top of page

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተከፈለ ካፒታሉ 5 ቢሊዮን ብር  እንደደረሰ ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Dec 12, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 3/2018


ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተከፈለ ካፒታሉ 5 ቢሊዮን ብር  እንደደረሰ ተናገረ፡፡


ይህም  ትልቅ ስኬት ነው ብሏል፡፡


በ2016 በጀት ዓመት የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 2.4 ቢሊዮን ብር እንደነበር ያስታወሰው ባንኩ  በአንድ ዓመት ውስጥ የ102 በመቶ አድገት በማምጣት 5 በሊዮን ብር አንደደረሰ ተናግሯል፡፡


ባንኮች ካፒታላቸውን 5 ቢሊዮን ብር እንዲያደርሱ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን መስፈርት ያስታወሰው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ  ከጊዜ ገደቡ በፊት ማሳካት መቻሉ በባስለክሲዮኖቹ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ዘንደ ያለውን ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ አያደገ መመጣቱን ያሳያል ብሏል፡፡

ይህ በመሳካቱ ባንኩ ከሎሎች ባንኮች ጋር መዋሃድ ሳይጠበቅበት እንዲቀጥል እንደሚያስችለው አና የመዋሃድም እቅድ አንደሌለው ተናግሯል፡፡


ይህ እንዲሳካም በተለይ ባለአክሲዮኞች ከፍተኛ አስተዋጾ ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡


ግሎባል ባንክ ኢትዮጰየ በ2017 በጀት ዓመት ከ 5.56  ቢሊዮን  ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን በአመታዊ ሪፖርቱ ተናግሯል፡፡


ይህም ባለፈው ዓመት ከተመዘገበው  ጋር ሲነፃፀር የ37 በመቶ ጨማሪ ማሳየቱን ተጠቅሷል፡፡


የባንኩ ጠቅላላ ሃብት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ  34.4  ቢሊዮን መድረሱ የተነገረ ሲሆን  ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ 42 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል፡፡


ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ  በ2017 በጀት ዓመት 7.53 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡን በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡


የባንኩን አጠቃላይ ተቀማጭ 25.75  ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ተብሏል፡፡


ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ፣ ከመጠባበቂያ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ 1.17 ቢሊዮን ብር አትርፌያለሁ ይህም ከቀዳሚው አመት ጋር ሲመሳከር የ33 በመቶ ብልጫ አለው ብሏል፡፡


የቅርንጫፎቹ ብዛት 237፣ የደንበኞቹ ቁጥር ደግሞ 1.8 ሚሊዮን መድረሳቸወንም አስረድቷል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page