ሐምሌ 22 2017 - አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አተገባበር ላይ ስጋት አለኝ ብሏል
- sheger1021fm
- Jul 29
- 1 min read
የፀጥታ ችግሮች እልባት አለማግኘታቸው፣ በጥቁር ገበያውና በመደበኛው የምንዛሪ ዋጋ መካከል ልዩነቱ እየሰፋ መሄዱ፣ የታሰበውን ያህል የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት አለመገኘቱ፣ እርዳታና ድጋፎች መቀነሳቸውና ሌላውንም በማንሳት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ወደ ኋላ ሊያንሸራትተው ይችላል ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ከIMF ጋር ለ4 ዓመት ውል አስራ እየተገበረችው ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተቋሙ ከሳምንት በፊት ያወጣው ሪፖርት ለሶስተኛ ጊዜ ግምገማ ካደረገ በኋላ ይፋ ያደረገው ነው፡፡
በዚህም ለመጀመሪያ ጊዜ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ወደ ኋላ ሊወስዱ ይችላሉ ያላቸውን ስጋቶችን በዝርዝር አሳውቋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፕራግማ ካፒታል ስራ አስፈፃሚ እና የኢንቨስትመንትና ፋይናንስ ባለሙያው መርዕድ ፍቅረዮሐንስ በተቋሙ የተነሱት ስጋቶች ትክክል መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር በመጭው ነሐሴ ወር ከ44 አባዳሪዎች ጋር ድርድር እንደሚጠብቀው ጠቅሰው IMF ሶስተኛ ያወጣውን ይሄንኑ ሪፖርት በጥብቅ እንደሚከተሉት የሚጠረጠር አይደለም ብለዋል፡፡
በመሆኑም በድርድሩም ወቅት ሊነሳ የሚችለው ዋናው ጉዳይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ይሳካል ወይ? የሚለው እንደሚሆን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለህልውናዋ ስትል የጀመረችውን ማሻሻያ እንዲሳካና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን የቤት ስራዎች ሁሉ በመስራት በትክክለኛው ሐዲድ እንዲሄድ ማድረግ ይጠበቅባታል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ውል ገብታ ብድር የወሰደችበት ማሻሻያ ካልተሳካና ወደኋላ ከሄደ ለኢትዮጵያ እጅግ የከፋ ይሆናልም ይላሉ፡፡
ካልተሳካላት የፋይናንስ አበዳሪና ደጋፊዎች በጥርጣሬ የሚያዩዋት፣ ትሆናለች ተብሏል፡፡
ለምታቅዳቸው ፕሮጀክቶችም ፋይናንስ ድጋፍ ማግኘት የሚቸግራትና ለኢኮኖሚዋም ወደ መደበኛ አሰራር ያስገባቻቸው አሰራሮች ሁሉ ከእጇ የሚያመልጡ እንደሚሆን ስጋታቸውን ተናግረዋል፡፡
IMF በጠንካራ ጎን የጠቀሳቸው ነጥቦችም አሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments