top of page

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፉት 6 ወራት ባካሄደው 13 የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከ1.3 ትሪሊዮን በላይ ብር ከገበያው መሰብሰቡን ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • 11 minutes ago
  • 1 min read

ጥር 25/2018


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፉት 6 ወራት ባካሄደው 13 የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከ1.3 ትሪሊዮን በላይ ብር ከገበያው መሰብሰቡን ተናገረ።


ላኪዎች፣ በዶላር ቤት የሚያከራዩ፣ በህጋዊ መንገድ ዶላር የሚያገኙ ሁሉ ያለ ገደብ ዶላራቸውን በባንክ ማስቀመጥና በፈለጉ ጊዜ መጠቀም እንዲችሉ ይደረጋል ተብሏል።


ባንኩ ይህን የተናገረው የራሱን እና የተጠሪ ተቋማትን የ6 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርት ዛሬ በፓርላማው ቀርቦ ለፕላን ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ ነው።


ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ አንዱ ዶላርን ለባንኮች በጨረታ እያቀረበ ብርን ከገበያው መሰብሰብ እንደሆነ ተናግሯል፡፡


በፓርላማ ተገኝተው ሪፖርቱን በንባብ ያቀረቡት የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ዘርዝረዋል።

ከዚህ ውስጥ እንዱ ዶላርን በጨረታ ለባንኮች ማቅረብ ነው ብለው ይህም ሁለት ጥቅም እንዳለው አስረድተዋል።


ገንዘብን ከገበያው ለመሰብሰብ ያግዛል፣ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙም ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል ።


በዚህም ባለፉት 6 ወራት ብሔራዊ ባንኩ 13 ዙር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አድርጎ ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ሰብሰቧል ሲሉ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) አስረድተዋል ።


በሌላ በኩል ገዢው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ሥርዓትን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት ከዚህ በኋላ አላስፈላጊ ገደቦች ይነሳሉ ብለዋል።


ነጋዴውም ሆነ ሌላው ያስቀመጠውን የውጭ ምንዛሬ ያለ ገደብ እንዲያገኝ ለማድረግ ይሰራል ሲሉ ተናግሯል ።


ስራ ፈጣሪዎች፣ ለኪዎች፣ ቤታቸውን በውጭ ምንዛሬ የሚያከራዩ ሰዎችን ጨምሮ በህጋዊ መንገድ ዶላር የሚያገኙ ሁሉ፣ ያለ ገደብ የራሳቸውን ወይንም ያስቀመጡትን የውጪ ምንዛሬ እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል።


ይህ ዜጎች ያለ ስጋት ገንዘባቸውን እንዲጠቀሙ እና በባንኮች እንዲያስቀምጡ በራስ መተማመንን ይፈጠራል ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዢው እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) አብራርተዋል።


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page