በኢትዮጵያ የተፈቀደላቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች 89 መሆናቸውን ብሔራዊ ባንክ ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- 50 minutes ago
- 1 min read
ህዳር 3 2018
በኢትዮጵያ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች 89 መሆናቸውን ብሔራዊ ባንክ ተናገረ፡፡
ቀደም ሲል የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዳይሰጥ ታግዶ የነበረውና ዋና መስሪያ ቤቱ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት በፎልስ ቸርች የሚገኘው ራማዳ ፔይ(ካህ) በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ አጠቃላይ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ በሕጋዊ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ዳግም እንዲካተት መደረጉን ባንኩ በመግለጫው ጠቅሷል።
ራማዳ ፔይ በሕጋዊ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ዳግም እንዲካተት የተደረገው አስፈላጊው የቁጥጥርና የክትትል ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑን ተነግሯል።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው የሚገኙ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በሙሉ የሀገሪቱ ሕግና ደንብ የሚጠይቀውን መስፈርት ለማሟላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል።
በውጪ አገር የሚኖሩ ሰዎች ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ በሚያስተላልፉበት በማንኛውም ወቅት ሕጋዊና ግልጽ የሆነ አካሄድ መከተላቸውን ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው ባንኩ አስረድቷል።
ፈቃድ የተሰጣቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን በ https://nbe.gov.et/mta/ ማወቅ አንደሚቻል ባንኩ ጠቁሟል።
በተሰጠው ዝርዝር መሰረትም በኢትዮጵያ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን ብዛት 89 መሆናቸውን ተመልክተናል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








