ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገሮች ልዩ ከሚያደርጓት ስርዓቶች አንዱ የቡና አፈላል ስርዓቷ ነው፡፡
- 17 minutes ago
- 1 min read
የካቲት 17/2018
ኢትዮጵያን ከሌሎች ሀገሮች ልዩ ከሚያደርጓት ስርዓቶች አንዱ የቡና አፈላል ስርዓቷ ነው፡፡
ቡና በኢትዮጵያ ከተሞችም ሆነ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ የተለየ የአቀራረብ ስርዓት አለው፡፡
ይህ የቡና አፈላል ሥርዓትና ሂደት ኢትዮጵያ አለማቀፍ ቅርስ አድርጋ ለማስመዝገብ ስራ መጀመሯም እየተነገረ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የቡና አፈላል ሥርዓት (የቡና ሥነ-ሥርዓት) በዓለም አቀፉ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ለማድረግ ስራ ከጀመረች ሰንብታለች፡፡
ኢትዮጵያ የቡና (Arabica Coffee) መገኛ ምድር ብቻ ሳትሆን፣ ቡናን ከመጠጥነት ባለፈ የማኅበራዊ መስተጋብር፣ የሰላም፣ እና የባህል መገለጫዋ እንደሆነ ይነገራል፡፡
በተጨማሪም የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት በኢትዮጵያውያን ዘንድ የዕለት ተዕለት ሕይወት አካል ነው ያሉት በአዲስ አበባ UNESCO ላይዘን ቢሮ የባህል ፕሮግራም ሀላፊ አቶ ጌቱ አሰፋ ይህ ሥርዓት በዩኒስኮ መመዝገቡ የሰው ልጅን የጋራ ባህል እሴት ለማሳደግ ይረዳናል ብለዋል፡፡
ይህ ሥርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ መመዝገቡ የቱሪዝም፣ የገበያ እድል እና ሌሎች መልካም አጋጣሚዎችን ይዞልን ይመጣል የተባለ ሲሆን እስከ መጭው አመት ድረስ የሚያስፈልጉ መረጃዎች ተሰባስበው ይቀርባሉ መባሉን ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments