top of page


በቀን እስከ 50 ሺህ ስኩዌር ሜትር ወይም ከ40 እስከ 45 ኮንቴነር ሴራሚክ ማምረት የሚችል ፋብሪካ ከ3 ሳምንት በኋላ ምርት ይጀምራል ተባለ።
መጋቢት 28/2018 በቀን እስከ 50 ሺህ ስኩዌር ሜትር ወይም ከ40 እስከ 45 ኮንቴነር ሴራሚክ ማምረት የሚችል ፋብሪካ ከ3 ሳምንት በኋላ ምርት ይጀምራል ተባለ። በ50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመንት ከአዲስ አበባ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በቱለፋ ከተማ የተገነባው ይህን ፋብሪካ የገነባው ባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ የተባለ ድርጅት ነው። በ30 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ የሴራሚክ እና የፖርስሊን ምርቶች ፋብሪካ ምርት ሲጀምር ብቻውን አሁን ካለው የሴራሚክ ፍላጎት እስከ 70 በመቶ ድረስ የማቅረብ አቅም አለው ተብሎለታል። በባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ የሚመረቱን ምርቶች ለገበያ የሚያቀርበው ማንሰን ኢንቨስትመንትስ ነው። የማንሰን ኢንቨስትመንትስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳዊት እርገቱ እና የባይጂያ ሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ ዋና
1 day ago1 min read


ዳሸን ባንክ ልዩ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድር ሽልማትን ጨምሮ አራት አዳዲስ አገልግሎቶችን ዛሬ አስጀመረ።
መጋቢት 24/2018 ዳሸን ባንክ ልዩ የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድር ሽልማትን ጨምሮ አራት አዳዲስ አገልግሎቶችን ዛሬ አስጀመረ። ባንኩ የሱፐር አፕ ተጠቃሚዎችን ለማበረታት እንዲሁም የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋት የቲክቶክ ይዘት ፈጠራ ውድድር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል። በዚህ ውድድር ለሚያሸንፉ የይዘት ፈጣሪዎች በድምሩ ስድስት ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት እንዳዘጋጀ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት (ኮሜርስ) በተዘጋጀ ስነ ስርአት ላይ ተነግሯል። በዳሸን ሱፐር አፕ ቲክቶክ ቻሌንጅ አሸናፊ ለመሆን ይዘት ፈጣሪዎች ስለ ዳሸን ባንክ ሱፐር አገልግሎቶች የሚገልፅ የቲክቶክ ቪዲዮ በመስራት ማጋራት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። የሰሩት ቪዲዮ በቲክቶክ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዕይታ ሲያገኝ፣ በዳሸን ሱፐር አፕ ውስጥ በሚገኘው የዳሸን ክሬቲቭ አ
5 days ago1 min read


ቪዛ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ ቪዛ ካርድ ደንበኞች የ2026 የዓለም ዋንጫን በአካል ተገኝተው የሚመለከቱበትን ዕድል ይዘው መቅረባቸውን ተናገሩ።
መጋቢት 24/2018 ቪዛ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ ቪዛ ካርድ ደንበኞች የ2026 የዓለም ዋንጫን በአካል ተገኝተው የሚመለከቱበትን ዕድል ይዘው መቅረባቸውን ተናገሩ። ዕድሉ የምድብ ጨዋታዎችን በአካል ለመመልከት የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል። ይህ ከመጋቢት 5 እስከ ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ንቅናቄ፣ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ የባንኩ የዴቢትም ሆነ የቅድመ ክፍያ ቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች በሙሉ ክፍት ነው ተብሏል። ደንበኞቹ በቪዛ ካርዳቸው የሚፈጽሙት እያንዳንዱ ግብይት እንደ አንድ ዕጣ ይቆጠራል የተባለ ሲሆን ለዚህ ምዝገባ አይጠየቅም ተብሏል። በቪዛ የምሥራቅ አፍሪካ ክላስተር ሓላፊ የሆኑት ያሬድ እንዳለ፣ የካርድ ተጠቃሚዎችን በየቀኑ እየፈጸሟቸው ለሚገኙ ግብይቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ተባብረን በመሸለማችን ደስተኞች ነን'' ብለዋል።
5 days ago1 min read


የእሳት እራት ተብሎ የሚጠራው ነፍሳት በኢትዮጵያ በአፅዋት ላይ ምንም ጉዳት የማያስከትል ቢሆንም አውሮፓ ከገባ ግን ከ100 በላይ የእፅዋት ዓይነቶችን ቀርጥፎ የሚበላ ሌላ ባህሪ ያለው ተባይ ይሆናል፡፡
መጋቢት 24/2018 የእሳት እራት ተብሎ የሚጠራው ነፍሳት በኢትዮጵያ በአፅዋት ላይ ምንም ጉዳት የማያስከትል ቢሆንም አውሮፓ ከገባ ግን ከ100 በላይ የእፅዋት ዓይነቶችን ቀርጥፎ የሚበላ ሌላ ባህሪ ያለው ተባይ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት ከአመታት በፊት በኢትዮጵያ የአበባ እርሻዎች ውስጥ መገኘቱን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ተባዩ ከምርቱ ጋር ወደኛ እንዳይመጣብን የሚል ማሳሰቢያ ሰትቶ ነበር፡፡ የአበባ ምርት ወደ ህብረቱ እንዳይገባ ከመታገዱ በፊት ምን እርምጃ ተወሰደ፡፡ በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል F C M የሚሰኘው ተባይ የቢራቢሮ ዝርያ ሲሆን በእኛ አገር የእሳት እራት በመባል ይታወቃል ። በሀገራችንአብዛኞቹ ዕፅዋት የዚህ ተባይ መኖሪያ ሆነው እንደሚያገለግሉ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ወንዳለ ሃብታሙ ነግረውናል፡፡
5 days ago1 min read
በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ።
መጋቢት 22/2018 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ። በእንግሊዝና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው የመኖሪያ ቤት ማፍራት የሚችሉበትን ዕድል ለመፍጠር የተዘጋጀ ኤክስፖ ነው ተብሏል። በሪል ስቴት አልሚዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ያለውን መተማመን ለማሳደግና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ግብይቶች እንዲፈፅሙ የተዘጋጁ ስርዓቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑም ተጠቅሷል። በኤክስፖው ላይ ከሚመለከታቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በሚደረግ የመረጃ ልውውጥና የፓናል ውይይት በዘርፉ ስላሉ ችግሮች ይነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኤክስፖውን አስመልክቶ ከተዘጋጀ መግለጫ ላይ ተመልክተናል። ባንኮች በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቢዝነስ ድ
Mar 311 min read


የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች አሁን ላይ ከ45 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ምርት ፍላጎት እየሸፈኑ ነው ተባለ።
መጋቢት 19/2018 የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች አሁን ላይ ከ45 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ምርት ፍላጎት እየሸፈኑ ነው ተባለ። እንደ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ከውጪ ይገቡ የነበሩትን ምርቶች እዚሁ በማምረት በከፊልም ቢሆን ፍላጎቱን እየሸፈኑ ነው። በዚህም ፋብሪካዎቹ ምርቶችን ወደ ተለያዩ ሀገራት በመላክ የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘት ባሻገር የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ማሟላት ላይም ጥሩ ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ መረዳት ይቻላል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ተናግረዋል። ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ከመሠረተ ልማት እና ብድር አቅርቦት ጋር የተገናኙ የፋብሪካዎቹ ችግሮች እንዲፈቱ የተደረገው ጥረት ውጤቶቹ እንዲገኙ አግዘዋል ብለዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር በአዲስ አበ
Mar 281 min read


የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ የተሰራው ስራ ውጤት እያመጣ ነው ሲል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተናገረ።
መጋቢት 18/2018 የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ የተሰራው ስራ ውጤት እያመጣ ነው ሲል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተናገረ። ሚኒስቴሩ እንዳለው የፋብሪካዎቹ አማካይ የማምረት አቅም አሁን ላይ 66.3 በመቶ ደርሷል። ከ8ዓመት በፊት አማካይ የማምረት አቅማቸው 46 በመቶ እንደነበር የሚኒስቴሩ የመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አበባ ታመነ ተናግረዋል። ከመሠረተ ልማት እና ጥሬ ዕቃ አቅርቦት እንዲሁም ከመንግስታዊ አገልግሎቶች ጋር የተያያዙ ችግሮች እንዲፈቱላቸው የተደረገው ጥረት የፋብሪካዎቹ የማምረት አቅም እንዲሻሻል ረድቷል ብለዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎችን የስራ ሃደት ከትናንት ጀምሮ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ተዘዋውረው እንዲመለከቱ
Mar 271 min read


የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ የገንዘብ እርዳታ ሊደረግላቸው ነው፡፡
መጋቢት 9/2018 የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ የገንዘብ እርዳታ ሊደረግላቸው ነው፡፡ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋሉ ዘርፍ ሴቶች እንዲሰማሩ ይበረታታሉ ብሏል፡፡ አለም አቀፍ የመልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ቀንን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እያከበረች ነው። በየዓመቱ መጋቢት 9 ቀን ወይም እንደ እ.ኤ.አ ማርች 18 ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የመልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እየተከበረ መሆኑን ሰምተናል። "ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ሀብት ነው" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን አለም አቀፍ ኩነትን መሰረት በማድረግ "ቆሻሻን ወደ ዕድል እንቀይር ሴቶችንና ወጣቶችን በኢኮኖሚ እናብቃ" በሚል ሀሳብም በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፔትኮ ኢትዮጵያ ከተባለ
Mar 181 min read


በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ውስጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለአነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ሊቀርብ መሆኑን ተነገረ፡፡
መጋቢት 9/2018 በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ውስጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለአነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ሊቀርብ መሆኑን ተነገረ፡፡ ይህ የሰማነው የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን እና ለእርሻ ድርጅት ባደረጉት አብሮ የመስራት ስምምነት ላይ ነው፡፡ ለእርሻ ደርጅት በሚቀጥሉት 4 ዓመታት አነስተኛ ማሳ ላላቸው ገበሬዎች ብድር ለማመቻቸት አቅዶ እየሰራ መሆኑን የተናገረ ሲሆን ከዚህ በፊት በሙከራ ደረጃ በሰራው ስራ ገበሬዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተጠቅሷል፡፡ የለእርሻ ድርጅት ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም እንድርያስ በዚህ ዓመት ብቻ ለ65 ሺህ ገበሬዎች ብድር ለማቅረብ እቅድ መያዛቸውን የሚናገሩ ሲሆን ለስራውም ከተለያዩ ባንኮች ጋር እንደሚሰሩም አስረድተዋል፡፡ በሙከራ የስራ ወቅት ገበሬው በትክክል የሚፈልገው ብድር ከተሰጠው ያለምንም ችግር ብድሩን መክፈ
Mar 181 min read


በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የሚገላበጠው አብዛኛው ገንዘብ ወይም ከ73 በመቶ በላዩ የሚዟዟረው በዲጂታል መንገድ ነው፡፡
መጋቢት 8/2018 በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት የሚገላበጠው አብዛኛው ገንዘብ ወይም ከ73 በመቶ በላዩ የሚዟዟረው በዲጂታል መንገድ ነው፡፡ በተያዘው የበጀት ዓመት በ6ት ወራት ውስጥ ብቻ 14.56 ትሪሊዮን ብር በዲጂታል መንገድ ተገላብጧል፡፡ ይህ በዲጂታል ገንዘብ ማስተላለፍ ጊዜን የሚቆጥብ፣ ምቹ መሆኑ ቢጠቀስም የአገልግሎት ክፍያውና ሌሎች ተቆራጮች መኖርና ለአጭበርባሪዎች የተጋለጠ ነው በሚልም ይወቀሳል፡ መንግስታዊ ተቋማት ለሚሰጡት አገልግሎት ክፍያቸውን ወደ ድርጅት ባንኪንግ ማዞራቸውን ተከትሎ ከማህበረሰቡ ለአገልግሎት እየተባለ የሚቆረጠው ገንዘብ እየበዛ መጥቷል፡፡ ደመወዝተኛውም ይሁን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ለተለያዩ የክፍያ ስርዓቶች የሚያደርጉት የገንዘብ ልውውጥ ተደራራቢ ታክስ እንዲከፍሉ አያደርግም? በጉዳዩ ላይ
Mar 171 min read


ኢትዮዽያ በአለም የሎጅስቲክስ ሜዳ
የካቲት 27/2018 የሎጅስቲክስ ስራ ፍፁም የሰላም መስመር እና እውቀት ይፈልጋል፡፡ ሎጅስቲክስ በኢትዮጵያ እንዲዘምን፣ እንዲቀላጠፍ አሁንም ብርቱ ስራ ይጠይቃል። እቃዎችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለማንቀሳቀስ፣ መያዝ፣ ማከማቸት እና ማስተናገድ ፤ በየትኛውም የአለም መሮጫ ኮሪደር እና ባህር ማገላበጥ ፤ በአየር በየብስ ምድር ለመላወስ ጥንቅቅ ያለ የሎጅስቲክስ ስራ ይፈልጋል። ለዚህ ደግሞ በየጊዜው በአለም በሚደረጉ ጉባኤዎች እና የሎጅስቲክስ ማህበራት ላይ በኃላፊነት ቦታ መገኘት እንደሚያስፈልግ ይታመናል። በተለይ ከአፍሪካ ብቸኛው የአለም ፍሬይት ፎርዋርደርስ ማህበር ፊያታ የቦርድ አባል እና በ ኢትዮጵያም የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ውብሸት በዚህ ጉዳይ ስጋት እንዳላቸው ነግረውናል። ኢትዮዽያ በአለም የሎጅስቲክስ ሜዳ ፤ በጭነት መርከቦች እና አጠቃላ
Mar 61 min read


የኤ ኤፍ ጂ ኤርክራፍት ፋይናንስ ጀርመን (AFG) እህት ኩባንያ የሆነው ኤ ኤፍ ጂ አቪየሺን አየርላንድ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ሀገራት መግባቱን ተናገረ።
የካቲት 24/2018 በአውሮፕላን ንግድና ሀብት አስተዳደር የሚታወቀው ኤ ኤፍ ጂ ኤርክራፍት ፋይናንስ ጀርመን (AFG) እህት ኩባንያ የሆነው ኤ ኤፍ ጂ አቪየሺን አየርላንድ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ሀገራት መግባቱን ተናገረ። ኩባንያው ለአፍሪካ ስራው ሲልም ሁለት ከፍተኛ ባለሞያዎቹን በአፍሪካ ተገኝተው እንዲሰሩ እንደመደባቸው ባወጣው መግለጫ ተናግሯል። AFG አቪዬሽን አየርላንድ የናይጄሪያው ካሊ ኤር ሁለት CRJ1000 አውሮፕላኖች ባለቤት እንዲሆን ማስቻሉን ተናግሯል። በዚህም የተነሳ የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች፣ አፕሬተሮች፣ የመንግሥት እና የአቪዬሽን ዘርፍ ሀላፊዎች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቸው ተረድቻለሁ ብሏል። ይህ ፍላጎት የአፍሪካ የአቪዬሽን ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረ መምጣቱን ያሳል ሲልም ኩ
Mar 42 min read


