ነሀሴ 2 2017 - የኢትዮጵያ ባንኮች በመዋሃድ የተሻለ ካፒታልና ጉልበት እንዲኖራቸው እየተመከሩ ነው፡፡
- sheger1021fm
- Aug 8
- 1 min read
የውጪ ባንኮች በኢትዮጵያ ስራ እንዲጀምሩ በሩ ከተከፈተ 3 ዓመት አለፈው፤ ግን እስካሁን ፍላጎት ካሳዩ ባንኮች በቀር ወደ ኢትዮዽያ ገብቶ ስራ የጀመረ የለም።
ይህ ስራ በባንኮች መካከል ፉክክሩን እንደሚያጠናክረው ይታመናል።
የኢትዮጵያ ባንኮች በመዋሃድ የተሻለ ካፒታልና ጉልበት እንዲኖራቸው እየተመከሩ ነው፡፡
እንዲህ ያለው አሰራርም በሌላው አለም የተለመደ ነው ሲሉ የንብ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሔኖክ ከበደ ያስረዳሉ።
በኢትዮጵያ ግን ይህ አሰራር አዲስ እንደመሆኑ እና ባንኮቹ የተለያየ ጠባይ ያላቸው በመሆኑ ምን ፈተናዎች ይኖሩታል?
መዋሃድ አለባቸው ሲባልስ እንዴት?
በሌላ በኩል ባንኮች በቁጥር አሁንም ብዙ አይደሉም ብለው እንደውም ቁጥራቸው ጨምሮ ዘርፋቸው መለያየት አለበት ብለው የሚሞግቱት ደግሞ በድሎይት አለም አቀፍ የኢንቨስትመንት አማካሪ የአፍሪካ ኢኮኖሚክስ አድቫይሰሪ ሊደርና በምስራቅ አፍሪካ የመርጅ አክዩሴሽነእ ቡድን መሪ አቶ ቴዎድሮስ ናቸው።
ለመሆኑ በየሰፈርና ቡድን ቅርጫቱ የተከፋፈሉት የኢትዮዽያ ባንኮች ይዋሀዱ ቢባልስ መንገዱ ምን ያህል እረጅምና ቀላል ሊሆን ይችላል?
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyu.com/ycxjmm3s











Comments