top of page

የሚበዙት ባንኮች ከመደበኛ ስራቸው ውጪ በሆኑ ሌሎች ተግባራት መሰማራታቸው

  • sheger1021fm
  • 22 minutes ago
  • 1 min read

ህዳር 4 2018 

 

የባንኮች በአቅምም፣ በአገልግሎት ጥራትም ልቀው የመገኘት ሀሳብ በየጊዜው ይነሳል።

 

ባንኮች ወደፊት ለሚመጣው ፉክክር ዝግጁ መሆን አለባቸው ይባላል።

 

በሌላ በኩል የሚበዙት ባንኮች ከመደበኛ ስራቸው ውጪ በሆኑ ሌሎች ተግባራት ሲሰማሩ ይታያል።

 

በኢ-ኮሜርስ፣ በትምህርት ዘርፍ፣ በሎጅስቲክስና በሌላው መፎካከራቸው በዝቶ እየታየ ነው።

ree

 

የክፍያ ሥርዓትን ማገዝ የሚጠበቅባቸው ባንኮች፣ ሶፍትዌር አበልፅገው በተለያየ ንግድና አገልግሎት ውስጥ ሲሳተፉ ይታያል።

 

ይህም የተቋቋሙበት ዓላማ ይህ ነው ወይ? የሚል ጥያቄን ያስነሳል።

 

ባንኮች ከድንችና ሽንኩርት ሽያጭ እስከ ሎጅስቲክ ዘርፍ ገብተው ሲሰሩ ይታያል፡፡

 

የባንክ ስራውን ከማሳደግና ማቀላጠፍ ወደዚህ ዓይነት ስራ ውስጥ መግባታቸው ምን ይዞ ይመጣል?  ባለሙያ ጠይቀናል።

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

 

ቴዎድሮስ ወርቁ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page