አቢሲንያ ባንክ ‹‹ይጀምሩ፣ ያድሱ እና ይደጉ›› በሚል መሪ ቃል ለሁለት ወራት ያህል ባካሄደው ፕሮግራም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ተናገረ።
የካቲት 19/2018 አቢሲንያ ባንክ ‹‹ይጀምሩ፣ ያድሱ እና ይደጉ›› በሚል መሪ ቃል ለሁለት ወራት ያህል ባካሄደው ፕሮግራም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ተናገረ። ከዚህ በተጨማሪም 140 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን አስረድቷል። ባንኩ ፕሮግራሙን ሲያካሂድ የነበረው አዳዲስ ደንበኞችን ለመመልመል፣ ነባር ደንበኞችን ከባንኩ ጋር ያላቸውን ደንበኝነት ለማደስ እንዲሁም ተቀማጭና የውጭ ምንዛሬ ግኝቶችን ለማሳደግ አስቦ እንደነበር ተጠቅሷል። ይህ ፕሮግራም ከህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥር 29 / 2018 ዓ.ም. ድረስ ሲካሄድ ቆይቷል ተብሏል። አቢሲኒያ ባንክ በዚህ መርሃግብር ደንበኞቹ ለማበረታታት ሽልማት አዘጋጅቷል። በዚህ መርሀ ግብር ለሽልማቱ ተሳታፊ የሆኑት ከብር 1000 ሺሕ ብር ጀምሮ ተ
Feb 261 min read


ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገሮች ልዩ ከሚያደርጓት ስርዓቶች አንዱ የቡና አፈላል ስርዓቷ ነው፡፡
የካቲት 17/2018 ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገሮች ልዩ ከሚያደርጓት ስርዓቶች አንዱ የቡና አፈላል ስርዓቷ ነው፡፡ ቡና በኢትዮጵያ ከተሞችም ሆነ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ የተለየ የአቀራረብ ስርዓት አለው፡፡ ይህ የቡና አፈላል ሥርዓትና ሂደት ኢትዮጵያ አለማቀፍ ቅርስ አድርጋ ለማስመዝገብ ስራ መጀመሯም እየተነገረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የቡና አፈላል ሥርዓት (የቡና ሥነ-ሥርዓት) በዓለም አቀፉ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ለማድረግ ስራ ከጀመረች ሰንብታለች፡፡ ኢትዮጵያ የቡና (Arabica Coffee) መገኛ ምድር ብቻ ሳትሆን፣ ቡናን ከመጠጥነት ባለፈ የማኅበራዊ መስተጋብር፣ የሰላም፣ እና የባህል መገለጫዋ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በተጨማሪም የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት በኢትዮጵያውያን ዘንድ የ
Feb 241 min read


የሰላም እጦት ኢትዮጵያን በቆዳው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ያህል ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል ሲል የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ተናገረ።
የካቲት 12/2018 የሰላም እጦት ኢትዮጵያን በቆዳው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ያህል ገቢ እንዳታገኝ አድርጓታል ሲል የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ተናገረ። ማህበሩ ይህን ያለው ለ15 ኛ ጊዜ የሚያካሄደውን የመላው አፍሪካ የቆዳ ንግድ ትርኢት “ሜሴ ፍራንክፈርት” ከተሰኘ አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት አዘጋጅ ጋር በጋራ ለማከናወን ትናንት በስካይ ላይት ሆቴል ባደረጉት ስምምነት ወቅት ነው። በመድረኩ ላይም በፀጥታ ችግር ምክንያት ከፍተኛ ቆዳ የሚገኝባቸው አካባቢዎች ላይ ቆዳዎችን ለመሰብሰብ ባለመቻሉ በርካታ ቆዳዎች በስብሰው እንደቀሩም ተነግሯል። በዚህ ምክንያት ኢንደስትሪዎች ማምረት የሚገባቸውን ያህል የቆዳ ውጤቶች እንዳያመርቱ ፥ ሀገርም በዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ያህል እንዳታገኝ አድርጎታል ተብሏል። በዘርፉ የተሰማሩ ኢንደስትሪዎች እየተቸገሩ
Feb 192 min read


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መዋዕለ ነዋያቸውን ፈሰስ ለሚያደርጉ ባለሀብቶች እምነት እንዲያደርጉ ቢያስችላቸውም በየጊዜው የሚለዋወጡ ህጎች ግን አሁንም ችግር ሆኖ ቀጥሏል ተባለ፡፡
የካቲት 12/2018 ኢትዮጵያ እያደረገቻቸው ያሉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሀገሪቱ መዋዕለ ነዋያቸውን ፈሰስ ለሚያደርጉ ባለሀብቶች እምነት እንዲያደርጉ ቢያስችላቸውም በየጊዜው የሚለዋወጡ ህጎች ግን አሁን ኢንቨስት ለሚያደርጉ ችግር ሆኖ ቀጥሏል ተባለ፡፡ ከውጭ የሚመጣ ሀብት በተወሰኑ ዘርፎች ላይ ብቻ ማዋሉም ሌሎች ዘርፎች በቂ ፋይናንስ እንዳያገኙ ከልክሏል ተብሏል፡፡ እንደ ትምህርት ፣ ጤና ፣ አነስተኛ እና ጥቃቅን ስራ ፈጠራ በመሳሰሉ ማህበራዊ ዘርፎች የሚሳተፉና ተዕኖ የሚያሳድሩ፣ ትርፍም የሚያገኙ ተቋማት የኢንቨስትመንት ሁኔታ ምን ይመስላል በሚል የተደረገ የምክክር መድረክ ላይ ነው ወሬው የሰማነው፡፡ ዝግጅቱን ያሰናዳው ACE investment እና Impact Advisors የተባለ የኢትዮጵያ ተቋም ከአለም አቀፉ አቀፍ GSG ተቋም ጋ
Feb 191 min read


''ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ብድር የምትፈልጉ ኑ ወደ እኔ በቂ የብድር ገንዘብ ተዘጋጅቶላችኋል'' የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የካቲት 11/2018 ''ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ብድር የምትፈልጉ ኑ ወደ እኔ በቂ የብድር ገንዘብ ተዘጋጅቶላችኋል'' ሲል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥሪ አቀረበ። ባንኩ በዚህ ዘርፍ በአሁኑ ሰዓት ብዙ የብር ጥያቄዎች የሉብኝም ብሏል። ባንኩ ይህን ያለው በረመዳን ወር የእልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቹ ዘካ ለመስጠት የሲቢኢ ኑር የዘካ ቁጠባ ሂሳብን እንዲገለገሉ ጥሪ ባቀረበበት ፕሮግራም ላይ ነው፡፡ ባንኩ ‘አብሮነትና በጎነት በረመዳን' ሲል የጠራውን ፕሮግራም በዛሬው እለት አስጀምሯል። የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የዘካ ቁጠባ ሂሳብ አንዱ መሆኑን አስታውሰው በተለይ በረመዳን የእምነቱ ተከታዮች እንዲገለገሉበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አገልግሎቱ የዘካ ሰጪና ተቀባዮችን ጊዜ፣ ወጪ፣ ልፋትና
Feb 181 min read


በተያዘው በጀት ዓመት 6 ወራት በስነ ምግባርና እና ብልሹ አሰራር ምክንያት 651 የሚሆኑ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ።
ጥር 28/2018 በተያዘው በጀት ዓመት 6 ወራት በስነ ምግባርና እና ብልሹ አሰራር ምክንያት 651 የሚሆኑ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ። አስተዳደራዊ እርምጃዎች ከተወሰደባቸው 651 ሰራተኞች የተሰናበቱ 13፣ የደመወዝ ቅጣት 481 እና 157 ደግሞ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተነግሯል። ይህ የተነገረው አገልግሎቱ የ2018 በጀት ዓመት 6 ወራት አፈፃፀሙን በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። በሌላ በኩል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት በዲጅታል የሙስና መጠቆሚያ 251፣ በሌሎች አማራጮች (በአካል፣ በኢሜል፣ በስልክ) ደግሞ 60 በድምሩ 311 ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች የቀረቡ መሆኑን ያነሳው አገልግሎቱ 270ቹ ተጣርተዋል ብሏል። በቀረቡ ጥቆማዎች መሰረትም ተጣርቶ ጥፋተኛ መሆናቸው ከተለዩ 118
Feb 51 min read


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፉት 6 ወራት ባካሄደው 13 የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከ1.3 ትሪሊዮን በላይ ብር ከገበያው መሰብሰቡን ተናገረ።
ጥር 25/2018 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፉት 6 ወራት ባካሄደው 13 የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከ1.3 ትሪሊዮን በላይ ብር ከገበያው መሰብሰቡን ተናገረ። ላኪዎች፣ በዶላር ቤት የሚያከራዩ፣ በህጋዊ መንገድ ዶላር የሚያገኙ ሁሉ ያለ ገደብ ዶላራቸውን በባንክ ማስቀመጥና በፈለጉ ጊዜ መጠቀም እንዲችሉ ይደረጋል ተብሏል። ባንኩ ይህን የተናገረው የራሱን እና የተጠሪ ተቋማትን የ6 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርት ዛሬ በፓርላማው ቀርቦ ለፕላን ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ ነው። ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ አንዱ ዶላርን ለባንኮች በጨረታ እያቀረበ ብርን ከገበያው መሰብሰብ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ በፓርላማ ተገኝተው ሪፖርቱን በንባብ ያቀረቡት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር
Feb 21 min read


ኢትዮጵያ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጋር በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ ደርሳበት የነበረው የብድር ሽግሽግ ሳይሳካ ቀረ፡፡
ጥር 22/2018 ኢትዮጵያ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጋር በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ ደርሳበት የነበረው የብድር ሽግሽግ ሳይሳካ ቀረ፡፡ የብድር ሽግሽጉን በተመለከተ ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ጠበቃ ቀጥራ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጋር ንግግር ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል፡፡ ከሳምንታት በፊትም በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም አሳውቀው ነበር፡፡ ይሁንና ስምምነታቸው ስራ ላይ ይውል ዘንድ የአለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት IMF እና የቡድን 20 ሃገራት የአበዳሪዎች ኮሚቴ ይሁንታ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡ ታዲያ የቡድን 20 ሃገራት የአበዳሪዎች ኮሚቴ እንዳለው ኢትዮጵያ ከወጭ ንግድ የምታገኘው ገቢ IMF ከተነበየው በላይ ከሆነ ከምታገኘው ገቢ 2 ነጥብ 75 በመቶ ለዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች በተጨማሪነት እንድትከፍል የሚጠይቀው የስምምነት አካል ኢትዮጵያ ብትስማማበትም
Jan 301 min read


ኢቲኬር የስፓይሩሊና ምግብ አጋዥ እና የውበት መጠበቂያ ምርቶችን እንዲያመርት ፍቃድ ተሰጠው።
ጥር 22/2018 ኢቲኬር የስፓይሩሊና ምግብ አጋዥ እና የውበት መጠበቂያ ምርቶችን እንዲያመርት ፍቃድ ተሰጠው። ስፓይሩሊና በያዘው ከፍተኛ ፕሮቲን እንደ አጋዥ ምግብ ወይንም ሰፕልመንት የሚመርጥ እንዲሁም ለውበት መጠበቂያነት የሚያገለግለውና በውሃ አካላት ላይ የሚገኘውን አልጌ ነው። ኢቲ ኬራ ስፓይሩሊና አልጌን ለአጋዥ ምግብነትም ፣ ለውበት መጠበቂያም አድርጎ እንዲያመርት የመጠቀሚያ ፈቃድ የሰጠው የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ነው፡፡ ይህን ስምምነትም በዛሬው እለት በኢቲኬር ፕሮዳክት መስራችና ባለቤት አቶ ማቲዮስ መባ እና የብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ (ዶ/ር) መካከል ተፈርሟል። ስፓይሮሊና አልጌን የመሳሰሉ የብዝሃ ሕይወቶችን ለመጠቀም ፣ ለማምረት ፍቃድ ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲት
Jan 301 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

