ምርት ለማጓጓዝ ከፍተኛ ቢሮክራሲና የተጠላለፈ አንደኛው ፈተና
- sheger1021fm
- 9 minutes ago
- 1 min read
ጥቅምት 26 2018
ለዘመናት የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ ሲረብሽ የነበረው ጉዳይ የኮንቴይነር እጥረት፣ የአስተሻሸግ ችግር እና ቅሸባ እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል።
ይኸው ችግር ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ የምታቀርባቸውን ምርቶች እንዲወድቁ ወይም እንዲመለሱ አድርጓል።
ከዚህም ባለፈ ምርት ለማጓጓዝ ከፍተኛ ቢሮክራሲና የተጠላለፈ የሎጅስቲክስ ስራም አንደኛው ፈተና ነው።
በአየር፣ በየብስ፣ በባህር፣ በባቡር፣ የሎጅስቲክስ ስራዋን ማቀላጠፍ ያላወቀችበት ኢትዮዽያ አሁንም ከዚህ መዓዘን ብዙ ስራ ይጠብቃታል።
ይህ በመሆኑም ከወጪ ንግድ የታሰበውን ያህል የውጪ ምንዛሪ ለመለቃቀም ፈትኖ ቆይቷል።
በተለይ በወጪ ንግድና ሌላውም ንግድ የሚሳተፉ በሙሉ የሎጀስቲክስ መደነቃቀፍን አሁንም ያነሳሉ፡፡
ከዚህም በላይ የኢትዮዽያ ወጭ ንግድ የውድድር እና ጥራት ችግር እያጋጠመው በሎጅስቲክስ አለመቀላጠፍም ምርቱ ሲመለስ ተሰምቷል ፤ የሐገርንም ስም በክፉ ሲያስነሳ ቆይቷል።
ይህን እና ተያያዥ የሎጅስቲክስ ችግሮችን ለመፍታት በአንደኛው ጠርዝ የተሰየመው የኢትዮጵያ ፍሬት ፎርዋርደርስ ኤንድ ሺፒንግ ኤጀንትስ አሶሴሽን እና ሌሎችስ ምን ይመክራሉ?

በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ፍሬት ፎርዋርደርስ ኤንድ ሺፒንግ ኤጀንትስ አሶሴሽን ፕሬዝዳንትና በአለም አቀፍ ፍሬይት ፎርዋርድ አሶሴሽን ፊያታ የቦርድ አባል የሆኑትን አቶ ዳዊት ውብሸትን ጠይቀናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s








