ102 በመቶ አድገት በማምጣት 5 በሊዮን ብር አንደደረሰ ተናግሯል፡፡ ባንኮች ካፒታላቸውን 5 ቢሊዮን ብር እንዲያደርሱ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን መስፈርት ያስታወሰው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከጊዜ ገደቡ በፊት ማሳካት መቻሉ በባስለክሲዮኖቹ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ዘንደ ያለውን ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ አያደገ መመጣቱን ያሳያል ብሏል፡፡ ይህ በመሳካቱ ባንኩ ከሎሎች ባንኮች ጋር መዋሃድ ሳይጠበቅበት እንዲቀጥል እንደሚያስችለው አና የመዋሃድም እቅድ አንደሌለው ተናግሯል፡፡ ይህ እንዲሳካም በተለይ ባለ
Dec 12, 20251 min read


ራሚስ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ ከ4.2 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናገረ።
ህዳር 29 2018 ራሚስ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱ ከ4.2 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናገረ። ይህም በአንድ ዓመት ውስጥ የ85 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ሲል ባንኩ ትናንት ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ባወጣው ሪፖርት ተናግሯል። ራሚስ ባንክ በበጀት ዓመቱ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ በማስመዝገብ ወደ ትርፍ ተሸጋግሬያለሁም ብሏል። ገቢው በዓመቱ ውስጥ የ3,726 ከመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል። ራሚስ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰቡንም ጠቅሷል። የቅርንጫፎቹን ብዛት 47፣ የደንበኞቹ ብዛት ደግሞ 352,000 መድረሳቸው በሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል። ባንኩ በበጀት ዓመቱ ማገባደጃ ላይ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያንና የካርድ ባንኪንግ አገልግሎቶቹን ለደንበኞቹ ማስተዋወቁን እና የላቁ የዲጅታል ባንክ አማራጮችን እንደ ኢንተር
Dec 8, 20251 min read


ኢትዮጵያ ተወዳጁ ቡናዋ በአለም አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ተመራጭ እንዲሆን፣ ይሰራል የተባለ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ማህበር ተመሰረተ።
ህዳር 17 2018 ኢትዮጵያ ተወዳጁ ቡናዋ በአለም አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ተመራጭ እንዲሆን፣ የሚገኘው ገቢም እንዲያድግ ይሰራል የተባለ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ማህበር ተመሰረተ። ማህበሩ በትናንትናው ዕለት የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር)፣ ቡና ላኪዎች በተገኙበት ይፋ ተደርጓል፡፡ የኢትዮጵያ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ማህበር የኢትዮጵያን ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ ያስተዋውቃል፣ የጥራት ደረጃው የጠበቀ እንዲሆን ይሰራል እንዲሁም ለቡና አምራቾች፣ ላኪዎች፣ ከቡና ጋር በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ግኑኝነት ላለቸው አካላት እድሎችን ይፈጥራል ተብሏል። ማህበሩ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና የሚባለው ቡና የትኛው ነው የሚለውን ከአምራቹ፣ ከላኪውና ከሌሎች ጋር በመሆን ይበይናል ሲሉ የማህበሩ ፕሬዚዳንት አሸናፊ አርጋው ነግረውናል፡፡ ባለ
Nov 26, 20252 min read


አሐዱ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ተናገረ።
ህዳር 13 2018 አሐዱ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ተናገረ። ባንኩ በበጀት ዓመቱ በበዙ የባንክ ስኬት መለኪያዎች ይበል የሚያስብል ውጤት ማስመዝገቡን በዛሬው ዕለት ባካሄደው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተናግሯል። ይህ ውጤት የተመዘገበውም በበዙ ችግሮች ውስጥ አልፎ መሆኑንም ጠቅሷል። የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ በበጀት ዓመቱ 7.88 ቢሊዮን ብር ደርሷል፤ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ41 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል። በሂሳብ ዓመቱ ከ88.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰቡንም #አሐዱ_ባንክ ጠቅሷል። ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ10.3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከ2.16 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ ከቀ
Nov 22, 20251 min read


