top of page

''ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ብድር የምትፈልጉ ኑ ወደ እኔ በቂ የብድር ገንዘብ ተዘጋጅቶላችኋል'' የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

  • 7 minutes ago
  • 1 min read

የካቲት 11/2018


''ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ብድር የምትፈልጉ ኑ ወደ እኔ በቂ የብድር ገንዘብ ተዘጋጅቶላችኋል'' ሲል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥሪ አቀረበ።


ባንኩ በዚህ ዘርፍ በአሁኑ ሰዓት ብዙ የብር ጥያቄዎች የሉብኝም ብሏል።


ባንኩ ይህን ያለው በረመዳን ወር የእልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቹ ዘካ ለመስጠት የሲቢኢ ኑር የዘካ ቁጠባ ሂሳብን እንዲገለገሉ ጥሪ ባቀረበበት ፕሮግራም ላይ ነው፡፡


ባንኩ ‘አብሮነትና በጎነት በረመዳን' ሲል የጠራውን ፕሮግራም በዛሬው እለት አስጀምሯል።


የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል የዘካ ቁጠባ ሂሳብ አንዱ መሆኑን አስታውሰው በተለይ  በረመዳን የእምነቱ ተከታዮች እንዲገለገሉበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡


አገልግሎቱ የዘካ ሰጪና ተቀባዮችን ጊዜ፣ ወጪ፣ ልፋትና መጉላላት የሚቀንስ፤ ተቀባዮች የተረጂነት ስሜት ሳይሰማቸው ክብራቸውን በጠበቀ መልኩ መቀበል የሚያስችላቸውና የጥሬ ገንዘብ ገደቦችን የሚያስቀር መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰዋል።


ፕሬዚዳንቱ የባንኩ ደንበኞች በረመዳን ወር ከዘካ እና የዒድ ተቀማጭ ሂሳቦች በተጨማሪ በሲቢኢ ኑር በኩል እየሰጣቸው ያሉትን የባንክ አገልግሎቶች ተጠቃሚ  እንዲሆኑ  ጋብዟል። 


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 11 ዓመታት ሆኖኛል ብሏል።


በአጠቃላይ በወለድ ነፃ ዘርፍ የተሰበሰበው ቁጠባ መጠን 267 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተነግሯል።


ከሰበሰበው ተቀማጭ ከ210 ቢሊዮን በላይ ለደንበኞች ፋይናንስ ተደርጓል ተብሏል።


ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ዘንድሮ በስምንት ወራት ውስጥ ብቻ 6.1 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን፣ከግብር በፊትም 3.75 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አቶ አቤ አስረድተዋል።


በዚህ የወለድ ነፃ አገልግሎት ዘርፍ በአሁኑ ሰዓት ብዙ ተበዳሪዎች የሉንም ያሉት ፕሬዚዳንቱ በተለይ ስራ ፈጣሪዎች መጥተው ይበደሩ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page