top of page

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መዋዕለ ነዋያቸውን ፈሰስ ለሚያደርጉ ባለሀብቶች እምነት እንዲያደርጉ ቢያስችላቸውም በየጊዜው የሚለዋወጡ ህጎች ግን አሁንም ችግር ሆኖ ቀጥሏል ተባለ፡፡

  • 4 hours ago
  • 1 min read

የካቲት 12/2018  

 

ኢትዮጵያ እያደረገቻቸው ያሉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሀገሪቱ መዋዕለ ነዋያቸውን ፈሰስ ለሚያደርጉ ባለሀብቶች እምነት እንዲያደርጉ ቢያስችላቸውም በየጊዜው የሚለዋወጡ ህጎች ግን አሁን ኢንቨስት ለሚያደርጉ ችግር ሆኖ ቀጥሏል ተባለ፡፡

 

ከውጭ የሚመጣ ሀብት በተወሰኑ ዘርፎች ላይ ብቻ ማዋሉም ሌሎች ዘርፎች በቂ ፋይናንስ እንዳያገኙ ከልክሏል ተብሏል፡፡

 

እንደ ትምህርት ፣ ጤና ፣ አነስተኛ እና ጥቃቅን ስራ ፈጠራ በመሳሰሉ ማህበራዊ ዘርፎች የሚሳተፉና ተዕኖ የሚያሳድሩ፣ ትርፍም የሚያገኙ ተቋማት የኢንቨስትመንት ሁኔታ ምን ይመስላል በሚል የተደረገ የምክክር መድረክ ላይ ነው ወሬው የሰማነው፡፡


ዝግጅቱን ያሰናዳው ACE investment እና Impact Advisors የተባለ የኢትዮጵያ ተቋም ከአለም አቀፉ  አቀፍ GSG ተቋም ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡

 

ተቋማቱ ባለፉት 4 ወራት በኢትዮጵያ በትምህርት ፣ ጤና በመሳሰሉት ማህበራዊ ዘርፎች የተሰማሩና ትርፍ የሚያገኙ ተቋማት የኢንቨስትመንት ሁኔታ ምን እንደሚመስል ፣ አበርታችን ነገሮች የሚታዩ ችግሮች ላይ ዳሰሳ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page