በላይአብ ሞተርስ እና የቻይናው ዩቺ አይ ኩባንያ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት መስማማታቸውም ተሰምቷል
ህዳር 10 2018 በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ የትኞቹ ተሽከርካሪዎች ናቸው ወደ ሀገር ቤት መግባት ያለባቸው? የሚለውን የሚወስን መመሪያ ተዘጋጅቷል፤ በቅርቡም ይፀድቃል ሲል የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ በላይአብ ሞተርስ እና የቻይናው ዩቺ አይ ኩባንያ በ #ተፈጥሮ_ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት መስማማታቸውም ተሰምቷል፡፡ አሁን የተለያዩ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣት ላይ የሚገኘው በላይ አብ ሞተርስ ከዶንግ ፊንግ ሞተርስ ጋር በመሆን በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግሯል፡፡ የመኪናዎቹ ሽያጭ ወደ ገበያ በሚገባበት ወቅት አስፈላጊውን የመኪና መለዋወጫና ሌሎች ግብአቶችን ለማቅረብ ከስምምነት መድረሱንም ሰምተናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. ማርታ በቀለ የሸገርን ወ
Nov 19, 20251 min read


‘’አዲስ ወደ ስራ ለሚገቡ ኢንተርፕራይዞች ብድር የሚሰጡ ተቋማት እጅግ ዝቅተኛ ናቸው’’ የኢንተርፕራይዝ ልማት ኢንስቲትዩት
ህዳር 10 2018 ‘’አዲስ ወደ ስራ ለሚገቡ ኢንተርፕራይዞች ብድር የሚሰጡ የፋይናንስ ተቋማት እጅግ ዝቅተኛ ናቸው’’ ሲል የኢንተርፕራይዝ ልማት ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርፕራይዞች ቁጥር በሚፈለገው ልክ እንዳያድግና ዘርፉ ለውጥ እንዳያመጣ አድርጓል ተብሏል፡፡ የኢንተር ፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን(ዶ/ር) እንደ አፍሪካ እንኳን ቢታይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የኢንተርፕራይዞች ቁጥር እጅግ አነስተኛ ነው ይላሉ፡፡ ለዚህ ብዙ ምክንያቶች ቢኖርም ዋነኞቹ መንግስት በሚፈለገው ልክ አስቻይ ሁኔታ አለመዘርጋቱ ፣ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶች ወደ ስራ ለመግባት ድፍረት ማጣት ተጠቃሽ ናቸው ይላሉ፡፡ ከዚህ ባለፈም ሀሳባቸውን ወደ ስራ ለማስገባት የሚጥሩ ስራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ አቅርቦት እጥረ
Nov 19, 20252 min read


ወደ አውሮፓ ህብረት የሚላክ በአነስተኛ አርሶ አደሮች ማሣ የተመረተ ቡና ከደን ምንጣሮ ነፃ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ ኢትዮጵያ ጀምራለች ተባለ
ህዳር 10 2018 ወደ አውሮፓ ህብረት የሚላክ በአነስተኛ አርሶ አደሮች ማሣ ላይ የተመረተ ቡና ከደን ምንጣሮ ነፃ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ ኢትዮጵያ ጀምራለች ተባለ። ስራው የተጀመረው ህብረቱ ወደ አባል ሀገራቱ የሚላክ የግብርና ምርት ከደን ምንጣሮ ነፃ መሆን እንዳለበት የሚያስገድደውን ህግ ለመተግበር እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ነው። የህብረቱ ህግ የህፃናትን ጉልበት በመጠቀም የሚለቀም ቡና ወደ አባል ሀገራቱ እንዳይገባ የሚከለክል መሆኑንም ሠምተናል። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. ንጋቱ ረጋሣ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerF
Nov 19, 20251 min read


ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ምክንያት የውጪ ባለሃብቶች ለኢንቨስትመንት እየመረጧት ነው ተባለ
ህዳር 5 2018 ኢትዮጵያ ከወር ግድም በፊት በይፋ በተቀላቀለችው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ምክንያት የውጪ ባለሃብቶች ለኢንቨስትመንት እየመረጧት ነው ተባለ። በስምምነቱ መሰረት ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚላኩ ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ጥብቅ የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነግሮናል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናን ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ በይፋ መቀላቀሏ ይታወሳል። ወደ አራት የአፍሪካ ሀገራት ምርቶችን በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት በመላክ ነው የንግድ ቀጠናውን የተቀላቀለችው። በአየር ትራንስፖርት የተላኩት ስጋ እንዲሁም የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ሲሆኑ ፤በየብስ ትራንስፖርት ደግሞ የተላኩት ቡና፣ የጥራጥሬ ምርቶችና የቅባት እህሎች ናቸው። ኬንያ
Nov 14, 20252 min read


የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ ሠራተኞች መብታቸው ለማረጋገጥ የሚደረገው ክትትል እንደሚጠናከር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናገረ
ህዳር 5 2018 በተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ ሠራተኞች መብታቸው ተከብሮ እየሰሩ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ የሚደረገው ክትትል እንደሚጠናከር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናገረ። ከሠሞኑ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአንድ ኢትዮጵያዊ ሠራተኛ ላይ ድብደባ የፈጸመ አንድ የውጪ ዜጋ እና የቅርብ ሃላፊው የስራ ውላቸው ተቋርጦ ከሀገር እንዲወጡ መደረጉን ኮርፖሬሽኑ ጨምሮ ተናግሯል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መብታቸው ተከብሮ እየሰሩ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ ፤ የሚደረገው ክትትል በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናግሯል። ኮርፖሬሽኑ ከሠሞኑ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአንድ ኢትዮጵያዊ ሠራተኛ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት መ
Nov 14, 20251 min read


የሚበዙት ባንኮች ከመደበኛ ስራቸው ውጪ በሆኑ ሌሎች ተግባራት መሰማራታቸው
ህዳር 4 2018 የባንኮች በአቅምም፣ በአገልግሎት ጥራትም ልቀው የመገኘት ሀሳብ በየጊዜው ይነሳል። ባንኮች ወደፊት ለሚመጣው ፉክክር ዝግጁ መሆን አለባቸው ይባላል። በሌላ በኩል የሚበዙት ባንኮች ከመደበኛ ስራቸው ውጪ በሆኑ ሌሎች ተግባራት ሲሰማሩ ይታያል። በኢ-ኮሜርስ፣ በትምህርት ዘርፍ፣ በሎጅስቲክስና በሌላው መፎካከራቸው በዝቶ እየታየ ነው። የክፍያ ሥርዓትን ማገዝ የሚጠበቅባቸው ባንኮች፣ ሶፍትዌር አበልፅገው በተለያየ ንግድና አገልግሎት ውስጥ ሲሳተፉ ይታያል። ይህም የተቋቋሙበት ዓላማ ይህ ነው ወይ? የሚል ጥያቄን ያስነሳል። ባንኮች ከድንችና ሽንኩርት ሽያጭ እስከ ሎጅስቲክ ዘርፍ ገብተው ሲሰሩ ይታያል፡፡ የባንክ ስራውን ከማሳደግና ማቀላጠፍ ወደዚህ ዓይነት ስራ ውስጥ መግባታቸው ምን ይዞ ይመጣል? ባለሙያ ጠይቀናል። ሙሉ
Nov 13, 20251 min read


