በተያዘው በጀት ዓመት 6 ወራት በስነ ምግባርና እና ብልሹ አሰራር ምክንያት 651 የሚሆኑ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ።
- sheger1021fm
- 38 minutes ago
- 1 min read
ጥር 28/2018
በተያዘው በጀት ዓመት 6 ወራት በስነ ምግባርና እና ብልሹ አሰራር ምክንያት 651 የሚሆኑ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተነገረ።
አስተዳደራዊ እርምጃዎች ከተወሰደባቸው 651 ሰራተኞች የተሰናበቱ 13፣ የደመወዝ ቅጣት 481 እና 157 ደግሞ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተነግሯል።
ይህ የተነገረው አገልግሎቱ የ2018 በጀት ዓመት 6 ወራት አፈፃፀሙን በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
በሌላ በኩል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት በዲጅታል የሙስና መጠቆሚያ 251፣ በሌሎች አማራጮች (በአካል፣ በኢሜል፣ በስልክ) ደግሞ 60 በድምሩ 311 ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች የቀረቡ መሆኑን ያነሳው አገልግሎቱ 270ቹ ተጣርተዋል ብሏል።

በቀረቡ ጥቆማዎች መሰረትም ተጣርቶ ጥፋተኛ መሆናቸው ከተለዩ 118 ሰራተኞች መካከል፤ በ75 ሰራተኞች ላይ ልዩ ልዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስዶባቸዋል ተብሏል።
ሌሎች በሂደት ላይ ይገኛሉ ያለው አገልግሎቱ በዚህም 14 የፅሁፍ፣ 47 የደሞዝ ቅጣት፣ 2 ከቦታ ማንሳት፣ 5 ስንብት እንዲሁም 7 ጉዳያቸው ተጣርቶ ነፃ የተባሉ ናቸው ብሏል።
በሌላ በኩል የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት የፈፀሙ 18 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቶ የ2 ሺህ ብር መቀጮ እና 2.95 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ተደርጓል መባሉንም በመግለጫው ላይ ሲነገር ሰምተናል።
የመሰረተ ልማትና ንብረት ስርቆት እና ውድመት ባደረሱ 14 ግለሰቦች ላይ ደግሞ ክስ ተመስርቶ ከ2 ሺህ ብር መቀጮ ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት ድረስ እንዲቀጡ በፍርድ ቤት ተወስኖባቸዋል ተብሏል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7








