top of page

በላይአብ ሞተርስ እና የቻይናው ዩቺ አይ ኩባንያ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት መስማማታቸውም ተሰምቷል

  • sheger1021fm
  • 20 hours ago
  • 1 min read

ህዳር 10 2018


በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ የትኞቹ ተሽከርካሪዎች ናቸው ወደ ሀገር ቤት መግባት ያለባቸው? የሚለውን የሚወስን መመሪያ ተዘጋጅቷል፤ በቅርቡም ይፀድቃል ሲል የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


በላይአብ ሞተርስ እና የቻይናው ዩቺ አይ ኩባንያ በ #ተፈጥሮ_ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት መስማማታቸውም ተሰምቷል፡፡


አሁን የተለያዩ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣት ላይ የሚገኘው በላይ አብ ሞተርስ ከዶንግ ፊንግ ሞተርስ ጋር በመሆን በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግሯል፡፡


የመኪናዎቹ ሽያጭ ወደ ገበያ በሚገባበት ወቅት አስፈላጊውን የመኪና መለዋወጫና ሌሎች ግብአቶችን ለማቅረብ ከስምምነት መድረሱንም ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page