በኢትዮጵያ የተፈቀደላቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች 89 መሆናቸውን ብሔራዊ ባንክ ተናገረ፡፡
ህዳር 3 2018 በኢትዮጵያ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች 89 መሆናቸውን ብሔራዊ ባንክ ተናገረ፡፡ ቀደም ሲል የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዳይሰጥ ታግዶ የነበረውና ዋና መስሪያ ቤቱ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት በፎልስ ቸርች የሚገኘው ራማዳ ፔይ(ካህ) በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ አጠቃላይ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ በሕጋዊ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ዳግም እንዲካተት መደረጉን ባንኩ በመግለጫው ጠቅሷል። ራማዳ ፔይ በሕጋዊ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ዳግም እንዲካተት የተደረገው አስፈላጊው የቁጥጥርና የክትትል ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑን ተነግሯል። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው የሚገኙ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በሙሉ የሀገሪቱ
Nov 12, 20251 min read


የኢኮኖሚ ድርጅቶችን እንዲቆጥሩ 40,000 ወጣቶች ተሰማርተዋል ተባለ፡፡
ህዳር 2 2018 በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የኢኮኖሚ ድርጅቶችን እንዲቆጥሩ 40,000 ወጣቶች ተሰማርተዋል ተባለ፡፡ ይህንን ያለው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱ ድርጅቶቹን እንዲቆጥሩልኝ ያሰማራኋቸው ወጣቶች ሁሉም የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ናቸው ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ከጥቅምት 1 ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም አይነት የኢኮኖሚ ድርጅቶች መረጃ የመቁጠር ስራ እየከወነ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ በዚህ ቆጠራ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢኮኖሚ ድርጅቶ ብዛት፣ በምን ዘርፍ እንደተሰማሩ፣ ያላቸው የሰው ሀይል፣ የሚገኙበት ቦታ፣ የሚጠቀሙት የግብዓት ዓይነት መጠንና ምንጭ፣ የምርት ሽያጮቻቸውና ምን ያህል ኤክስፖርት እንደሚያደርጉ እንዲሁም በስራቸው የሚገጥሟቸው ችግሮች ይመዘገባል
Nov 11, 20252 min read


አዋሽ ባንክ የመስመር ዲጂታል የብድር አገልግሎት ይፋ ማድረጉን ተናገረ።
ጥቅምት 28 2018 አዋሽ ባንክ የመስመር ዲጂታል የብድር አገልግሎት ይፋ ማድረጉን ተናገረ። ባንኩ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በዲጂታል መተግበሪያ በኩል የብድር አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችል '"መስመር ዲጂታል የብድር አገልግሎት" በአዋሽ ብር ፕሮ መተግበሪያ በኩል አቅርቧል ተብሏል። ባንኩ ይህንን መተግበሪያ ይፋ ያደረገው ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እና ከፈርስት ኮንሰልት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተናግሯል። አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በሙሉ አቅማቸው እንዳይወጡ እና ስራዎችን እንዳይከውኑ ከሚያደርጓቸው ችግሮች መካከል የብድር አገልግሎት አለማግኘት አንዱ መሆኑን የአዋሽ ባንክ ሲኒየር ችፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ዮሀንስ መርጋ አንስተዋል። ለዚህ ችግር መፍትሄ ለመስጠት ደግሞ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አገልግ
Nov 7, 20251 min read


ገበያው ልቅ ነፃነት ሳይሆን የመንግስትን ጥብቅ ቁጥጥር ያሻል ተብሏል
ጥቅምት 27 2018 የአንዳንድ ምርቶች ዋጋ ባልታወቀ ምክንያት ሁለትና ሶስት እጥፍ ሲያድግ ሌላ ጊዜ ደግሞ በዛው ልክ ሲወርድ ይታያል፡፡ የደላሎች ጣልቃ ግብነት እና የመንግስት የቁጥጥር ማነስ እንዲህ ላለው ያልተረጋጋ ዋጋ ምክንያቶች መካከል እንደሆኑ ባለሙያዎች ይነገራሉ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራትም ገበያው ልቅ ነፃነት ሳይሆን የመንግስትን ጥብቅ ቁጥጥር ያሻል ተብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… ንጋቱ ረጋሣ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… 👇👇👇 🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/ 🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478 🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1 📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm 💬Wh
Nov 6, 20251 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

