top of page

ትምህርት የማህበረሰብ አገልግሎት መሆን ሲገባው እንዴት ወደ ንግድ መስመር ሊገባ ይችላል?

  • sheger1021fm
  • Aug 14
  • 1 min read

ሁሉም ፊቱን ወደ ትምህርት ያዙር፣ ትምህርት ከንግድ እና ቢዝነስ ጠባይ ይላቀቅ፣ ትምህርት ፈፅሞ ንግድ አይደለም ሊሆንም አይችልም ሲባል ምን ማለት ይሆን?


በእርግጥ በኢትዮጵያ #ትምህርት ንግድ ነው፤ ለዚያውም የተጧጧፈ የቢዝነስ ስራ ነው ይባላል።


በተለይ የግል ተማሪ ቤቶች የንግድ ፈቃድ አውጥተው ወይም ከአምራችና አገልግሎት አቅራቢ ፈቃድ ጋር አጣምረው የሚሰሩት እንደሆነ ይሰማል።


ታዲያ ትምህርት የማህበረሰብ አገልግሎት መሆን ሲገባው እንዴት ወደ #ንግድ መስመር ሊገባ ይችላል? አካሄዱም ከዚህ መላቀቅ አለበት ተብሏል።


አቶ ደሳለኝ መኩሪያ ባለፉት 20 ዓመታት ከታች ከአንደኛ ደረጃ አንስቶ እስከ ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ በመምህርነት አገልግለዋል።


በትምህርት ቢዝነስ ስራና ኢኮኖሚ ውስጥም በአስተዳደር ጭምር ለረጅም ጊዜ ቆይተዋል።


አቶ ደሳለኝ ትምህርት የማህበረሰብ አገልግሎት እንጂ የንግድ ፈቃድ ወጥቶበት የሚሸቀጥ ዘርፍ አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

ተያያዥ ዘገባን ለማድመጥ….

ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበል

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page