አቢሲንያ ባንክ ‹‹ይጀምሩ፣ ያድሱ እና ይደጉ›› በሚል መሪ ቃል ለሁለት ወራት ያህል ባካሄደው ፕሮግራም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ተናገረ።
- Feb 26
- 1 min read
የካቲት 19/2018
አቢሲንያ ባንክ ‹‹ይጀምሩ፣ ያድሱ እና ይደጉ›› በሚል መሪ ቃል ለሁለት ወራት ያህል ባካሄደው ፕሮግራም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን ተናገረ።
ከዚህ በተጨማሪም 140 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን አስረድቷል።
ባንኩ ፕሮግራሙን ሲያካሂድ የነበረው አዳዲስ ደንበኞችን ለመመልመል፣ ነባር ደንበኞችን ከባንኩ ጋር ያላቸውን ደንበኝነት ለማደስ እንዲሁም ተቀማጭና የውጭ ምንዛሬ ግኝቶችን ለማሳደግ አስቦ እንደነበር ተጠቅሷል።
ይህ ፕሮግራም ከህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥር 29 / 2018 ዓ.ም. ድረስ ሲካሄድ ቆይቷል ተብሏል።
አቢሲኒያ ባንክ በዚህ መርሃግብር ደንበኞቹ ለማበረታታት ሽልማት አዘጋጅቷል።
በዚህ መርሀ ግብር ለሽልማቱ ተሳታፊ የሆኑት ከብር 1000 ሺሕ ብር ጀምሮ ተቀማጭ ያደረጉ አዲስ እና ነባር ደንበኞች፣ ከባንኩ ጋር በአጋርነት ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በባንኩ ዲጂታል ውጤቶችን ተጠቅመው ክፍያ የፈጸሙ፣ 50 የአሜሪካን ዶላር እና ከዛ በላይ የመነዘሩ እና ተቀማጭ ያደረጉ ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪም ከወረቀት ነጻ የባንክ አገግሎትን ለመጠቀም አስቻይ የሆኑትን የጣትና የፊት ገጽታ አሻራ የሰጡ እንዲሁም የATM ካርድ እና ሞባይል ባንኪንግ ንቁ ያደረጉ ደንበኞች ይገኙበታል ተብሏል።
በዛሬው እለትም የዚህ ሽልማት አሸናፊዎች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አዳራሽ ታውቀዋል።
አንድ ዘመናዊ የቤት ተሽከርካሪ ፣ ሦስት ላፕቶፖች፣ ሦስት ቴሌቪዥኖች እና አንድ የልብስ ማጠቢያ ማሽን በድምሩ ስምንት ዕጣዎች ለባለ እድለኞቹ የሚሰጡ ሽልማቶች ናቸው።
ባንኩ ወደፊትም የደንበኞቼን ቁጥር ይበልጥ ለማሳደግ፣ አዳዲስ የዲጂታል የባንክ ተጠቃሚዎችን ለመመልመል፣ እንዲሁም የሀብት ማሰባሰብ ሥራዎችን የሚያሳድጉ ማበረታቻዎችን በመቅረጽ አገልግሎቱን አጠናክሬ እቀጥላለሁ ብሏል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments