አዋሽ ባንክ የመስመር ዲጂታል የብድር አገልግሎት ይፋ ማድረጉን ተናገረ።
- sheger1021fm
- 1 day ago
- 1 min read
ጥቅምት 28 2018
አዋሽ ባንክ የመስመር ዲጂታል የብድር አገልግሎት ይፋ ማድረጉን ተናገረ።
ባንኩ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በዲጂታል መተግበሪያ በኩል የብድር አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችል '"መስመር ዲጂታል የብድር አገልግሎት" በአዋሽ ብር ፕሮ መተግበሪያ በኩል አቅርቧል ተብሏል።
ባንኩ ይህንን መተግበሪያ ይፋ ያደረገው ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እና ከፈርስት ኮንሰልት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተናግሯል።
አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በሙሉ አቅማቸው እንዳይወጡ እና ስራዎችን እንዳይከውኑ ከሚያደርጓቸው ችግሮች መካከል የብድር አገልግሎት አለማግኘት አንዱ መሆኑን የአዋሽ ባንክ ሲኒየር ችፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ዮሀንስ መርጋ አንስተዋል።
ለዚህ ችግር መፍትሄ ለመስጠት ደግሞ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አገልግሎት የማመቻቸት ስራ እየከወነ እንደሆነ ተናግረዋል።

መስመር በተሰኘው የብድር ፕሮግራም ላለፉት ሶስት አመታት በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አገልግሎቱን እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ያነሳው አዋሽ ባንክ ስልጠናዎችን እና የብድር ዕድሎችን እያመቻቸሁ ነው ብሏል።
በዚህም ፕሮግራሙ ከተጀመረ እስካሁን ድረስ ከ66,000 በላይ ኢንተርፕራይዞች አገልግሎቱን ለማግኘት ጥያቄ ያቀረቡ መሆኑን ያነሱት አቶ ዮሀንስ መርጋ ከነዚህም ውስጥ ከ13,000 በላይ ለሚሆኑት ከ1.3 ቢሊየን ብር በላይ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርገናል ብለዋል።
በዚህ የብድር አገልግሎት ሴት ስራ ፈጣሪዎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ሲባል ሰምተናል።
ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ውስጥ 32 በመቶዎቹ ሴቶች ናቸው ተብሏል።
ዛሬ በአዋሽ ባንክ ይፋ የተደረገው የመስመር ዲጂታል የብድር አገልግሎት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የብድር አገልግሎት በማዘመን ይረዳል ተብሎለታል።
ከብድር ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ለመሆንም በአዋሽ ብር ፕሮ በኩል ወይም *901# ላይ በመደወል ደንበኞች አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ አዋሽ ባንክ እወቁልኝ ብሏል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








