የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ ሠራተኞች መብታቸው ለማረጋገጥ የሚደረገው ክትትል እንደሚጠናከር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናገረ
- sheger1021fm
- Nov 14
- 1 min read
ህዳር 5 2018
በተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ ሠራተኞች መብታቸው ተከብሮ እየሰሩ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ የሚደረገው ክትትል እንደሚጠናከር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናገረ።
ከሠሞኑ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአንድ ኢትዮጵያዊ ሠራተኛ ላይ ድብደባ የፈጸመ አንድ የውጪ ዜጋ እና የቅርብ ሃላፊው የስራ ውላቸው ተቋርጦ ከሀገር እንዲወጡ መደረጉን ኮርፖሬሽኑ ጨምሮ ተናግሯል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መብታቸው ተከብሮ እየሰሩ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ ፤ የሚደረገው ክትትል በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናግሯል።
ኮርፖሬሽኑ ከሠሞኑ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአንድ ኢትዮጵያዊ ሠራተኛ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት መነሻ አድርጎ እንዳለው የትኛውም ስራ ሲሰራ የዜጎችን መብት ባከበረ መልኩ መሆን አለበት።
በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ይሰሩ በነበሩ አንድ ኢትዮጵያዊ እና የቅርብ አለቃው መካከል የተፈጠረው አለመግባባት መነሻ በስራ ገተበታህ ላይ አልተገኘህም የሚል እንደሆነ፤ የኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ ጳውሎስ በለጠ ነግረውናል።
ክስተቱን ተከትሎ ድብደባውን የፈጸመው የውጭ ዜጋ እና የእሱ የቅርብ አለቃ የሆነ ሰው የስራ ውላቸው ተቋርጦ ከሀገር እንዲወጡ ተደርጓል ተብሏል።
ችግሩን ተከትሎ እርምጃ አልወሰዱም የተባሉ ሶስት የኩባንያው የስራ ሃላፊዎች ደግሞ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ አንደተሰጣቸው አቶ ጳውሎስ ተናግረዋል።
የትኛውም ስራ ሲሰራ የዜጎች መብት እና የሀገር ህግ ተከብሮ መሆን እንደሚገባው የተናገሩት አቶ ጳውሎስ ፤ በሁሉም የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መብታቸው ተከብሮ እየሰሩ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ የምናደርገውን ክትትል ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን እናጠናክራለን ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments