top of page

የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ የገንዘብ እርዳታ ሊደረግላቸው ነው፡፡

  • 2 hours ago
  • 1 min read

መጋቢት 9/2018


የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ የገንዘብ እርዳታ ሊደረግላቸው ነው፡፡


ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋሉ ዘርፍ ሴቶች እንዲሰማሩ ይበረታታሉ ብሏል፡፡


አለም አቀፍ የመልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ቀንን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እያከበረች ነው።


በየዓመቱ መጋቢት 9 ቀን ወይም እንደ እ.ኤ.አ ማርች 18 ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የመልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እየተከበረ መሆኑን ሰምተናል።


"ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ሀብት ነው" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን አለም አቀፍ ኩነትን መሰረት በማድረግ "ቆሻሻን ወደ ዕድል እንቀይር ሴቶችንና ወጣቶችን በኢኮኖሚ እናብቃ" በሚል ሀሳብም በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል።


የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፔትኮ ኢትዮጵያ ከተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ጋር በመተባበር ያሰናዳው መርሀ ግብር ነው፡፡


የወዳደቁ ቁሶችን ሰብስቦ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ያስፈለገበት የመጀመሪያው አላማ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ነው ተብሏል፡፡


በዚህም ፔትኮ ኢትዮጵያ ፕላስቲክን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውሉ ድርጅቶችን ከመደገፍ ባለፈም በሚፈለገው መጠን ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን አዳዲስ የህግ ማዕቀፎች እንዲጨመሩ፣ መሻሻል ያለባቸው እና ክፍተት የታየባቸው ህጎችም እንዲስተካከሉ ጭምር እሰራለሁ ነው ብሏል።


በተለይም ደግሞ ሴቶች ባሉበት ሆነው በቀላሉ ከወዳደቁ ግብአቶች የተለያዩ ለአገልግሎት የሚውሉ ምርቶችን እንዲሰሩ ማድረግ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የተናገረው ፔትኮ ኢትዮጵያ የራሳቸውን ገቢ እንዲኖራቸው እና ኢኮኖሚያቸው የተሻለ እንዲሆን ስራዎችን እከውናለሁ ማለቱን ሰምተናል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page